Sunday, November 15, 2020

ጽንፈኛው የሕወሓት ቡድን በአሸባሪነት እንዲፈረጅ የአማራ ምሁራን መማክርት ጠየቀ

ጽንፈኛው የሕወሓት ቡድን በአሸባሪነት  እንዲፈረጅ  የአማራ ምሁራን መማክርት ጠየቀ
********************
መንግስት በህገ ወጡ የሕወሓት ቡድን ላይ  የጀመረውን ህግ የማስከበር ርምጃ  በህግ ተጠያቂ እስከ ማድረግ  እንዲዘልቅ የአማራ ምሁራን መማክርት ጠይቋል።

ለሁለት ቀናት የዘለቀውን  አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ሲያካሂድ ቆይቶ፣መማክርቱ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

“ኢትዮጵያ እና አማራ ጠል” የሆነውን የሕወሓት ሕገ ወጥ ቡድን ድርጊቱን እንደሚኮንነው መማክርቱ  በመግለፅ ፣ጽንፈኛው የሕወሓት ቡድን በአሸባሪነት  እንዲፈረጅም ጠይቋል።

በመንግስት እየተካሄደ ያለው የህግ የማስከበር እርምጃ እንዲሁም በህግ ተጠያቂ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት እንደሚያደንቅ እና እንደሚደግፍም አመልክቷል።

መማክርቱ ዓመታዊ የእቅድ ክንውኑ ላይ በሰፊው የተወያየ ሲሆን በቀጣይ እቅዶች ዙሪያም መክሯል።

የአማራ ክልል ተቋማትን በሁሉም ዘርፎች ለመገንባት እና በጥናት የተለዩ ችግሮችን  የያዘ የመፍትሔ ሀሳብ በጉባኤው ቀርቧል።

የክልሉን የትምህርት ጥራት ለማሻሻል የመፍትሔ ሃሳቦች ይሆናሉ ያላቸውን የጥናት ውጤቶችም አስቀምጧል።

የአረንጓዴ አሻራ ጅምሮች በሳይንሳዊ መንገድ ማስቀጠል የሚያስችሉ ሳይንሳዊ የሙከራ ስራዎችን መለየቱንም እንዲሁ።

ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ተገቢው ፖለቲካዊ እና አስተዳደራዊ ውክልና ያገኙ ዘንድ ታሳቢ መደረግ ያለባቸው ተግባራትን ለይቶ አቋም መያዙን መማክርቱ በሰጠው  መግለጫው አስታውቋል።

በእስሌማን አባይ
my translation.
Amhara scholars seek advice to classify extremist TPLF as terrorists

 ********************
 Amhara scholars have called for the government to continue its crackdown on illegal TPLF groups.

 Following the two-day annual general assembly, the council issued a statement.

 The council condemned the TPLF's illegal activities in Ethiopia and Amhara, and called for the extremist TPLF to be classified as a terrorist group.

 He expressed his appreciation and support for the government's ongoing law enforcement efforts and efforts to hold it accountable.

 The council discussed the annual plan in detail and discussed future plans.

 The conference proposed solutions to the construction of institutions in the Amhara region in all sectors and identified specific problems.

 He also outlined the findings of research that could be a solution to improve the quality of education in the region.

 It also identifies scientific experiments that can continue the green footprint in a scientific way.

 The council said in a statement that it has identified the issues that need to be considered in order for the Amhara people living outside the region to receive appropriate political and administrative representation.

 By Islam Nile


የህወሓት ጽንፈኛ ቡድን የመከላከያ ሰራዊትና የኤርትራ ሰራዊት የደንብ ልብስን እያመረተ በማጭበርበር ስራ ውስጥ መግባቱ ተገለጸ

የህወሓት ጽንፈኛ ቡድን የመከላከያ ሰራዊትና የኤርትራ ሰራዊት የደንብ ልብስን እያመረተ በማጭበርበር ስራ ውስጥ መግባቱ ተገለጸ
------------------------------------------------
የህወሓት ጽንፈኛ ቡድን የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊትና የኤርትራ ሰራዊት የደንብ ልብስን እያመረተ የማጭበርበር ስራ ውስጥ መግባቱ ተገለጸ፡፡

