የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Sunday, January 2, 2022

146 people who were arrested in Benishangul-Gumuz state of emergency are released

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል 146 ግለሰቦች ተፈቱ 
**********

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሀገር ኅልውና ማስከበር ኅብረ-ብሔራዊ ዘመቻ ጋር ተያይዞ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከአሸባሪው ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ 146 ግለሰቦች የተሀድሶ ሥልጠና ተሰጥቷቸው ተለቀዋል። 

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014 መሠረት የሽብርተኛው ህወሓት እና የሽብር ግብረ-አበሮቹ እንቅስቃሴ ደጋፊ እና ፈጻሚ እንደሆኑ የተጠረጠሩ ግለሰቦች ቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል። 

በክልሉ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች ተከባብረው እየኖሩ ባሉበት በዚህ ወቅት የሀገርንም ሆነ የክልሉን ኅልውና አደጋ ውስጥ ለመክተት የሽብርተኛው ህወሓትን እና የግብረአበሮቹን ዕኩይ ዓላማ መሳካት በንፁሃን ዜጎች ላይ እየፈፀሙ ያሉት ግድያ፣ ዝርፍያ እና ሌሎችም ከፍተኛ ጭካኔ የተሞላባቸው ኢ-ሰብአዊ ጥቃቶች እጅግ አደገኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። 

ይህንን ከግምት በማስገባት በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተጠርጥረው የተያዙ ሌሌች ተጠርጣሪዎችም በየደረጃው ጉዳያቸው ተጣርቶ ሰላማዊ መሆናቸው ሲረጋገጥ በቀጣይ እንደሚለቀቁ መገለጹን የክልሉ ማስ ሚዲያ ዘግቧል። 
146 people who were arrested in Benishangul-Gumuz state of emergency are released 
 **********

 In Benishangul Gumuz, 146 individuals arrested in connection with the state of emergency have been rehabilitated and rehabilitated in connection with the state of emergency.

 It is to be recalled that in accordance with the Emergency Proclamation No. 5/2014, individuals suspected of supporting and carrying out the activities of the terrorist TPLF and its terrorist affiliates were arrested.

 At a time when the people of the region are living in dignity, the terrorist, TPLF, and its collaborators' intentions to endanger the very existence of the country and the region have reached alarming proportions.

 With this in mind, other suspects arrested during the state of emergency will be released once their cases are investigated and found to be peaceful, according to regional Mass Media.



የክልሉን አቅም እና የዜጎችን የመልማት ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ የገቢ አሰባሰብ ሥርዓት ሊተለም ይገባል፦ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)

የክልሉን አቅም እና የዜጎችን የመልማት ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ የገቢ አሰባሰብ ሥርዓት ሊተለም ይገባል፦ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) 
************************** 

የክልሉን አቅም እና የዜጎችን የመልማት ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ የገቢ አሰባሰብ ሥርዓት ሊተለም እንደሚገባ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ተናገሩ። 

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የገቢ ንቅናቄ ፍኖተ ካርታ አውደ ጥናት በባህርዳር እየተካሄደ ነው። 

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ክልሉ ባለው አቅም፣ እንቅስቃሴ እና በሚጠበቅበት መጠን ግብር ለመሰብሰብ ተግዳሮቶች እንዳሉ አንስተዋል። 

በመሆኑም ገቢዎች ቢሮ ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በጋራ ያዘጋጁት የግብር አሰባሰብ ፍኖተ ካርታው ይታዩ የነበሩ ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችል እንደሚሆን ተስፋቸውን ገልጸዋል። 

የክልሉ ገቢ ከሕዝቡ ቁጥር፣ ከመልማት አቅም እና በጦርነቱ ከገጠመው ውድመት አኳያ ሊሠራ እንደሚገባም አሳስበዋል። 

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ አማካሪዎች ቡድንም የገቢ አሰባሰብ ችግሮች፣ መፍትሔዎች እና ሊወሰዱ የሚገባቸው እርምጃዎች ላይ ጥናት አቅርበዋል። 

