Shop Amazon

Thursday, January 13, 2022

Terrorist TPLF has blocked humanitarian access to the people of Tigray - Government Communication Service

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ለትግራይ ህዝብ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይቀርብ እንቅፋት ሆኗል - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
*******************

የትግራይ ክልል ህዝብ ሰብዓዊ የምግብና ምግብ-ነክ ያልሆነ እርዳታ ያለ ምንም መስተጓጎል እንዲቀርብለት፣ የክልሉ አርሶ አደር የክረምት ዝናብን በመጠቀም የራሱን ምርት እንዲያመርትና ከዕርዳታ እንዲላቀቅ መንግስት ሰብዓዊነትን ማዕከል ያደረገ የተናጠል የተኩስ አቁም ማድረጉ ይታወሳል።

ይሁንና የአሸባሪው የህወሓት ቡድን ይህን በጎ ዓላማ ያነገበውን የመንግሥት የተናጠል ውሳኔ ወደ ጎን በማድረግ የፀረ-ህዝብ እና የሽብር አቋሙን በግልፅ ያሳየበትን ተግባር የአማራና አፋር ክልሎችን በመውረር እንዲሁም በክልሎቹ በሚገኙ ንጹሃን ላይ እጅግ ዘግናኝ ወንጀሎችን በመፈጸም ለእኩይ ዓላማ የቆመ ቡድን መሆኑን በግልፅ አስመስክሯል።

መንግሥት ለትግራይ ህዝብ ባለው ውግንና እና የዕለት ደራሽ ዕርዳታ ያለ ምንም መስተጓጐል በአፋር ክልል በአብአላ በኩል በቀጥታ ወደ ትግራይ ክልል እንዲጓጓዝ ባስቀመጠው አቅጣጫ እንዲሁም የአፋር ክልል መንግሥትና ህዝብ ለትግራይ ክልል ባላቸው አጋርነት እ.ኤ.አ ከሐምሌ 12/2021  ጀምሮ በ1010 ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲቀርብ ተደርጓል።

ይሁን እንጂ የአሸባሪው የህወሓት ቡድን የትግራይን ህዝብ በስም ለመነገጃነት ከማዋል ውጪ ቆሜለታለሁ ብሎ ለሚሰብከው ህዝብ እንኳ ሰብዓዊነት የማይሰማው በመሆኑ ዕርዳታ ጭነው ወደ ክልሉ የገቡት 1ሺ10 ተሽከርካሪዎች ተመልሰው ዕርዳታ ጭነው ወደ ክልሉ እንዲመለሱ በማድረግ ፋንታ የአሸባሪው የህወሓት ቡድን ወራሪ ኃይል አማራና አፋር ክልልን ሲወር የሠራዊቱ ማጓጓዣ አድርጐ ተጠቅሞባቸዋል።

ይባስ ብሎ በጊዜያዊነት ወረራ አድርጐ ከቆየባቸው እንደ ኮምቦልቻና ሌሎች አካባቢዎች ከሚገኙ የመንግሥትና የግል መጋዘኖች የዘረፈውን ስንዴና ሌሎች ምግብና ምግብ - ነክ ያልሆኑ አቅርቦቶች በትግራይ ክልል በሚገኙ መጋዘኖች ካከማቸ በኋላ ወደ ትግራይ ክልል ዕርዳታ ማስገቢያ በሆነው በአብዓላ መስመር ወረራ በማካሄድና የከባድ መሣሪያ ተኩስ በመክፈት መስመሩ እንዲዘጋ በማድረግ እ.ኤ.አ. ከዲሴምበር 15/2021 ጀምሮ ዕርዳታ እንዳይቀርብ አስተጓጉሏል።
እንደ አለም ጤና ድርጅት አይነት ለሁሉም ሰው በእኩል ቆመናል የሚሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ግን አሸባሪው ቡድን የአማራ እና አፋር ክልሎችን በወረረበት ወቅት ሆስፒታሎችን እና የጤና ጣቢያዎችን ሲዘርፍና ሲያወድም ንፁሃንን ሲደፍርና ሲገድል የሽብር ቡድኑን ድርጊት ሲያወግዙ አልተደመጡም።

ይልቁንም መንግስት ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ እንዳይገባ እያደረገ ነው በሚል የአሸባሪው ቡድን የሚያሰማውን ፕሮፖጋንዳ ተቀብለው እያስተጋቡት ይገኛል፤ ይህ በመንግስት ዘንድ ፍፁም ተቀባይነት የለውም።

