Tuesday, March 11, 2014

ቋንቋ ይወለዳል፣ ያድጋል ፣ ይሞታል ነው አሉ አማርኛ ግን ተበረዘ

ቋንቋ ይወለዳል፣ ያድጋል ፣ ይሞታል ነው አሉ አማርኛ ግን ተበረዘ
ስለ ሌሎች  የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እንዴት እንደሆነ አላውቅም አማርኛ ግን በቃ ጠጅ መሆኑ ቀርቶ ብርዝ ሆኗል። የእንግሊዘኛ ቃላቶች ከነ ቁማቸው መግባታቸው ብቻ ሳይሆን  ካለ ቦታቸው መግባታቸው ነው። አንዳንዴ ሰው ፊት አማርኛ ሚስጢር ማውራት በምንም አይቻልም። እስኪ ለአብነት ያክል ይህን አባባል አንብቡትና ስንት እንግሊዝኛ ቃላት እንደተጠቅምሁ አስቡት።
ሬድ ይት ላይ ስቶፕ ሳላድርግ አልፌ ፖሊሱ ትኬት ሰጠኝ።
 እስኪ ይህንን በአማርኛ ልጻፍው።
ቀዩ መብራት ላይ ሳልቆም ስላለፍሁ ቅጣት አገኘሁ።
 በሌላም አርፍተ ነገር መጻፍ እንችለን።  ይህ ለአብንት ያክል ነው። ሌላው የአማርኛ መበላሽት እራሱ በራሱ ነው (self destruction)። ለምሳሌ ተመችኝ (comfort) ይምቻል,  ተመቸችኝ የሚሉት ቃላቶች የሚያገልግሉ ለእቃዎች  ለምሳሌ ለሶፋ ወንብር፣ ለአልጋ ወይም ለባርጩሜ ነው። እከሌ ተመችኝ፣ ሙዚቃው ይምቻል። ከእንግሊዘኛ ቃል መጣ  እንዳይባል ራሱ በእንግሊዝኛ ምቾት (comfort)  የሚያያዘው ከአካላዊ ምቾት ጋር ነው ለውስጣዊ ስሜት (ምቾት) ግን አይሆንም። ቢሆንም አገባቡ ለየት ያለ ነው። ታዲያ የዘመኑ አማርኛ ሲያጌጡ ይመለጡ ነው። ወዲያ..

የድሮ የኢትዮጵያ እረኛ ታሪክ ሰሪ ነበር ያሁኑስ?

የድሮ የኢትዮጵያ እረኛ ታሪክ ሰሪ, ነበር ያሁኑስ?
እውነት ይሁን ውሽት አናውቅም ቡናን ያገኘው ካሊድ እረኛ ነው አሉ። አይገርምም???? ካሊድ ያገኘው ነገር ስንቱን ቢሊዮነር አደርገው::  የዘመኑ እረኛስ? ለዚያውስ የሚጠበቅ በግና የሚጠበቅበት ሜዳ ካል አይደል። እስኪ አንዴ ቆም ብላችሁ አስቡ። እኛ የዚህ ዘመን ሰውች ስራችን በቃ ከዚህ በፊት የተፈጠሩትን መጠቀም ብቻ ነው። ለምሳሌ ቡናን ካሊድ አግኘው ጤፍንስ ማነው? መጀምሪያ እንጀራ የጋገረችው? ማንው ሽሮ ወጥን የፈጠርው? ጠጅንስ? ጠላ ከሄት ምጣ? አይገርምም። ዳቦስ? ማንች የመጀምሪያዋ ዶሮ ወጥ ሰሪ? የአረቂ ነገርማ በጣም የሚገርም ነው። ታዲያ አይገርምም እኛ ያለፈው ትውልድ ብቸኛ ተጥቃሚዎች ስንሆን ለሚቀጥለው ትውልድ የምናዎርስው ምንም ጥሩ ነገር የለነም። ቆይ፣ ቆየ እረ አለን ብዙ የምናውርስው። ለምሳሌ ዘረኝነት፣ ሸር፣ ምቀኝነት፣ ተንኮል፣ ጉቦ፣ አድሎ፣ ሌላም ሌላም...

የዲይስፖራ ትርጉም ቅጥ አጣ።

የዲይስፖራ ትርጉም ቅጥ አጣ። በብዛት የሃገራችን የቋንቋ ትርጉም በባለሙያዎች የተመረኮዘ ሳይሆን አንድ ተዋቂ ሰው ቴሌቭዥን ላይ ወይም ራዲዮ ወይም ጋዜጣ ሊሆን ይችላል  ያንን ቃል ከተናገረ ወይም ከተናገረች ያ ቃል ትክክል ነው ብለን መደገም መደጋገም ነው። ለዚሁም ትልቁ ምሳሌ ዲያስፖራ ነው። ይህ ቃል የተሰጠው ሳይወዱ በግዳቸው ከሃገራቸው፣ ከቤት  ከቀያቸው በስደት በስው አገር ይኖሩ ለነበሩ እስራልያውያን (Jew) የተስጠ መጠሪያ ነበር። እዚህ ላይ ዋናውና ትልቁ ቃል " ሳይወዱ ብግዴታ" የሚለው ቃል ነው። ታዲያ ያ ቃል ለሁሉም በውጭ አገር ለሚኖር ኢትዮጵያዊ አያገለግለም። ለምሳሌ ለትምህረት፣ በዲቪ፣ ለጉብኝት፣ ለስራ፣ በልጆች ወይም በወላጆች የመኖሪያ ፍቃድ አግኝተው ከሃገር ፀሃይ ሞቋቸው ሰው አይቷቸው በቦሌ ሰተት ብለው የወጡት ዲያስፖራ አይደሉም። ታዲያ ማንው ዲያስፖራ? Well  እራሳችሁን ጠይቁ...