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኝ፣ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት፣ ምሁራን፣ የግብር አምባሳደሮች እና በዘርፉ የሚሠሩ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል። 

በራሔል ፍሬው 


የሲዳማ ክልል ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ሀዋሳ ላይ ምክክር ማካሄድ ጀምረዋል**********************የሲዳማ ክልል የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ሀዋሳ ላይ ምክክር ማካሄድ የጀመሩ ሲሆን በዚህ የምክክር መድረኩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፍ አቶ አብርሃም ማርሻሎን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል። አቶ ደስታ ሌዳሞ በመድረኩ በከሃዲው የሽብር ቡድን የተቃጣብንንና ያለፍላጎት ተገደን ያካሄድነውን ጦርነት ክብሩንና ልዕልናውን ላለማስደፈር በቆረጠው ከመላው የሀገራችን ህዝብና ከጀግናው መከላከያ ኃይላችን ጋር በመቀናጀት የኢትዮጵያን አሸናፊነት አረጋግጠናል፣ድል ተቀዳጅተናል፣የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችንን ቅስም ሰብረናል ብለዋል።ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም አሁን ላይ አንድ በመሆናችን ያገኘነውን ድል በልማቱም አንድ ሆነን የተጎዱ ወገኖቻችንን በመደገፍና የኢኮኖሚያችንን ጉዳት እንዲያገግም የማድረጉ ስራ ትኩረታችንን ከማድረግ ጎን ለጎን የሀገራችንንና የክልላችንን ሰላም ተደራጅተን መጠበቅ ይኖርብናልም ብለዋል። ኢትዮጵያዊያን ነክቶ በቀላሉ መመለስ እንደማይቻልና ኢትዮጵያዊነት ከየትኛውም ጉዳይ በላይ መሆኑን በሁሉም ኢትዮጵያውያን በውጭና በሀገር ውስጥ ህዝባዊ ማእበልና ወኔ ማየት ችለናል፤ ይህም ለኛ ትልቅ ድል ለጠላት ደግሞ ትልቅ ፍርሃትንና ሽንፈትን አከናንቧል ብለዋል።"ለድላችን መገኘት በተናጠል የተደረገ ትግል የለም፤በተናጠል የመጣ ድልም የለም" በማለት የክልሉ ር/መስተዳድሩ ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ አክለውም በመድረኩ አንስተው፤ ድሉም የሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ነው በማለት ገልፀዋል።በሌላ በኩል የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ በበኩላቸው በጠላት የተነካውና የተደፈረው ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ህዝብ በመሆኑ ምክንያት ከዳር እስከ ዳር ተደራጅቶ፣ ተደጋግፎና ተጠናክሮ የፊትና የኃላ ደጀን በመሆን በግንባር በአካል ከጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ጎን አብሮ እስከመቆም ታሪክ የማይረሳውን ደጀንነቱን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ አረጋግጧል ብለዋል።ኃላፊው አክለውም እንደገለፁት ድሉን ከነባራዊ እውኔታና ሃቅ ውጭ መጠምዘዝም ማድረግም የማይቻልና ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ህዝብና ህዝብ ብቻ መሆኑንና አሸናፊዋም ኢትዮጵያ መሆኑን ጨምረው አንስተዋል።በመሆኑም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮቻችን ከድህረ ጦርነት በኋላ ሊፈጠሩ የሚችሉ ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን በሚገባ ተገንዝቦ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣ ለማድረግ መድረኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።በመጨረሻም በዚህ ለሶስት ቀናት በሚቆየው መድረክ አመራሩ በጉዳዩ ላይ ከሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ መነሻ በድህረ ጦርነትና ከዚያ በኃላ ባለው ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ የፀጥታና የሰብአዊ ጉዳዮች ሁኔታዎች ላይ በቀረበው ሰነድ ላይ ሰፍ ውይይትና ምክክር ካደረገ በኃላ ይህንን ተግባር ከነባራዊ ሁኔታ ጋር በማመጋገብ በብቃት ለመምራት የማስቻል በሚቀመጡ የጋራ አቅጣጫዎች ላይ በመግባባት ምክክሩ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉhttps://www.youtube.com/c/EBCworld/ በምስል የሚገኙ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የኢንስታግራም ገፃችንን ይከተሉ https://www.instagram.com/ebcnews1/አጫጭርና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ https://twitter.com/ebczena ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉhttps://t.me/EBCNEWSNOW

የሲዳማ ክልል ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ሀዋሳ ላይ ምክክር ማካሄድ ጀምረዋል
**********************

የሲዳማ ክልል የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ሀዋሳ ላይ ምክክር  ማካሄድ  የጀመሩ ሲሆን በዚህ የምክክር መድረኩ ላይ  የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፍ አቶ አብርሃም ማርሻሎን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።
 
አቶ ደስታ ሌዳሞ በመድረኩ በከሃዲው የሽብር ቡድን የተቃጣብንንና ያለፍላጎት ተገደን ያካሄድነውን ጦርነት ክብሩንና ልዕልናውን ላለማስደፈር በቆረጠው ከመላው የሀገራችን ህዝብና ከጀግናው መከላከያ ኃይላችን ጋር በመቀናጀት የኢትዮጵያን አሸናፊነት አረጋግጠናል፣ድል ተቀዳጅተናል፣የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችንን ቅስም ሰብረናል ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም አሁን ላይ አንድ በመሆናችን ያገኘነውን ድል በልማቱም አንድ ሆነን የተጎዱ ወገኖቻችንን በመደገፍና የኢኮኖሚያችንን ጉዳት እንዲያገግም የማድረጉ ስራ ትኩረታችንን ከማድረግ ጎን ለጎን የሀገራችንንና የክልላችንን ሰላም ተደራጅተን መጠበቅ ይኖርብናልም ብለዋል። 

ኢትዮጵያዊያን ነክቶ በቀላሉ መመለስ እንደማይቻልና ኢትዮጵያዊነት ከየትኛውም ጉዳይ በላይ መሆኑን በሁሉም ኢትዮጵያውያን በውጭና በሀገር ውስጥ ህዝባዊ ማእበልና ወኔ ማየት ችለናል፤ ይህም ለኛ ትልቅ ድል ለጠላት ደግሞ ትልቅ ፍርሃትንና ሽንፈትን አከናንቧል ብለዋል።

"ለድላችን መገኘት በተናጠል የተደረገ ትግል የለም፤በተናጠል የመጣ ድልም የለም" በማለት የክልሉ ር/መስተዳድሩ ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ አክለውም በመድረኩ አንስተው፤ ድሉም የሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ነው በማለት ገልፀዋል።

በሌላ በኩል የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ በበኩላቸው በጠላት የተነካውና የተደፈረው ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ህዝብ በመሆኑ ምክንያት ከዳር እስከ ዳር ተደራጅቶ፣ ተደጋግፎና ተጠናክሮ የፊትና የኃላ ደጀን በመሆን በግንባር በአካል ከጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ጎን አብሮ እስከመቆም ታሪክ የማይረሳውን ደጀንነቱን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ አረጋግጧል ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም እንደገለፁት ድሉን ከነባራዊ እውኔታና ሃቅ ውጭ መጠምዘዝም ማድረግም የማይቻልና ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ህዝብና ህዝብ ብቻ መሆኑንና አሸናፊዋም ኢትዮጵያ መሆኑን ጨምረው አንስተዋል።

በመሆኑም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮቻችን ከድህረ ጦርነት በኋላ ሊፈጠሩ የሚችሉ ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን በሚገባ ተገንዝቦ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣ ለማድረግ መድረኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

በመጨረሻም በዚህ ለሶስት ቀናት በሚቆየው መድረክ አመራሩ በጉዳዩ ላይ ከሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ መነሻ በድህረ ጦርነትና ከዚያ በኃላ ባለው ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ የፀጥታና የሰብአዊ ጉዳዮች ሁኔታዎች ላይ በቀረበው ሰነድ ላይ ሰፍ ውይይትና ምክክር ካደረገ በኃላ ይህንን ተግባር ከነባራዊ ሁኔታ ጋር በማመጋገብ በብቃት ለመምራት የማስቻል በሚቀመጡ የጋራ አቅጣጫዎች ላይ በመግባባት ምክክሩ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

የባህርዳር ሀገረ ስብከት መጭውን የልደት(የገና) በዓልን ምክንያት በማድረግ የትግራይ ወራሪ ቡድን ባደረሰው ጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች ማቋቋሚያ የሚውል የ4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

የባህርዳር ሀገረ ስብከት መጭውን የልደት(የገና) በዓልን ምክንያት በማድረግ የትግራይ ወራሪ ቡድን ባደረሰው ጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች ማቋቋሚያ የሚውል የ4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።
*****
የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ዻዻስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፅዕ አቡነ አብርሃም እንደገለፁት ሰው በችግር ጊዜ መረዳዳት በጨነቀ ጊዜ ማጽናናት ከእግዚአብሔር የተሰጠን ፀጋ በመሆኑ በሀገረ ስብከቱ ስር ያሉ 40 የሚሆኑ ገዳማትና አድባራት ከነ አገልጋዮች በማስተባበር ካሁን በፊት ሲያደርግ ከቆየው ድጋፍ በተጨማሪ ከሀገረ ስብከት እስከ ታችኛው አጥቢያ ቤተክርስቲያን ድረስ የሚገኙ ምዕመናንና ምዕመናትን የተሳተፉበት ድጋፍ መሆኑን ተናግረዋል።

ቤተ ክርስቲያኗ ከጸሎት ባለፈ ለተራቡ፣ለተጠሙና ለተራዙ ወገኖቻችን መድረስ፣ ለፈረሱ የትምህርት፣ የጤና እና የኃይማኖት ተቋማት እንዲሁም የግለሰብና የመንግስት ቤቶችን መልሶ መጠገን ተገቢ በመሆኑ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

ብፅዕነታቸው አያይዘውም ሰው ለሰው መዳህኒት መሆኑን ወደ ጎን በመተው አጥፊ ከሚሆን ይልቅ የሚጠቅመው ክፉውን ጊዜ ተደጋግፎና ተከባብሮ በማሳለፍ እና ክፍውን በጋራ ሀይ በማለት ለጋራ ከሰላምና ልማት በጋራ መቆም እንደሚገባ አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ በበኩላቸው በብፅዕ አቡነ አብርሃም የሚመራው የባህርዳር ሀገረ ስብከት ከዚህ በፊት የህልውና ዘመቻው ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ ህዝቡን በጸሎት ከመጠበቅ ባሻገር እየተደረገ ያለው የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ ከሚጠበቀው በላይ መሆኑን አስታውሰዋል።

በዛሬው ዕለትም መንፈሳዊና የቁሳዊ እንዲሁም ስነ ልቦናዊ ጉዳት ለደረሰባቸውና በከፍተኛ ችግር ውስጥ ለሚገኙ የጦርነት ቀጠና ሆነው ለቆዮ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋሚያ የሚውል የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ 4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በማድረጋቸው በባህርዳር ከተማ ህዝብና መንግስት ስም የከበረ ምስጋና ያላቸው መሆኑን ገልፀዋል።

በመሆኑም ከተማ አስተዳደሩ በሚያከናውናቸው የህዝብ ልማትና ሰላም ግንባታ ተግባራት ላይ ሀገረ ስብከቱ ከጎናቸው እንደማይለይና የተጀመረውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያላቸውን የፀና እምነት ገልፀዋል ።

መረጃው የባህርዳር ከተማ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ነው።

የዛሬው አዲስ ዘመን ጋዜጣ

የአፄ ቴዎድሮስ ሹሩባ (ቁንዳላ) የሽኝት መርሐ-ግብር ተካሄደ

የአፄ ቴዎድሮስ ሹሩባ (ቁንዳላ) የሽኝት መርሐ-ግብር ተካሄደ 
******************** 

የአፄ ቴዎድሮስ ሹሩባ (ቁንዳላ) ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር የሽኝት መርሐ-ግብር ተካሂዷል። 

