Shop Amazon

Saturday, November 21, 2020

Government will do everything possible to ensure stability in Tigray and free our citizens from harm and deprivation: Prime Minister Abiy Ahmed

መንግሥት በትግራይ ክልል መረጋጋት እንዲሰፍን እና ዜጎቻችን ከጉዳት እና እጦት ነፃ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
****************************

የፌዴራል መንግሥት ለትግራይ ሕዝብ አጠቃላይ ደኅንነት እና ጤንነት ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጥ ስለሆነ፣ በትግራይ ክልል መረጋጋት እንዲሰፍን እና ዜጎቻችን ከጉዳት እና እጦት ነፃ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሕግ ማስከበር ተልእኮው የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ባለፉት ጥቂት ቀናት ያስመዘገበው ድል የሚደነቅ ነው። 

ሠራዊታችን ትናንት ምሽት በአዲግራት ዙሪያ ያሉትን አካባቢዎች ከተቆጣጠረ በኋላ ዛሬ ደግሞ አዲግራትን ከሕወሓት ኃይል ሙሉ በሙሉ ነፃ አውጥቷል ብለዋል። 

የፌዴራል መንግሥት በተቆጣጠራቸው ከተማዎች እና አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች፣ በፀጥታ ኃይሎች ጥበቃ እየተደረገላቸው ወደ ዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው መመለስ ጀምረዋል።
ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በመሆን፣ ሰብአዊ እና ማኅበራዊ ፍላጎቶች የሚሟሉበትን መንገድ እናመቻቻለን ሲሉ ተናግረዋል። 

የሰብአዊ ድጋፍ ክንውኖችን ለመከታተል በፌዴራል መንግሥት የተዋቀረው ከፍተኛ ኮሚቴ፣ ተመጣጣኝ እና ወቅታዊ ድጋፍ ለማቅረብ የሚያስችል መረጃን እንዲያሰባስቡ ተጨባጭ ሁኔታውን የሚያጣሩ ልዑካንን ወደ ስፍራው መላኩንም ገልጸዋል።

በተጨማሪም ኮሚቴው ባለፉት ቀናት መኖሪያቸውን ጥለው የተሰደዱትን ዜጎች ሁሉ ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ እና ለማቋቋም ከባለድርሻ አካላት ጋር መሥራቱን እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

Government will do everything possible to ensure stability in Tigray and free our citizens from harm and deprivation: Prime Minister Abiy Ahmed
 *******************************

 Prime Minister Abiy Ahmed said the federal government attaches great importance to the overall well-being and health of the people of Tigray.

 The success of the Ethiopian Defense Forces over the past few days is commendable.

 "Our forces took control of the area around Adigrat last night and today they have completely liberated Adigrat from the TPLF," he said.

 Citizens in federally controlled towns and areas began to return to normal activities under the protection of security forces.
 "We will work with the entire Ethiopian people to ensure that our humanitarian and social needs are met," he said.

 He said a high-level committee set up by the federal government to monitor humanitarian activities has sent a fact-finding mission to gather information to provide adequate and timely support.

 The committee also said it will continue to work with stakeholders to repatriate and resettle all displaced persons in the past few days.

No comments:

Post a Comment