ከዋልታ ጋር ቆይታ ያደረጉት በሀገር መከላከያ ሰራዊት የኢንዶክተርነሽን ዳይሬክተር ተወካይ ብርጋዴል ጄነራል ኩማ ሚዴቅሳ ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን እየደረሰበት ያለውን ሽንፍት ተከትሎ የኤርትራ ሰራዊት የደንብ ልብስ አመሳስሎ በማምረትና ቅጥረኞችን በማልበስ በቁጥጥር ስር አዋልኩ የሚል ድራማ እየተወነ ነው ብለዋል፡፡

በትግራይ ክልል በሚገኘው አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ በህወሓት ውስጥ የሚገኘው ጽንፈኛ ቡድን የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊትና የኤርትራ ሰራዊት የደንብ ልብስን አመሳስሎ እያመረተ እንደነበረ ይታወቃል ያሉት ብርጋዴል ጄነራል ኩማ፣ የጽንፈኛ ቡድኑ ገና ብዙ ማጭበርበሪያ ስራዎችን እየሰራ በመገናኛ ብዙኃን ሊያስተላልፍ ስለሚችል ህዝቡ ይህን ሊረዳ ይገባል ብለዋል፡፡

ጽንፈኛው ቡድኑ እርስ በእርስ የሚጋጩ የሀሰት ወሬዎችን መንዛቱን እንደቀጠለ እና ለሚሰራቸው ወንጀሎች ሌላን አካል ተጠያቂ ለማድረግ እንደሚጥር ተናግረዋል፡፡

ጽንፈኛ ቡድኑ በኤርትራ መንግስት እንደተመታ አድርጎ የሀሰት ወሬ እየነዛ ነው የተባለ ሲሆን፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከኢትዮጵያም አልፎ ሰላምንና ደህንነትን በማስጠበቅ በኩል ይታወቃል፤ የማንንም የውጪ ጣልቃ ገብነት አይፈልግም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ሀገር መከላከያ ሰራዊት በደረሰበት ጥቃት ቁጭት ውስጥ ገብቶ ይህን ጽንፈኛ ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰራ ነው ያሉት ብርጋዴል ጄነራል ኩማ ህዝቡ የከሃዲው ቡድን የሚነዛውን የሀሰት ወሬ ወደ ጎን በመተው ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ይህ ጽንፈኛ ቡድን የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት የደንብ ልብስንም አመሳስሎ በማምረት ለጥፋት ስራው ተጠያቂ ለማድረግ እየጣረ በመሆኑ ህብረተሰቡ በንቃትና በጥንቃቄ አካባቢውን እንዲቃኝ ብርጋዴር ጄነራሉ አሳስበዋል፡፡

(በመስከረም ቸርነት)

የህወሓት ጦር ከአላማጣ ተሸንፎ ሲባረር በእስር ላይ የነበሩ 10,000 ያህል ሰዎችን ይዞ ሸሽቷል ተባለ።

ህዳር 6፣2013

የህወሓት ጦር ከአላማጣ ተሸንፎ ሲባረር በእስር ላይ የነበሩ 10,000 ያህል ሰዎችን ይዞ ሸሽቷል ተባለ።

የመከላከያ ሰራዊት የራያ የአላማጣ ከተማን ከሕወሓት ነፃ አውጥቷል ሲልም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ ባወጣው መግለጫ ተናግሯል።

የከተማዋ ነዋሪዎች ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በላይ የሆኑ በርካታ የአካባቢው ወጣቶች በአጥፊው ኃይል ለጦርነት እንዳይመለመሉ በመፍራት አካባቢውን ለቀው መሰደዳቸውን ተናግረዋል ተብሏል።

መከላከያ ሠራዊት አላማጣን በቁጥጥር ስር ማዋሉ፣የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራው በሰላማዊ ዜጎች ላይ ተጽዕኖ እንዳያስከትል አስፈላጊው ጥንቃቄ ታክሎበት፣በውጤታማ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ያሳያል ሲል መግለጫው ተናግሯል።


የሕወሓት ጽንፈኛ ቡድን ከአላማጣ አካባቢ በእስረኛ መልክ ይዟቸው የነበሩ ከ10 ሺህ በላይ ወጣቶችን አፍኖ መውሰ...

የመከላከያ ሠራዊት የአላማጣ ከተማ ከጽንፈኛው የህወሓት ታጣቂ ቡድን ተቆጣጠረ ።

በደምቢ ደሎ ዩኒቨርስቲ በፅንፈኛው ህወሃት ቡድን አመራር ሰጭነት በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ አስራ ሰባት ተማሪዎች በመከላከያ ሰራዊታችን ታጅበው አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሰበር ዜና አንኳን ደስ አላችው!!