ሽኝቱ ከብሔራዊ ሙዚየም ተነስቶ ወደ 4 ኪሎ አደባባይ እንደሚደረግ ተገልጿል። 
 
በሽኝት መርሐ-ግብሩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ጨምሮ አባት አርበኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ አርቲስቶች እና ሌሎች ተገኝተዋል። 

የአፄ ቴዎድሮስ የሹሩባ (ቁንዳላ) በጎንደር ከተማ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግለት ከጎንደር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
Emperor Tewodros Shuruba's Ceremony  was held
 ********************

 Emperor Tewodros Shuruba (Qundala) was flown from Addis Ababa to Gondar.

 It will be held at the 4 Kilo Square from the National Museum.

 Patriots, invited government officials, celebrities, artists and others were present at the event.

 According to Gondar Communication, Emperor Tewodros Shuruuba (Qundala) will be given a warm welcome in Gondar.

The TPLF has looted more than 1.5 billion birr worth of property in North Shoa, according to a study

አሸባሪው ሕወሓት በሰሜን ሸዋ ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መዝረፉን ጥናት አመለከተ

አሸባሪው ሕወሓት በሰሜን ሸዋ በወረራ ይዞቸው በነበሩ አካባቢዎች አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የግለሰቦች ቤት ቁሳቁስና ዕቃዎች ዝርፊያና ውድመት ማድረሱን የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ባደረገው ጥናት ማረጋገጡን አስታወቀ።

በዩኒቨርሲቲው የጥራትና ምርምር ተባባሪ ዲን ዶክተር አራጋው አለማየሁ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ አሸባሪ ቡድኑ ህብረተሰቡ በቤት ውስጥ የሚገለገልባቸውን ከአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ እንደ ማንኪያ፣ ትሪ፣ ፍራሽ፣ ፍሪጅ፣ ቴሊቭዥኖችና የመሳሰሉትን ቁሳቁሶች በመዝረፍና በማውደም ኪሳራ አድርሷል።

የሽብር ቡድኑ በተለያዩ የሕዝብ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ዝርፊያና ውድመት መፈጸሙን አውስተው፤ቡድኑ የአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ዝርፊያና ውድመት ያስከተለው በግለሰቦች የቤት ቁሳቁስ ላይ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል። 

ይህም የአማራን ሕዝብ የከፋ ድህነት ውስጥ ለመክተት አስቦና አልሞ ያደረገው መሆኑን ገልጸዋል።

በሰሜን ሸዋ በትምህርት ተቋማት ላይም አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን የጠቆሙት ዶክተር አራጋው፤ አጣዬ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት ላይ ብቻ ከ54 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል ሲሉ ተናግረዋል።

እንደ ዶክተር አራጋው ገለጻ፤ በሸዋሮቢት ከተማ 11 ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር ፣በቀወት ወረዳ 11 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ብር፣ በጣርማ በር አራት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ብር፣ በሞላሌ 25 ነጥብ አምስት ሚሊዮን እንዲሁም በመንዝ ጌራ 25 ነጥብ አራት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ላይ ውድመትና ዘረፋ ተፈጽሟል።

እንደ ዶክተር አራጋው ከሆነ፤ አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በዞኑ በሚገኙ የተለያዩ ባንኮች ላይ ውድመት አድርሷል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ብቻ በኤቴኤም ማሽን፣ ኮምፒውተርና መስኮቶች ላይ ያደረሰው ውድመት 30 ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር በላይ ይገመታል።

በአምስት ሆስፒታሎች በእያንዳንዳቸው ላይ 31 ሚሊዮን ብር በላይ ውድመትና ዘረፋ ማድረሱን የጠቆሙት ዶክተር አራጋው፤ ውድመቱ 155 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት መሆኑንም ገልፀዋል።

የዩኒቨርሲቲው ጥናት ሙሉ ሰሜን ሸዋን እንዳካተተ የጠቆሙት ዶክተር አራጋው፣ አምስት ከተማ አስተዳደሮችንና ስምንት ወረዳዎች ላይ የሽብር ቡድኑ ያደረሳቸውን ውድመቶች መሸፈኑንም ገልፀዋል።

በጠቅላላ በሰሜን ሸዋ ዞን በሁሉም ዘርፍ የደረሰው የንብረት ውድመት ጥናቱ ሲጠናቀቅ ይፋ እንደሚሆንም የዩኒቨርሲቲው የጥራትና ምርምር ተባባሪ ዲን ዶክተር አራጋው ጠቁመዋል።
The TPLF has looted more than 1.5 billion birr worth of property in North Shoa, according to a study

 According to a study conducted by Debre Berhan University, the terrorist group TPLF has looted and destroyed more than 1.5 billion birr worth of personal belongings in North Shoa.

 Dr. Aragaw Alemayehu, Dean of Quality and Research at the University, told the Ethiopian Press Agency:  The terrorist group looted and destroyed more than 1.5 billion birr worth of household items such as spoons, trays, mattresses, refrigerators, televisions, and so on.

 He recalled that the terrorist group had looted and destroyed several public institutions, adding that the group had looted and destroyed more than 1.5 billion birr in personal belongings.

 He said this was done with the intention of impoverishing the people of Amhara.

 Dr. Aragaw pointed out that the terrorist group TPLF has inflicted heavy casualties on educational institutions in North Shoa.  He said more than 54 million birr worth of property was destroyed at Ataye Technical and Vocational School alone.

 According to Dr. Aragaw:  More than 11.9 million birr worth of property was destroyed in Shewarobit town, 11.7 million birr in Kewet woreda, 4.7 million birr in Tarmaber, 25.5 million birr in Molale and 25.4 million birr in Menz Gera.

 According to Dr. Aragaw:  The terrorist group TPLF has destroyed several banks in the zone.  The damage to the Commercial Bank of Ethiopia alone is estimated at over 30.5 million birr.

 According to Dr. Aragaw, more than 31 million birr was destroyed and looted in five hospitals each.  He said the damage is estimated at over 155 million birr.

 Dr. Aragaw said the university study covered the entire North Shoa, adding that it covered the damage caused by the terrorist group to five city administrations and eight woredas.

 According to Dr. Aragaw, Dean of Quality and Research at the University, the damage to property in all sectors of North Shoa Zone will be announced upon completion.


Diaspora event in Meskel Square with photo

ዳያስፖራዎች የተሳተፉበት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በመስቀል አደባባይ በፎቶ 

