Thursday, November 26, 2020

Humanitarian aid is being provided in areas controlled by the Tigray Defense Forces

በትግራይ ክልል የመከላከያ ሠራዊቱ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች የሰብአዊ እርዳታ እየቀረበ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
*****************

በትግራይ ክልል የመከላከያ ሠራዊቱ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች የሰብአዊ እርዳታ እየቀረበ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስታወቀ።

የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል ለሚገኙ ዜጎች የሚያስፈልገውን የሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ ትኩረቱን ሰጥቶ እንደሚሰራም አስታውቋል።

መንግስት በቀጣይም ከአጋር ለጋሽ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ያስታወቀው።

በክልሉ በተለይ ከመኖሪያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ በአፋጣኝ ለማድረስ የሰላም ሚኒስቴር ከሌሎች የፌዴራል ተቋማት ጋር በጋራ እየሰሩ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም የምግብ፣ የመጠጥ ውሃ፣ መድሀኒት እና ሌሎች ምግብ ነክ ያልሆኑ አቅርቦቶችን የፌዴራል መንግስቱ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች በካንፖች ውስጥ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ማቅረብ ተጀምሯል።
 
በስፍራው በአሁኑ ወቅት አራት ስደተኞችን ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚሆኑ ካምፖች ለማቋቋም እየተሰራ ሲሆን ይህን ለማስተባበር የተቋቋመው ኮሚቴም ዜጎችን በፍቃዳቸው መልሶ ለማቋቋም እንደሚሰራ ተገልጿል።

መንግስት የተሰደዱ ኢትዮጵያውያንን መልሶ ለማቋቋም እና የተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎችን ጨምሮ ከሁሉም ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች ጋር በጥምረት ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጧል።
Humanitarian aid is being provided in areas controlled by the Tigray Defense Forces
 *****************

 The Prime Minister's Office announced that humanitarian assistance is being provided in areas under the control of the Tigray Defense Forces.

 He said the federal government will focus on providing humanitarian assistance to the people of Tigray State.

 He said the government will continue to strengthen its support to partner donors.

 The Ministry of Peace is working with other federal institutions to provide immediate assistance to the displaced people in the state.

 As a result, food, drinking water, medicine, and other non-food items were provided to IDPs in camps controlled by the federal government.

 Work is currently underway to set up camps for four refugees, and the committee will work to rehabilitate them voluntarily.

 The government reaffirmed its commitment to rehabilitate displaced Ethiopians and work with all international aid agencies, including the United Nations.

No comments:

Post a Comment