በደምቢ ደሎ ዩኒቨርስቲ በፅንፈኛው ህወሃት ቡድን አመራር ሰጭነት በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ አስራ ሰባት ተማሪዎች በመከላከያ ሰራዊታችን ታጅበው አዲስ አበባ ገብተዋል።

ተማሪዎቹ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰባቸውም ተገልፆል ክቡር ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ስለተማሪዎቹ ሁኔታ ነገ ፖርላማ ላይ በሚካሄደው ስብሰባ ይገልፃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

እስካሁን በሃገራችን ኢትዮጲያ ደረጃ ዘርንና ሃይማኖትን ተኮር በማድረግ ሲካሄዱ የነበሩ ጭፍጨፋዎችም በፅንፈኛው ቡድን ህወሃት ተልኮ ሰጭነት እና አስተባባሪነት እንደተካሄደም ተረጋግጧል ድል ለኢትዮጲያ ህዝቦች። 

ምንጭ  Afar Media Network

ስለ አማራ ልዩ ኃይል ጀብዱ የተሰጠ ምስክርነት

ስለ አማራ ልዩ ኃይል ጀብዱ የተሰጠ ምስክርነት (ከዒላማቸው ውጭ የመቱ ወታደሮች አላየሁም።)
           =====
ሀያ ሶስት ዓመታት በውጊያ ውስጥ ቆይቻለሁ። እነዚህን የመሰሉ ተዋጊዎች ግን አጋጥሞኝ አያውቅም። ክላሽንኮቭ ቁመው እንደስናይፐር ይተኩሳሉ። ከኢላማቸው ውጭ የመቱ ወታደሮች አላየሁም። የውጊያ ቀጠናቸው ከፊት ለፊቱ ግንባር በግራና በቀኝ ክንፍ ቢሆንም በፍጥነት ስለሚያጠቁ የመሃል ግባሩን ጭምር እነሱ ይሸፍኑት ነበር።

-ሌላው አስገራሚ ባህሪያቸው እጅግ ፈጣን ተዋጊዎች መሆናቸው ነው። ሶስት ቀናት ይፈጃሉ ተብለው የተገመቱትን ከሁመራ በስተ ምዕራብ እና በስተደቡብ ምዕራብ የሚገኙትን አራት ጠቃሚ ወታደራዊ ቦታዎችን በሰባት ስዓታት ብቻ የወገን ጦር ሊቆጣጠር የቻለው በእነሱ ታምራዊ የውጊያ ስልት ነበር።

- ከኤርትራውያን ጋር በዛላንበሳ እና በቡሬ ግንባር ተዋግቻለሁ። ከትግሬዎቹ ጋር አሁን የግንባር ጦርነት ውስጥ ገብተናል። ሁለቱም በፊት ለፊት ጦርነት ብዙም ባይሆኑ በደፈጣና በቆረጣ ውጊያ ድንቆች ናቸው ።
ዐማሮቹ ግን በሁሉም የውጊያ ዓይነቶች ፍጹም ተወዳዳሪ የላቸውም።

-አስቸጋሪ ይሆናሉ ተብለው በተገመቱ ግንባሮች ለመሰለፍ አያመንቱም። እንደውም ጀብዱ ለመፈፀም ካላቸው ፅኑ ፍላጎት የተነሳ የጠላት ጦር ይበረታባቸዋል የተባሉትን ምሽጎች ለመደርመስ ይሽቀዳደማሉ። ጦርነቱ ጋብ ሲል ወደ ማታ የሰው ኃይል ስምሪትና ድልድል ቆጠራ ስናደርግ ከእነሱ ወገን ጥቂትም ቢሆን የጎደለ የለም። ወታደራዊ ስልጠና ብቻውን እንዲህ አያደርግም ከትውልድ የሚተላለፍ አንዳች ድፍረትና ብልሃት ቢኖር እንጅ ብየ አስባለሁ።