Diaspora event in Meskel Square with photo

Attaye Hospital has begun normal operation

የአጣዬ ሆስፒታል ስራ መጀመሩ ተገለፀ
 
እንደሚታወቀው በሰሜን ሸዋ የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በጦርነቱ ሙሉ በሙሉ ውድመት ደርሶበት ስራ ማቆሙ ይታወቃል።ይህን ተከትሎ የአጣዬ ሆስፒታልን ስራ ለማስጀመርና መልሶ ለማቋቋም የወራቤ ኮም/ስፔ/ሆስፒታል ሃላፊነት በመውሰድ የህክምና ቡድን በማደራጀት እንዲሁም ለድንገተኛ ፤ለእናቶችና ህጻናት አገልግሎት የሚያስፈልጉ የህክምና መሳሪያ, መድሃኒትና ሌሎች ዕቃዎችን በመያዝ ከሳምንት በፊት መንቀሳቀሳቸው ይታወቃል።ቡድኑ አጣዬ ሆስፒታል በመድረስ የያዙትን ግብዓት በማስረከብ ከአጣዬ ሆስፒታል ማኔጅመንት ጋር በመሆን ሁሉንም አገ/ት መስጫ ክፍሎችን በመዞር ችግሮችን በዝርዝር በመለየት የሙያና የስነልቦና ድጋፍ በማድረግ ታላቅ ሃላፊነት በመወጣት አገ/ት በማስጀመር ተመልሰዋል።ቡድኑ እንደተመለሱም  ለሆስፒታሉ ማኔጅመንት የተለዩ ዝርዝር ጉዳዮችን በማቅረብ በአጭርና በረጅም ጊዜ የሚፈቱትን በመለየት አቅርቧል።በተለዩ ችግሮች መሰረት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በመለየት ለሁለተኛ ዙር የተለያዩ የህክምና መሰሪያዎችን፤መድኃኒቶችን በመያዝ ወደ አጣዬ ሆስፒታል በመዉሰድ በአሁኑ ሰዓት የተመላላሽ፤ድንገተኛ ፤ተኝቶ ህክምና፤ላብራቶሪ ፤ፋርማሲ አገልግሎት መጀመሩን የአጣዬ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ አራጋው የገለፁ ሲሆን ለተደረገላቸው ድጋፍ እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን በመግለፅ የወራቤ ኮም/ስፔ/ሆስፒታል የማይተካ ወንድማማችነት ስላሳየን ከፍ ያለ ምስጋና አቅርቧል።ይህ ድጋፍ የአጣዬ ሆስፒታል ሙሉ አገልግሎት እስኪጀምር ድረስ የወራቤ ኮም/ስፔ/ሆስፒታል ድጋፉን እንደሚቀጥል የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል ሽፋ የገለፁ ሲሆን የህክምና ቡድኑ ላደረገው ድጋፍም  ምስጋና አቅርቧል።

It is announced that the work of Attaye Hospital has begun

 It is known that Attaye Primary Hospital in North Shoa was completely destroyed during the war.  The team arrived at Ataye Hospital and handed over their resources to Ataye Hospital Management.  Ato Aragaw, General Manager of Attaye Hospital, said that the outpatient, emergency, inpatient, laboratory and pharmaceutical service has just started.  He thanked the hospital for its unwavering brotherhood.

Saturday, January 1, 2022

24 suspects arrested in Addis Ababa for robbing foreigners

ታህሳስ 23፣ 2014

በአዲስ አበባ በቡድን ተደራጅተው የውጭ አገር ዜጎች ላይ ዝርፊያ ሲፈፅሙ የነበሩ 24 ተጠርጣሪዎች ተያዙ፡፡ 

የዘራፊዎች ዓላማ ኢትዮጵያ ሰላም እንደሌላት በማስመሰል ከሌሎች ሀገሮች ጋር ለማቃረን ነው ሲል ፖሊስ ተናግሯል፡፡ 

ንጋቱ ሙሉ

January 01, 2014

 24 suspects arrested in Addis Ababa for robbing foreigners

 "The purpose of the thugs is to disguise Ethiopia as a country without peace," he said.

 The whole morning




This year's Christmas will be celebrated nationally in Lalibela, according to the Ethiopian Ministry of Tourism.



የገና በዓል በብሔራዊ ደረጃ በላልይበላ ይከበራል -የቱሪዝም ሚኒስቴር
***********************

 የዘንድሮዉ የገና በዓል በልዩ ድምቀት በብሄራዊ ደረጃ በላልይበላ ከተማ እንደሚከበር የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በዓሉን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ከአማራ ክልል መንግስት፣ ከአማራ ክልል ቱሪዝም ቢሮ እና ከደብረ ሮሃ ቅ/ላልይበላ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት ዝግጅቱን ማጠናቀቁንሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል ፡፡

በላልይበላ ከተማ የሚከበረዉ የገና በዓል እንደሀገር በኮረና ወረርሽንና በፀጥታ ችግር ተቀዛቅዞ የነበረዉን የቱሪዝም ዘርፍ ልማት እንቅስቃሴ እንደሚያነቃቃው ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

በክብረበዓሉ ላይ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የሀገሪቱን ጥሪ ተቀብለው የመጡ የዳያስፖራ አባላት፣ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና የመገናኛ ብዙሃን ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/ 
ገና Christmas is celebrated nationally in Lalibela - Ministry of Tourism
 ***********************

 This year's Christmas will be celebrated nationally in Lalibela, according to the Ministry of Tourism.