አሁንም ለአንድ ወገን ባጋደለው አቋማቸው በመጽናት የሽብር ቡድኑ ወደ ትግራይ የሰብአዊ እርዳታ እንዳይገባ እንቅፋት መሆኑን በግልጽ አለማንሳታቸው በተዛባ አመለካከታቸው መጽናታቸውን እና ውግንናቸው ለህዝብ ጥቅም ሳይሆን ለፖለቲካ አጀንዳ መሆኑን ያመለክታል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለትግራይ ክልል ህዝብ የዕለት ደራሽ እርዳታ ያለ ምንም መስተጓጎል እንዲቀርብ ለማስቻል በየጊዜው ከአጋር አካላት ጋር ምክክር በማድረግ እየሠራ ይገኛል።

ምንም እንኳ ቀደም ብለው እርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ ክልል ገብተው ያልተመለሱ 1ሺ10 ከባድ ተሽከርካሪዎች በክልሉ መኖራቸውን እያወቀ በዓለም ምግብ ፕሮግራም ባለቤትነት ሥር ያሉ 118 ከባድ ተሽከርካሪዎች በሙሉ አቅማቸው የእርዳታ ማጓጓዝ ሥራ እንዲሰሩ ፈቅዷል፤ እርዳታውን ለሚያጓጉዙ ሾፌሮችም ሙሉ የደህንነት ዋስትና እንዲያገኙ አድርጓል።
 
ከዚህም በላይ በቀጣይነት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታትና የዕርዳታ አቅርቦቱ ያለ እንቅፋት እንዲከናወን ለማድረግ ያለው ቁርጠኝነት እንደተጠበቀ ነው።

በመጨረሻም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብና አጋር አካላት የአሸባሪውን የህወሓት ቡድን እኩይ ተግባርና የእርዳታ እንቅስቃሴ አደናቃፊነት እንዲኮንኑ እያሳሰብን መንግሥት እንደ ወትሮው የዕርዳታ አቅርቦቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግ የበኩሉን ሁሉ እንደሚወጣ እንገልጻለን።
Terrorist TPLF has blocked humanitarian access to the people of Tigray - Government Communication Service
 *******************

 It is to be recalled that the government has imposed a humanitarian-centric ceasefire in order to ensure that the people of the Tigray region receive humanitarian food and non-food assistance without interruption.

 However, the terrorist group, the TPLF, has clearly demonstrated its anti-people and anti-terrorism stance by invading the Amhara and Afar regions and committing heinous crimes against innocent people in those regions.

 The government and the people of Tigray have partnered with 1010 trucks from 10/2021 trucks to the Tigray Regional State in the direction of Abala and the Afar Regional State.  Humanitarian aid has been provided.

 However, the T-TPLF invaded Amhara and Afar regions instead of sending 1,010 trucks back to the region, as the T-TPLF invaded Tigray and used it as an inhumane treatment for the people of Tigray.

 To make matters worse, he looted wheat and other food and non-food items from government and private warehouses in Kombolcha and other areas, which he had temporarily invaded, and raided the Abala line, which is a gateway to the Tigray region, and opened fire with heavy artillery.  A.  He has been barred from providing assistance since December 15, 2021.
 However, international organizations such as the World Health Organization (WHO), which claims to be equal for all, have not been heard condemning the terrorist group's looting, destruction of hospitals and health centers, rapes and killings of civilians during the invasion of Amhara and Afar regions.

 Instead, they are echoing the propaganda of the terrorist group that the government is preventing aid from entering the Tigray region.  This is completely unacceptable to the government.

 By remaining steadfast in their one-sided stance, they did not make it clear that the terrorist group was an obstacle to humanitarian access to Tigray, indicating that they persisted in their misconceptions and sided with the political agenda, not the public interest.

 The Ethiopian government regularly consults with stakeholders to ensure that the people of the Tigray region receive daily assistance without interruption.

 The World Food Program (WFP) has allowed 118 trucks to operate at full capacity, despite the fact that there are 1,010 trucks that have not yet returned to Tigray.  It also provides full security for drivers transporting assistance.

 Moreover, he remains committed to solving ongoing problems and ensuring that relief efforts continue unabated.

 Finally, we urge the international community and its partners to condemn the terrorist activities of the TPLF and to obstruct the flow of aid.

 Government Communication Service


የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

No comments:

Post a Comment