የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Tuesday, December 1, 2020

በአማራ ክልል የሚገኙ 23 ከተሞች በከተማ አስተዳደርነት እንዲመሩ መወሰኑ ተገለጸ

በአማራ ክልል የሚገኙ 23 ከተሞች በከተማ አስተዳደርነት እንዲመሩ መወሰኑ ተገለጸ 
*************************

በአማራ ክልል የሚገኙ 23 ከተሞች በከተማ አስተዳደርነት እንዲመሩ መወሰኑ ተገልጿል፡፡

በከተሞች የአደረጃጀት ፈርጅ መወሰኛና ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 65/2001 መሰረት መስፈርት አሟልተው የተገኙ 23 ከተሞች ከፈርጅ ሶስት ወደ ፈርጅ ሁለት የደረጃ ሽግግር ማለትም በከተማ አስተዳደርነት ለመመራት በክልሉ ከተማ ልማትና ቤቶች ኮንስትራክሽን ቢሮ አጥንቶ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ተቀብሎ ም/ቤቱ አጽድቋል፡፡

ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ በስፋት መክሮ የከተሞችን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ከመፍታትና ወደ ፊት ያላቸውን የመልማት ዕድል የተጠቀሱ ከተሞችን የደረጃ ሽግግር አጽድቋል፡፡

በዚህም መሰረት ከደቡብ ጎንደር ዞን ወገዳ፣ሀሙሲት እና እብናት፣ከአዊ ብሄረሰብ ዞን አዲስ ቅዳም፣አገው ግምጃ ቤት፣ፈንድቃ፣ከምስራቅ ጐጃም ዞን ደብረ ወርቅ፣ሉማሜ አማኑኤል እና ግንደ ወይን፣ከምዕራብ ጐጃም ዞን ሽንዲ፣ጅጋ ከተሞች ይገኙበታል፡፡

ከደቡብ ወሎ ዞን ከለላ፣ቱሉአውሊያ፣ሀርቡ፣አቅስታ፣ደጎል፣ ከሰሜን ሽዋ ዞን ደብርሲና፣ሞላሌ፣አንዋሪ፣ከሰሜን ወሎ ዞን ጋሸና እንዲሁም ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ደግሞ ቆላ ድባ እና ሻውራ ከተሞች መስፈርቱን ያሟሉ ሆነው በመገኘታቸው በከተማ አስተዳድር እንዲመሩ ተወስኗል፡፡

በመሆኑም ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ የተጠቀሱ ከተሞች ከፈርጅ ሶስት ወደ ፈርጅ ሁለት የደረጃ ሽግግር በማድረግ የከተማ አስተዳደርነት ዕውቅና እንዲያገኙ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ወስኗል፡፡

ተግባራዊነቱን በተመለከተም ክልሉ ካለበት ነባራዊ ሁኔታ አንፃር የበጀት እጥረት ያገጠመ በመሆኑ የደረጃ ሽግግር የተፈቀደላቸው 23ቱ ከተሞች ከክልል የስራ ማስኬጃም ይሁን ሌላ በጀት የማይመደብ መሆኑን አውቀው በራሳቸው በጀት ቁጠባን መሰረት በማድረግ ወደ ስራ መግባት እንዳለባቸው ማስታወቁን ከአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡


No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Curated Products for Generation X

https://amzn.to/3VhbwJz GenX Essentials - Curated Products for Generation X ...

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon