እውነትም የፈረስ ጉልበት
Thursday, April 17, 2014
Wednesday, April 16, 2014
ኢትዮጵያ እንደ ህንድ ብትሆን ፋሲካ ምን ይመስል ነበር?
ህንድ አገር አሉ፣ "አሉ" ነው ሰው የከብት ስጋ ስለማይበላ በሬና ላም ጋሪ ይጎትታሉ, ከዚያ አርጅተው መሞት ብቻ ነው። ይህ አገራችን ውስጥ ቢሆን ምን ይፈጠራል? አታድርስ ነው እንጂ እውን ቢሆን ክትፎ፣ ዱለት፣ ጥብስ፣ ጎረድ ጎረድ፣ ስጋ ወጥ ሁሉም ባይ ባይ ይሉና አቶ ሽሮ ብቻ አለቃ ይሆን ነበር። ፋሲካም በቃ ምን ይመስል ይሆን:
ግን እርስዎ ይስማማሉ? ብታምኑም ባታምኑም ጥቅሙ ያመዝናል። ለኪስም ለጤንነትም ጥሩ ነበር ፣ በተለይ ደግሞ አሁን በሬው በማዳበሪያ እያደገ ሰውን በሽታ ላይ ነው የጣለው አሉ::
ሱዳንና ግብፅ ሉጣሉ ነው አሉ?
የምስራች ሱዳንና ግብፅ ሉጣሉ ነው አሉ። ሰው ሲጣላ የምስራች አይባልም ግን በኢትዮጵያ የመጣ ስለሆ ነው። ይህን ቢቢሲ፣ ሲኤንኤን ወይም አልጃዚራ የዘገበው አይደለም። የውስጥ አዋቂ ነው የተነፈሰው። ነገሩ እንዲህ ነው። ድሮ ሱዳን ከዛሬዋ ደቡብ ሱዳን ነፃ አውጪ ጋር ግብ ግብ ስትፈጥር ግብጽ ድመጿን አጥፍታ በሰሜን ሱዳን ወይም ደግሞ በደቡብ ግብፅ ላይ ወደ ቀይ ባህር የምትጥጋዋን ሃላብ (Hala'ib (Arabic: حلايب) or Halayeb) የተለለች ቦታ(ወደብ) አፈፍ አድርጋ ልክ አሁን ራሽያ ካርምያን እንደወስደችው ትወስዳልች። በዚያን ወቅት አልባሽር ሃሳቡ ሁሉ ደቡብ ሱዳንና ዳርፉር ላይ ስለነበር የሆዴን በሆዴ ብሎ ቁጭ ብሎ ነበር። አሁን ግን የይገባኛል ጥያቄ ስላነሳ ግብፅ ለጥያቄው ደስተኛ አይደለችም ነው የሚሉት። ይህ ብጥብጥ ገና ጥንስስ ሲሆን እየፈላ ነው አሉ። ይህ ለኢትዮጵያ ታላቅ ዜና ነው። ሳይደግስ አይጣላም ይሉታል ይህን ነው።
Hala'ib
or Halayeb is a Red Sea port and town, located in the Hala'ib Triangle,
a 20,580 km² area disputed between Egypt and Sudan. The town lies on
the southern tip of the Egyptian Red Sea Riviera and is near the ruins
of medieval Aydhab.
Hala'ib
ፔት (pet) ዶሮ ወይም በግ
ከዚህ
ከአሜሪካ አንድ ድረ ገጽ አለ ስሙ ክሬግስ ሊስት(craigslist) ይባላል። ልክ
ኮልፌ ተራ፣ መርካቶ፣ ፒያሳ ሁሉም ተደባልቆ እንደ ማለት ነው።ድረ ገጹ ላይ አንዱ ቤት
ያከራያል፣ ሌላው አሮጌ ካልሲ ይሽጣል፣ አንዷ እዩኝ ትላለች አንዱ ይህን እፈልጋለሁ ይላል ሌላው ስራተኛ ቀጣሪ አስቀጣሪ ነኝ፣ እንጨት ፈላጭ፣ ቀለም ቀቢ፣ አስተማሪ፣ ዘበኛ፣ ልጅ ጠባቂ በቃ ሁሉም አለ። ታዲያ አንድ ቀን በአጋጣሚ አንድ ሰው ዶሮ በነጻ እሰጣለሁ የሚል ማስታወቂያ አየሁ። በቃ ቀይ ገብስማ
ዶሮ። ወዲያው ደወልሁለት። የሚከተለው ቃላ ምልልስ ተደሮጎ ነበር። በአጭሩ
እኔ
“ሄሎ”
ባለ
ዶሮ “ሄሎ”
እኔ
“ማስታዎዊያ አይቼ
ነበር ክሬግሊስት ላይ”
ባለ ዶሮ “የምን
ማስታዎቂያ?”
እኔ”
በነጻ የምትሰጥ
ዶሮ”
ባለ ዶሮ “አዎ አለች”
እኔ
“መውሰድ እችላለሁ”
ባለ
ዶሮ “አዎ ግን
አንድ ነገር ቃል ግባ”
እኔ
“ምን?”