 The ministry has completed the preparations in collaboration with the Amhara Regional State Government, the Amhara Regional State Tourism Bureau and the Debre Roha St. Lalibela Administration to celebrate the occasion, Prime Minister Ambassador Nassie Chali said in a press statement.

 She said the Christmas celebration in Lalibela will revive the tourism sector, which has been stagnant due to the epidemic and insecurity in the country.

 The event is expected to be attended by senior federal and state government officials, His Holiness the Pope, members of the Diaspora who have accepted the invitation, and influential individuals and the media.

 Subscribe to our official YouTube channel for our video information
 https://www.youtube.com/c/EBCworld/


Prime Minister Abiy Ahmed has sent a message of congratulations on the New Year 2022

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የ2022 አዲስ ዓመትን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
**********************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ የገባውን የ2022 የጎርጎሳውያን አዲስ ዓመት በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

"በዓለም ዙሪያ ለምትኖሩ ወዳጆቻችን እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንኳን 2022 አዲስ ዓመት አደረሳችሁ" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት።

Prime Minister Abiy Ahmed has sent a message of congratulations on the New Year 2022
 **********************

 Prime Minister Abiy Ahmed has sent a message of congratulations on the 2022 Gregorian New Year.

 "Happy New Year 2022 to our friends around the world and to all Ethiopians and people of Ethiopian descent," the prime minister said in a message posted on his social media page.


More than 42 million birr assistance has been provided to IDPs in Afar State

በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ42 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ  ድጋፍ ተደረገ
**********************
በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ42 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የእለት ደራሽ ድጋፍ ተደረገ፡፡
በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አስተባባሪነት የሰዎች ለሰዎች ድርጅት 40 ሚሊዮን ብር እንዲሁም አፍሪካን ቻይልድ ፖሊሲ ፎረም 2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አድርገዋል።

ድጋፉ በክልሉ የሚገኙ ከ40 ሺህ በላይ ተፈናቃዮችን ለአንድ ወር ተጠቃሚ የሚያደርግ እንደሆነ ተገልጿል።

የሰዎች ለሰዎች ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ አቶ ይልማ ታዬ ድጋፉን ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተወካይ አቶ አሊ ሁሴን አስረክበዋል፡፡

አቶ ይልማ በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት ድርጅቱ ተደራሽ በሆኑ አካባቢዎች ሁሉ የእለት ደራሽ ድጋፍና የመልሶ ማቋቋም ስራዎቹን አጠናክሮ ይቀጥላል።

የድርጅቱ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ በበኩሉ እንዳለው፤ ድርጅቱ በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች ያደረገው ድጋፍ ለወገን አለኝታነቱን ያሳየ ነው ብሏል፡፡

ተፈናቃዮችን መደገፍ የሁሉም ህብረተሰብ ኃላፊነት እንደሆነም አትሌቱ ገልጿል።

በአሊ ሚራ
More than 42 million birr assistance has been provided to IDPs in Afar State
 **********************
 More than 42 million birr daily assistance was provided to IDPs in Afar State.

 Under the coordination of the Civil Society Organizations Authority, the people donated 40 million birr and the African Child Policy Forum donated over 2 million birr.

 The aid will benefit more than 40,000 IDPs in the region for one month.

 Yilma Taye, Ethiopian Representative to the People's Organization for Human Rights, handed over the support to Ali Hussein, Deputy Chief of the Regional State.

 During the handover, Yilma said the organization will continue to strengthen its day-to-day support and rehabilitation activities in all accessible areas.

 Athlete Major Haile Gebreselassie, the organization's volunteer ambassador, said:  He said the organization's support for the displaced in the Afar region is a testament to its resilience.

 "Supporting the displaced is the responsibility of the whole community," he said.

 By Ali Mira



Curated Products for Generation X

https://amzn.to/3VhbwJz GenX Essentials - Curated Products for Generation X ...

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon