Shop Amazon

Tuesday, January 18, 2022

The Feast of Tabernacles is celebrated today by the followers of the Ethiopian Orthodox Tewahedo faith

የከተራ በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ ዛሬ ይከበራል
*****************

የከተራ በዓል በዛሬው ዕለት በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ ይከበራል።

በመላ ሀገሪቱ ታቦታት ከአድባራት ወጥተው በካህናት፣ በዲያቆናት እና በምዕመናን ታጅበው ወደ ጥምቀተ ባህሩ ይወርዳሉ።

ታቦታት ወደ ማደሪያቸው ጥምቀተ ባህር ከደረሱ በኋላም አዳራቸውን በዚያው የሚያደርጉ ሲሆን በካህናትና ዲያቆናት ዝማሬና ሌሎች ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች ይከወናሉ።

በማግስቱ ደግሞ የጥምቀት በዓል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች የሚከበር ይሆናል።

በዓሉ በአዲስ አበባ በጃን ሜዳ በአቅራቢያ የሚገኙ አድባራትና ገዳማት ታቦታት የጥምቀት በዓልን በጋራ የሚያከብሩ ሲሆን በጎንደር ከተማም ከአድባራትና ገዳማት ጉዞ በመጀመር ታቦታቱ ምሽት ላይ ጃን ሜዳ የሚያድሩ ይሆናል።

በዘንድሮ የከተራና የጥምቀት በዓል ላይ “ወደ ሀገር ቤት” ሀገራዊ ጥሪን ተቀብለው የመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በብዛት የሚታደሙበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

የከተራና የጥምቀት በዓላት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩ ሃይማኖታዊና የአደባባይ በዓላት መካከል ይጠቀሳሉ።

ወደ ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ በብሔራዊ ደረጃ የሚከበረውን የከተራ እና ጥምቀት በዓል ለመታደም ወደ ከተማዋ ለሚጓዙ ደንበኞቹ ክብረ ወሰን ሆኖ የተመዘገበ 22 በረራ ማድረጉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማስታወቁም ይታወሳል።

The Feast of Tabernacles is celebrated today by the followers of the Ethiopian Orthodox Tewahedo faith
 *****************

 The Feast of Tabernacles is celebrated today by the followers of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church.

 Throughout the country, the Ark was taken out of the churches and escorted by priests, deacons, and parishioners to the baptismal font.

 After the Ark of the Covenant was baptized, they spent the night there, singing hymns and other religious ceremonies.

 The next day, the baptismal feast will be celebrated with various religious ceremonies.

 Churches and monasteries near Jan Meda in Addis Ababa will jointly celebrate the Feast of Baptism.

 It is expected that this year's Christmas and Baptism Day will be attended by a large number of Ethiopians and people of Ethiopian descent.

 The Feast of Unleavened Bread and Baptism are among the most important religious and public holidays celebrated by Christians.

 Ethiopian Airlines has announced 22 flights to the ancient city of Gondar in honor of its customers.

No comments:

Post a Comment