ባለ
ዶሮ “ዶሮዋን መብላት አትችልም”
እኔ
“ምን?”
ባለ
ዶሮ “አዎ ዶሮዋን መብላት አትችልም”
እኔ
“ህም…”
ባለ
ዶሮ “አዎ ዶሮዋ ፔት (pet) ነች። ግን አንቁላሏን ብቻ ነው መብላት የምትችለው”
እኔ
ፔት የሚለው ድመት ናት ነው
የመሰለኝ
እኔ
“እሺ”
ከዚያ
የት እንደማስቀምጣት ግራው ሲገባኝ ሳላመጣ ቀረሁ።
ግን
ያ ፔት (pet) የሚለው ነገር ሁሌ ያስቀኛል
ምክንያቱም
እዚህ አሜሪካ (የሌላውን አገር አላውቅም) በግም ሆነ ፍየል ወይም ዶሮ አሳማማ መሆን ይችላል አንዴ ፔት (pet) የሚለውን ስም ካገኘ አይበላም አሉ። ፔት (pet) ማለት ልክ የእንስሳ ጓደኛ ማለት ነው። ከሁሉ ፈገግ ያደረገኝ ኢትዮጵያ እያለሁ አስፈልፍየ
አሳድጌ ትልቅ ሲሆኑ ያው ታርደው የተበሉት ፔቶቼ ናቸው። አዎ የለመዱት በግም ሆነ ዶሮ ሲታረድ ያሳዝናል ግን ያው ያለ ነው። ቻለው ቻለው አለ ዘፋኙ:: የአገራችን ዶሮወችና በጎች የዚህ
የፔትን ነገር ቢሰሙ ለፋሲካ ስንት ዶሮውች ነፍሳቸው ይተርፍ ነበር። ግን የፔትን ነገር ያገራችን ዶሮችና በጎች አይስሙት ነው።
ዳሩ ዋጋቸው ስለናር ሳንወድ በግዳችን ፔቶች ሆነዋል።
Tuesday, April 15, 2014
የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ የሆነ ሁሉ ሁሌ አባታችን ሆይ ብሎ መፀልየን ያውቃል:: ይበል! ይበል! ነው።
የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ የሆነ ሁሉ ሁሌ አባታችን ሆይ ብሎ መፀልየን ያውቃል:: ይበል! ይበል! ነው።
ግን የአባታችን ሆይ ፀሎት እያንዳንዱ መስመር ትልቅ ሚስጢር ያለው ሃያል ቃል ነው። ከሁሉ በየእለቱ ከምንፀልየው ውስጥ ግን ብዙወቻችን ትልቅ ውሸት ይዘን ነው ይምንፀልየው።
በተለይም ደግሞ አንደኛዋ መስመር በቃ በውሸት የተሞላች ነች። እንዲህ ትላለች "እኛም የበደሉልን ይቅር እንደምንል ሁሉ በደላችንን ይቅር በለን።" አቤት ውሽት። አሁን ማን ይሙት ማነው የበደለውን ይቅር የሚል? ወይ እራስን መደለል። እኔ ካዛሬ ጀምሬ ያንን ፀሎት በፀለይሁ ቁጥር በቀን አንድ ሰው ይቅር ለማለት ተንስቻለሁና እናንተም ተከተሉኝ።
ይቅር ሳልል አባታችን ሆይን መፀለይ እራሱ ታላቅ ሐጢያት ነው። ውሽት ጥሩ አይደለምና!
If you like this share.
The Lord's Prayer In English
Our Father who art in Heaven
Hallowed by thy name
Thy Kingdom come
Thy will be done
On Earth as it is in Heaven
Give us this day our daily bread
And forgive us our trespasses
As we forgive those who trespass against us
And lead us not into temptation
But deliver us from evil
For thine is the Kingdom
The Power and the Glory
Forever and ever
Amen
The Lord's Prayer in Ge'ez
Abune Zebesemayat
Yitkedes Simike
Timsa Mengistike
Weyikun Fekadeke
Bekeme Besemay Kemahu Bemedir
Sisayene Zelele Ilitene Habeneyom
Hidig Lene Abesane Wegegayene
Keme Nihinenee Nihidig Leze Abese Lene
Etabiane Igzeeo Wiste Mensut
Ala Addihanene
Webalihane Imkwulu Ikuy Isme Zeake
Yeite Mengist Hayl We Sebhat
Lealem alem
Amen
The Lord's Prayer in Amharic
Abatachin Hoy Besemay Yemitnor
Simmeh Yekedes
Mengistih Timta
Fekadeh Besemay Indehonech
Indehum Bemedir Tihun
Yeilet Injerachinin Siten Zare
Bedelachininim Yeker Belen
Enyam Yebedelu Yeker Endeminil
Abetu Wede Fetenan Atagban
Kekefu Hulu Adinen Enje
Mengist Yante Natinna
Haylim Kibre Misganna
Lezelamu
Amen
Subscribe to:
Posts (Atom)