Wednesday, December 2, 2020

ጀግናዋ ም/አስር አለቃ ከሀዲውን ኮሎኔል ማንቁርቱን ይዛ አስረከበች

ሕዳር 23 ቀን 2013 

ጀግናዋ ም/አስር አለቃ ከሀዲውን ኮሎኔል ማንቁርቱን ይዛ አስረከበች ።

20ኛ ቃሉ ክ/ጦር ሰሜን ዕዝ ካሏት የጦር ክፍሎች ውስጥ አንዱ ነው። በዚህ ክ/ጦር 1ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አባል የሆነችው ምክትል አስር አለቃ ገባያነሽ ደባልቄ የሻለቃው አዛዥ ኮሎኔል ሰለሞን ገ/ዮሃንስ አጃቢ ነች ። ጁንታ መሆኑን ግን አታውቅም ።

የእብሪት ርምጃቸው ከመጀመሩ ከ3 ቀናት በፊት ሰራዊቱ የምግብና መጠጥ አገልግሎት የሚያገኝባቸውን መንገድ በመዝጋት ሰራዊቱን ለከፍተኛ ርሃብና ጥም ዳርጏል ።

ሁሉም የሰራዊት አባል የግል ትጥቁን በአንድ ክፍል በማስቀመጥ በህብረተሰብ የድጋፍ ስራዎች ላይ እንዲረባረብ ማድረጉን ትናገራለች ።

በተለይም ጥቅምት 24 ቀን 2013 ምሽት ላይ ሁሉንም የጥበቃ ቦታዎች በትግራይ ተወላጅ የሰራዊት አባላት እንዲሸፈኑ በማድረግ ፣ የከሃዲው ቡድን ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ምንም አይነት ዝግጅትና ትጥቅ ባልነበረው ሰራዊታችን ላይ ከፍተኛ ተኩስ እንዲከፍትም አድርጏል ብላለች ።

ሆኖም ታላቅ ጀግንነትና ኢትዮጵያዊ ማንነትን የወረሰው ጀግናው ሃይላችን የማይታሰቡ ጀብዶችን ጭምር በመፈፀም ፣ ወደ ኤርትራ ስልታዊ ማፈግፈግ በማድረግ ራሱን ማዳን ችሏል ብላለች ።

በዚህ ሁሉ ግፍና በደል መሃል የሻለቃዋ ዋና አዛዥና ለዘመናት የመራቸውን የሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የካደው ኮሎኔል ሰለሞን ገ/ዮሃንስ ራሱን መፀዳጃ ቤት ውስጥ በመደበቅ በጁንታው የተሰጠውን ተልዕኮ መፈፀም እንደጀመረ በሃዘን ስሜት ውስጥ ሆና አስታውሳለች ።

ውትድርና በኢትዮጵያዊነት ፍቅር መታጠብና በጀግንነት ካባ መድመቅ ነው የምትለው እንስቷ ጀግና ፣ ራስህን ለሃገር አሳልፈህ ከሰጠህ ኢትዮጵያዊ መሆን ብቻውን ጀግንነትን ይወልዳል ስትል የቀድሞ አለቃዋን እንዴት ከስሯ እንዲንበረከክ እንዳደረገችው እንዲህ ታጫውተናለች ።

"... ሰራዊታችን በታፈነበት ጥቅምት 24 ምሽት 2 ሰዓት ላይ በከባድ መሳሪያ የታጀበ ተኩስ ወደ ካምፓችን ተተኮሰ፣ በዚህ ሰዓት ወደ  መፀዳጃ ቤት ራሱን የደበቀው ከሃዲው አዛዥ ተብዬ ፣ እኔ በትግራይ ሚሊሻና ልዩ ሃይል ጥይት ከምሞት አንተን ገድዬ ራሴን አጠፋለሁ አልኩት፣ ተኩሱ በርትቷል፣ ሁሉም ራሱን ለማዳን ወደህሊናው የመጣለትን አማራጭ እየተጠቀመ ይሯሯጣል..."

"... በመጨረሻም ከተደበቀበት መፀዳጃ ቤት እንዲወጣና እኔ የምለውን ብቻ እንዲፈፅም እሽ የማይል ከሆነ ግን እንደምገድለው አስጠነቀቁት፥ እሱም በፍርሃት ውስጥ ሆኖ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ ወደነገርኩት ቦታ መጣ፥ ሽጉጡንና ማዕረጉን እንዲሰጠኝ አደረኩ፣ ከዛም ጫማውን እንዲያወልቅ አድርጌ በየመንገዱ ከማገኛቸው የሰራዊት አባላት ጋር በመተባበርና ሙሉ ለሊት የእግር ጉዞ በማድረግ ኤርትራ ይዤው በመግባት ታማኝ እና ሙሉ ኢትዮጵያዊ ለሆኑ አመራሮች አስረከብኩ  ።"

ሰራዊታችን በራሱ ወገኖች የደረሰበትን በቃላት የማይገለፅ ግፍና በደል ተሸክሞ ቂምን ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ፍቅር አስቀድሞ ለድል በመብቃቱ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማትም ምክትል አስር አለቃ ገበያነሽ ደባልቄ ስሜቷን አጋርታናለች ።

ኢትዮጵያችን ምንም እንኳን በራሱ ጉያ ተወሽቀው ሳቋን እየቀሙ ውርደቷን የሚያፋጥኑና መበተኗን ገሃድ ለማውጣት ሌት ተቀን የሚሯሯጡ ወጪት ሰባሪዎች ቅዠታቸውን ቢኖሩትም ፣ ክብሯን የሚያስጠብቁ ከራሳቸው ህይወት ይልቅ የሃገራችውን ክብር የሚያስቀድሙ ፣ የማይታመን ጀግንነት እየፈፀሙ ኢትዮጵያችንን ከፍ ያደረጉ የበርካታ የቁርጥ ቀን ልጆች ባለቤት ናት ኢትዮጵያ !

ምክትል አስር አለቃ ገባያነሽ ደባልቄም ጀግና ማፍራት የማትሰለቸው ሃገራችን ከሰጠችን እንቁ ኢትዮጵያውያን አንዷ ናት ። እንዳንቺ  አይነት ኩሩ ኢትዮጵያዊ ሁሌም በኢትዮጵያዊ ክብር ደምቆ ይኖራል ።

የከሃዲዎች መጨረሻ ፣ ሃገርን ለማዋረድ ባሴሩት ህልም ውስጥ ተጠልፎ መውደቅ ነው ።

አበበ ሰማኝ ( ከግዳጅ ቀጣና )
ፎቶግራፍ ብርሃኑ ወርቁ

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት በሙሉ እንዲሁም አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አናስተካክላለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment) እንችላለን። የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViberም ሆነ Whatspp ይደውሉልን። ስልክ ቁጥራችን 619 255 5530 ነው ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Translate

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon

Call Yebbo

የቦ ኮሚኒኬሽን ኔት ወርክ ፣ ለ25 አመታት በላይ የስራ ልምድ ያካበተው የእናንተው በእናንተው። ከምሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ የውክልና አገልግሎት መስጠት የኢትዮጵያ ፓስፖርት አገልግሎት መስጠት የቢጫ ካርድ የማውጣት አገልግሎት የታክስ አገልግሎት መስጠት (የትም የኢትዮጵያ ግዛት ይኑሩ) የጉዞ ወኪል የትርጉም ስራ አገልግሎት ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 619-255-5530 ይደውሉ።