አዲስ አበባ ላይ አበባ የሚበቅልበት ቦታ ሊጠፋ ነው

አዲስ አበባ ላይ አበባ የሚበቅልበት ቦታ ሊጠፋ ነው
 እረ ምነው ነው የሚያሰኘው። አዲስ አበባ ምነው መናፍሻ፣ ባዶ ቦታ፣ ኳስ መጫወቻፓርክ የሚባሉ ነገሮች ከፕላኑ ውስጥ ጠፉ።  እረ ይታሰብበት። ትንሽ ቆይቶ አበባ የሚታየው ባለ አበባ ቀሚስ ብቻ ላይ እንዳይሆን

ጤፍን ያዩበት አይናቸው ውስጥ የጤፍ እብቅ ይግባበት (Amen)

ጤፍን ያዩበት አይናቸው ውስጥ የጤፍ እብቅ  ይግባበት
እኔ ሳድግ ጤፍ የሚሸጠው በሰሃን ተሰፍሮ  ነበር። ከገሬው ላይ። ከዚያ ጤፍ ነጋዴ መጣ,  በኪሎ የሚቸበችብ። ከዚያ ደርቅ እንጀራ መሸጥ ጀመረ፣ ከዚያ ጤፍ ከሌላ ዱቄት ጋር ተደባልቆ ጤፍ እንጀራ ተብሎ መሸጥ ጀመረ:: እንጀራ ሆነ። እንጀራ  በሸክላ ምጣድ ሳይሆን በኤሌክትሪክ መጋገር ጀመር:: ሰፋቱም አነስ::ውፍረቱም ቀነስ:: ከሳ መነመነ:: ከዚያ አሜሪካ ምድር ገባ :: በቃ እንጀራ ቅጡን አጣ፣ አይኑ ጠፋ፣ መልኩ ጠፋ፣ቅርጹ ጠፋ በቃ እንጀራ እንጀራ መሆኑ ማጠራጠር ጀመረ። ከዚያ ጤፍን አይን በላው። የፈርንጅ አይን አየው። ብለው ብለው ታላቁ ምግብ ሱፐር  ፉድ (super food)  እያሉ ይጠሩት ጀመር። ምን ያማ ጤፍ ቡና ሊሆን ነዋ። ያኔ በሰሃን ስንዝቀው የነበረው ጤፍ ዛሬ እንደ ወንጂ ስኳር በላስቲክ እየታሸገ ሊሽጥ ግን የወንጂ ስኳር ምን ነበር? ያንን በሌላ ጊዜ አሁን ግን ስለ ጤፍ። ከሁሉ ያሳሰበኝ ጤፍ ከቻይና እንዳይመጣ ነው። ምንው ፈረንጅ ሌላ ስራ አጣ? ምነው ጤፍን አዩብን? ለሁሉም ጤፍን ያዩበት አይናቸው ውስጥ የጤፍ እብቅ ይግባብት (Amen)

MPORTANT NOTICE TO ALL VISA APPLICANTS CONCERNING VACCINATION REQUIREMENTS

Recent changes to the United States immigration law now require immigrant visa
applicants to obtain certain vaccination (listed below) prior to the issuance of immigrant
visa. Panel physicians who conduct medical examination of im
migrant visa applicants
are now required to verify that immigrant visa applicants have met the new vaccination
requirement, or that is medically inappropriate for the visa application to receive one or
more of the listed vaccinations.
Mumps
Influenza type b(Hib) and, Measles, Hepatitis B
Rubella
Variecella
Polio
Pneumococcal
Tetanus and diphtheria toxoids Influenza
Pertussis
In order to assist the panel physician, and to avoid delays in the processing of an
immigrant visa, all immigrant visa applicants should have their vaccination
records available for the panel physician’s review at the time of the immigrant medical
examination. Visa applicants should consult with their regular hea
lth care provider to obtain a copy of their immunization record, if one is available. If you do not have a
vaccination record, the panel physician will work with you to determine which vaccination you may need to meet the requirement. Certain waivers of the vaccination
requirement are available upon the recommendation of the panel physician

Physicians in Ethiopia authorized to give medical examinations for U.S. Visa applications are

Physicians in Ethiopia authorized to give medical examinations for U.S. Visa
applications are:
Dr. Akeza Teame
Dr. Kinetsew Melkamu (Pediatr
ician)
Dr. Selamawit Asmelash (Pediatrician)
Dr. Betelhem Gebremichael
St. Yared General Hospital
Bole Sub City, Kebele 12/13
On the road to CMC, 800 meters from Megenagna square
Tel: 011 645 4604, 011 645 4653
Fax: +251 11 6454706
Dr. Akeza
Teame (Internist and Infection Specialist)
Dr. Kaleab Tesfaye (Pediatrician)
American Medical Centre (AMC)
Yeka Sub City Kebele 20/21
Inside the Sunshine Real Estate Compound (Meri Luke)
Tel. +251-116678000/04/ 07
Dr. Ikovac Szlapak Lovorka
Dr. Simret Kelile
Dr. Fitsum Shiferaw
Dr. Wondwossen Arega
Dr. Niyat Tadesse
Dr. Ramisetty Rama
INTERNATIONAL OFFICE
FOR MIGRATION (IOM)
Bole Kefle Ketema, Kebele 02
Behind Bole DH Geda