-ስለ ዐማራ ልዩ ኃይል እና ስለ ዐማሮቹ ጀግንነት የምገልፅበት ቃላት ባይኖረኘም በቻልኩት አቅምና ባገኘውት አጋጣሚ ለሁሉም ከምንመሰክረው የጦር ሜዳ ውሎየና ከወታደር ታሪኬ አንዱ ይሄው ነው። ኢትዮጵያ ከሁለት ሽህ ዓመታት በላይ ታፍራና ተከብራ የኖረችበት አንዱ ሚስጥር ይሄው ነው።
*
በወልቃይት ሁመራ ግንባር ከዐማራ ልዩ ኃይል ና ሚሊሻ ጋር የተሰለፈ የደቡብ ኢትዮጵያ ተወላጅ የመከላከያ መኮንን ስለ ዐማራ ልዩ ኃይል ጀግንነት ከሰጠው የዓይን ምስክርነት።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ Belete Kassa Mekonnen

Egypt hires $65k monthly US lobbying firm Biden victory


SHARThe Egyptian government has hired a lobbying firm following the success of Joe Biden in the US elections, reports Foreign Lobby.

The $65,000 monthly contract was signed between the Egypt's Ambassador to the US, Motaz Zahran, and Brownstein Hyatt Farber Schreck. Under their agreement the firm will "provide government relations services and strategic consul on matters before the US government."

"They are clearly worried," said Michele Dunne, director of the Middle East programme at Carnegie.

"When it became clear that Biden would be named the winner, [Sisi] sent his congratulations and now you see all these former foreign ministers and major figures being called out onto the talk shows to reassure the government supporters in Egypt that everything's going to be fine with Biden."

Shortly after Biden was tipped to win, Egypt began releasing political prisoners in what experts said was related to growing calls on the Sisi government to abide by human rights and a predicted change in US policy towards Egypt.

In his now famous reference, Trump referred to Al-Sisi as his "favourite dictator"

In October, 56 US congressmen wrote an open letter to Al-Sisi that stated human rights abuses in Egypt would not be tolerated if Joe Biden won the election and that he would not write Al-Sisi a blank cheque.

Shortly afterwards, 222 MEPs called on Egypt to release its political prisoners.

This is not the first time Egypt has hired firms to boost its image. In 2017 Egyptian intelligence hired two US public relations firms Weber Shandwick and Cassidy & Associates Inc. in Washington to lobby on the country's behalf and improve its image.

The companies would assist Egypt in promoting strategic partnership with the US.

In 2019 Egypt hired an undisclosed US PR firm to counter negative press about the country and improve its image abroad in an attempt to whitewash its severe human rights abuses, rather than put an end to them.

The US sends roughly $1.3 billion worth of annual military aid a year to Egypt though there have been threats that Egypt must abide by human rights to continue to receive the funding. At the beginning of this year, the state department threatened to slash it following the death of an American citizen in jail.

በሞጣ ከተማ አስተዳደር ያረፈችው ሄሊኮፍተር በቴክኒክ ብልሽት በመሆኑ ተገለጠ

#አታወናብዱ_ሞጣ_ሰላም_ነው

በምስራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን በሞጣ ከተማ አስተዳደር ህዳር 06/2013 ዓ.ም ከምሽቱ 12:30 አካባቢ ያረፈችው ሄሊኮፍተር በቴክኒክ ብልሽት በመሆኑ ህዝባችን በመረጋጋት የአካባቢያችንን ሰላም በመጠበቅ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል መልክታችንን እናስተላልፋለን።
የሞጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ፅ/ቤት

#መረጃውን_ሸር_አድርጉ??

The United States has condemned the TPLF's efforts to globalize the conflict in Tigray

ሕወሓት በትግራይ የተፈጠረውን ግጭት ዓለምአቀፍ ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት አሜሪካ አወገዘች 
***************************
 በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚነስትር ቲቦር ናዢ ሕወሓት በኤርትራ ላይ የፈጸመችውን ተቀባይነት የሌላቸው ጥቃቶች አውግዘዋል።

 ይህ በትግራይ የተፈጠረውን ግጭት ዓለም አቀፍ ለማድረግ የሚደረግ ጥረት ነው አሜሪካ አጥብቃ ታወግዘዋለች ብለዋል  ቲቦርናዥ በትዊተር ገፃቸው፡፡ 

ረዳት ሚኒስትሩ ሰላማዊ ሰዎችን እንዲጠበቁ   ውጥረቶች እንዲረግቡና ሰላም እንዲሰፍን  የምናደርገው ጥረት ይቀጥላል ብለዋል።

The United States has condemned the TPLF's efforts to globalize the conflict in Tigray
 ***************************
 The US Assistant Secretary of State for African Affairs, Tibor Nazis, has condemned the TPLF's unacceptable attacks on Eritrea.

 "The United States strongly condemns this attempt to globalize the conflict in Tigray," Tibornaj said on Twitter.

 "We will continue to work for peace and stability in the country," he said.

The Turkish government understands that what Ethiopia is doing is a law enforcement campaign: Turkish Foreign Minister

የቱርክ መንግስት ኢትዮጵያ እየወሰደች ያለችው ተግባር ህግን የማስከበር ዘመቻ እንደሆነ ይረዳል-የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
****************************
ቱርክ ኢትዮጵያ እየወሰደች ያለችው ተግባር ህግን የማስከበር ዘመቻ አድርጋ እንደምትገነዘብ  የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሱግሉ (Mevlut Cavusoglu) አስታወቁ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሱግሉ (Mevlut Cavusoglu) በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን የህግ ማስከበር ሥራ  በሚመለከት በስልክ ተወያይተዋል።

ዘመቻውም በአጭር ጊዜ እንደሚጠናቀቅ እና መንግስት የንጹሃን ዜጎች ደህንነትን እንደሚያስጠብቅ እምነታቸው  መሆኑን የቱርኩ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጽንፈኛው የሕወሓት ቡድን በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ስለፈፀመው ጥቃት እና ዝርፊያ ገለጻ  አድርገውላቸዋል።

የጁንታው ድርጊቱ ወንጀል ብቻ ሳይሆን የሀገር ሉዓላዊነትን መዳፈር እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተው አብራርተዋል። 

ስለሆነም ወንጀለኛውን ቡድን ወደ ፍርድ በማቅረብ በክልሉ የህግ ማስከበር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

The Turkish government understands that what Ethiopia is doing is a law enforcement campaign: Turkish Foreign Minister
 *******************************
 Foreign Minister Mevlut Cavusoglu has said that Turkey recognizes Ethiopia's actions as a law enforcement operation.

 Deputy Prime Minister and Foreign Minister Demeke Mekonnen and Turkish Foreign Minister Mevlut Cavusoglu had a telephone conversation over ongoing law enforcement activities in Tigray State.

 He said the campaign is expected to end soon and that the government will ensure the safety of innocent people.

 Foreign Minister Demeke Mekonnen briefed them on the TPLF's attack on the Northern Command.

 He emphasized that the decision was not a crime but a violation of the sovereignty of the country.

 Foreign Affairs Minister Demeke Mekonnen said law enforcement activities are underway in the region to bring the perpetrators to justice.

አዲስ የድል ዜና ከራያ አላማጣ‼️



"ኢትዮጵያ ትቀጥላለች የከሃዲው ትህነግ ቡድን ይፈርሳል።"የራያ አላማጣ ከተማ ነዋሪዎች

በጀግኖች የመከላከያ ሰራዊታችን የአማራ ልዩ ኃይልና ሌሎች የክልላችን የፀጥታ ኃይሎች በደረሰበት ሽንፈት በዛሬው እለት ከሃዲው የትህነግ ቡድን ራያ አላማጣን ለቆ ፈርጥጧል።

ደስታቸውን ሲገልፁ ያገኘናቸው የራያ አላማጣ ከተማ ነዋሪዎች ለመከላከያ እና ለአማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ አክብሮትና ፍቅራቸውን በወሎ የእንግዳ አቀባበል ስርአታቸው አሳይተዋል።

የዝግጅት ክፍላችን ያነጋገራቸው የራያ አላማጣ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለፁልን ላለፉት በርካታ አመታት የከሃዲው ትህነግ ቡድን ስንሰቃይ እና በገዛ ሀገራችን እንደ ባዕድ ተቆጥረን ስንሳደድ ቆይተናል።

ዛሬ ግን ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊ፣ የአማራ ልዩ ኃይል እንዲሁም በሌሎች የፀጥታ አካላት ነፃ ወጥተናል ኢትዮጵያ ትቀጥላለች የከሃዲው ትህነግ ቡድን ይፈርሳል ብለዋል።

ነዋሪዎቹ ጨምረውም በገዛ መሬታችን እኛን እያፈናቀሉ ከሌላ አካባቢ ለመጡ የትህነግ ቡድኖች መሬታችንን ሲያሳርሱብን ቆይተዋል ሲሉ በምሬት ገልፀዋል።

የመከላከያ እና የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በበኩላቸው ህዝቡ ያደረገልን አቀባበልና ድጋፍ በዘራፊው ትህነግ ምን ያህል ተጨቁነው እንደነበር ያሳያል ብለዋል።

"ጉዟችን ከሃዲው የትህነግ ቡድን እስኪደመሰስ ይቀጥላል‼️"

አማራ ፖሊስ ኮሚሽን

የሕወሓት ጁንታ በመከላከያ ኃይሉ ጀግንነት እና በኢትዮጵያ ሕዝቦች የጋራ ክንድ ጀንበሩ ጠልቃለች-የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሓላፊ

የሕወሓት ጁንታ በመከላከያ ኃይሉ ጀግንነት እና በኢትዮጵያ ሕዝቦች የጋራ ክንድ ጀንበሩ ጠልቃለች-የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሓላፊ
****************************

27 ዓመታትን ፈላጭ ከፋፋይ ሥርዓት ሲከተል የነበረው እና ለኢትዮጵያ ሕዝቦች የመከራ ምንጭ ሆኖ የቆየው የሕወሓት ጁንታ በመከላከያ ኃይሉ ጀግንነት እና በኢትዮጵያ ሕዝቦች የጋራ ክንድ ጀንበሩ የጠለቀችበት መሆኑን የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሓላፊ አቶ ነብዩ ስሁልሚካኤል ገለጹ።

በሕወሓት ውስጥ የሚገኘው ጨካኝ የጁንታ ቡድን ላለፉት 45 ዓመታት የትግራይ ሕዝብን አፍኖ በመግዛት ከልማት እና ከዴሞክራሲ እንዲርቅ ከማድረጉም ባሻገር በኢትዮጵያ ውስጥ ከፋፋይ ሥርዓትን በማንገሥ ሕዝቡ እርስ በራሱ በጥርጣሬ እንዲተያይ አድርጓል ብለዋል ኃላፊው።

ከሁለት ዓመታት በፊት በዚህ ጨቋኝ ቡድን የተማረሩ ኢትዮጵያውያን ባደረጉት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ቡድኑ ከሥልጣኑ ተወግዶ መቀሌ መመሸጉንና  መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከለውጡ ነፃነት እና ዴሞክራሲ ሲጎናጸፍ የትግራይ ሕዝብ ግን አሁንም በጁንታው ቡድን በጨለማ ውስጥ እንዲዳክር እንደተፈረደበት አቶ ነብዩ አመልክተዋል።

ግፍ እና በደል ልምዱ የሆነው ይኸው ጁንታ ቡድን፣ ላለፉት 20 ዓመታት ከትግራይ ሕዝብ ጋር ደስታ እና መከራን በጋራ እንደ አንድ ቤተሰብ ሲያሳልፍ በቆየው የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት በማድረስ ከሀዲነቱን የሚያረጋግጥ በደል ፈጽሟል፣ ይህም በርካታ የትግራይ ሕዝብን እንዳስቆጣው ጠቁመዋል።

ቡድኑ ያሰማራው ልዩ ኃይል ዓላማ ለሌለው ጦርነት ራሳችንን አንማግድም ማለት መጀመሩን ጠቁመው፣ ሚሊሻውም ይህ ጦርነት የጥቂት የሕወሓት ካድሬዎች ጦርነት እንጂ የሕዝብ ጦርነት ባለመሆኑ አንዋጋም በማለት እጃቸውን ለመከላከያ በመስጠት ላይ ይገኛል ብለዋል።

መከላከያ ሠራዊቱም ከትግራይ ሕዝብ ጭምር በሚያገኘው ሕዝባዊ ድጋፍ እየተመራ ጦርነቱን በአጭር ጊዜ ለመቋጨት ወደ አጥፊው ቡድን በመንደርደር ላይ እንደሚገኝ አቶ ነብዩ አብራርተዋል።

ቡድኑ ከዚህ በኋላ እንኳን መንግሥት ሆኖ ሊቀጥል ቀርቶ ቡድን ሆኖ መቀጠል ከማይችልበት የመጨረሻ ደረጃ ላይ መድረሱን አመልክተው፣ በቅርቡም ግብዓተ መሬቱ ይፈጸማል ሲሉ አቶ ነብዩ ተናግረዋል።

የትግራይ ሕዝብ ለውጥ እየፈለገ የኖረ ሕዝብ በመሆኑ መንግሥት ያቋቋመውን አዲሱን አስተዳደር በመደገፍ የጁንታውን መጨረሻ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል ማለታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በዘገባው አመልክቷል።