ጤና ሚኒስቴር ከ 7 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶዝ በላይ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ድጋፍ ተረከበ!!
_________________
የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባቱን ድጋፍ ያደረጉት አገራት የጀርመን እና የፖርቹጋል መንግስታት ናቸው።
የሁለቱንም መንግስታት ድጋፍ የተቀበሉት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የጀርመን እና የፖርቹጋል መንግስታት ከ7 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶዝ በላይ የጆንሰን የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ለሀገራችን ድጋፍ ማድረጋቸው የኮቪድ-19 ስርጭት በተበራከተበት ወቅት መሆኑ ያለውን ጫና ከመቀነስ አንፃር ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡
የጀርመን እና የፖርቹጋል መንግስታት ለኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ እያደረጉት ያለውን ድጋፉና ትብብር ያደነቁት ዶክተር ሊያ ታደሰ በጦርነቱ የተጎዱ የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረትም የሁለቱም መንግስታት ድጋፉ እንዳይለያቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ለተደረገው ድጋፍም የጀርመን እና የፖርቹጋል መንግስታትን፣ዩኒሴፍን እና የአለም ጤና ድርጅትን አመስግነዋል፡፡በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ዶክተር ሊያ ታደሰ ጠይቀዋል።
በኢትዮጵያ የጀርመን ምክትል አምባሳደር ሄይኮ ኒትሽክ እና የፖርቹጋል ኤምባሲ ተወካይ ጆዋና ማሪንሆ በበኩላቸው መንግስታቸው በኮቫክስ የክትባቶች ዓለም አቀፍ ጥምረት አማካኝነት ለኢትዮጵያ የጆንሰን የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ያደነቁት የሁለቱ መንግስታት ተወካዮች እየጨመረ የመጣውን የኮቪድ-19 ስርጭት ለመግታት መንግስታቸው ወደፊትም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
የጀርመን መንግስት በኢትዮጵያ የጀርመን ምክትል አምባሰደር አማካይነት ሰባት ሚሊዮን አንድ መቶ ዘጠና ሁለት ሺ ስምንት መቶ (7,192,800) እና የፖርቹጋል መንግስት በኢትዮጵያ የፖርቹጋል ኤምባሲ በኩል አንድ መቶ ስልሳ አምስት ሺህ ስድስት መቶ (165,600) ዶዝ የኮቪድ -19 መከላከያ ክትባት ድጋፍ አድርገዋል።
Ministry of Health receives over 7.3 million doses of CV 19 vaccine !!
_________________
The governments of Germany and Portugal are co-sponsoring the CVD vaccine.
Receiving the support of both governments, the Minister of Health, Dr. Leah Tadesse, said that the German and Portuguese governments will provide more than 7.3 million doses of Johnson's Covide-19 vaccine to our country at a time when the distribution of Covd-19 is increasing.
Hailing the support and cooperation of the German and Portuguese governments to the Ethiopian government and people, Dr. Leah Tadesse called on both German and Portuguese governments, UNICEF and the World Health Organization (WHO) to continue their support for the ongoing efforts to rehabilitate war-torn health facilities. Dr. Leah Tadesse asked.
German Deputy Ambassador to Ethiopia Heiko Nietzsche and Portuguese Embassy Representative Joanna Mariho on his part said his government has supported the Johnson-Covide-19 vaccine in Ethiopia through the Covax International Coalition.
Representatives of the two governments praised the ongoing efforts of the Ethiopian government to prevent the spread of CVD-19 and said that their government will continue to strengthen its support to curb the increasing distribution of CVD-19.
No comments:
Post a Comment