Shop Amazon

Sunday, November 15, 2020

የሕወሓት ጁንታ በመከላከያ ኃይሉ ጀግንነት እና በኢትዮጵያ ሕዝቦች የጋራ ክንድ ጀንበሩ ጠልቃለች-የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሓላፊ

የሕወሓት ጁንታ በመከላከያ ኃይሉ ጀግንነት እና በኢትዮጵያ ሕዝቦች የጋራ ክንድ ጀንበሩ ጠልቃለች-የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሓላፊ
****************************

27 ዓመታትን ፈላጭ ከፋፋይ ሥርዓት ሲከተል የነበረው እና ለኢትዮጵያ ሕዝቦች የመከራ ምንጭ ሆኖ የቆየው የሕወሓት ጁንታ በመከላከያ ኃይሉ ጀግንነት እና በኢትዮጵያ ሕዝቦች የጋራ ክንድ ጀንበሩ የጠለቀችበት መሆኑን የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሓላፊ አቶ ነብዩ ስሁልሚካኤል ገለጹ።

በሕወሓት ውስጥ የሚገኘው ጨካኝ የጁንታ ቡድን ላለፉት 45 ዓመታት የትግራይ ሕዝብን አፍኖ በመግዛት ከልማት እና ከዴሞክራሲ እንዲርቅ ከማድረጉም ባሻገር በኢትዮጵያ ውስጥ ከፋፋይ ሥርዓትን በማንገሥ ሕዝቡ እርስ በራሱ በጥርጣሬ እንዲተያይ አድርጓል ብለዋል ኃላፊው።

ከሁለት ዓመታት በፊት በዚህ ጨቋኝ ቡድን የተማረሩ ኢትዮጵያውያን ባደረጉት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ቡድኑ ከሥልጣኑ ተወግዶ መቀሌ መመሸጉንና  መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከለውጡ ነፃነት እና ዴሞክራሲ ሲጎናጸፍ የትግራይ ሕዝብ ግን አሁንም በጁንታው ቡድን በጨለማ ውስጥ እንዲዳክር እንደተፈረደበት አቶ ነብዩ አመልክተዋል።

ግፍ እና በደል ልምዱ የሆነው ይኸው ጁንታ ቡድን፣ ላለፉት 20 ዓመታት ከትግራይ ሕዝብ ጋር ደስታ እና መከራን በጋራ እንደ አንድ ቤተሰብ ሲያሳልፍ በቆየው የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት በማድረስ ከሀዲነቱን የሚያረጋግጥ በደል ፈጽሟል፣ ይህም በርካታ የትግራይ ሕዝብን እንዳስቆጣው ጠቁመዋል።

ቡድኑ ያሰማራው ልዩ ኃይል ዓላማ ለሌለው ጦርነት ራሳችንን አንማግድም ማለት መጀመሩን ጠቁመው፣ ሚሊሻውም ይህ ጦርነት የጥቂት የሕወሓት ካድሬዎች ጦርነት እንጂ የሕዝብ ጦርነት ባለመሆኑ አንዋጋም በማለት እጃቸውን ለመከላከያ በመስጠት ላይ ይገኛል ብለዋል።

መከላከያ ሠራዊቱም ከትግራይ ሕዝብ ጭምር በሚያገኘው ሕዝባዊ ድጋፍ እየተመራ ጦርነቱን በአጭር ጊዜ ለመቋጨት ወደ አጥፊው ቡድን በመንደርደር ላይ እንደሚገኝ አቶ ነብዩ አብራርተዋል።

ቡድኑ ከዚህ በኋላ እንኳን መንግሥት ሆኖ ሊቀጥል ቀርቶ ቡድን ሆኖ መቀጠል ከማይችልበት የመጨረሻ ደረጃ ላይ መድረሱን አመልክተው፣ በቅርቡም ግብዓተ መሬቱ ይፈጸማል ሲሉ አቶ ነብዩ ተናግረዋል።

የትግራይ ሕዝብ ለውጥ እየፈለገ የኖረ ሕዝብ በመሆኑ መንግሥት ያቋቋመውን አዲሱን አስተዳደር በመደገፍ የጁንታውን መጨረሻ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል ማለታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በዘገባው አመልክቷል።


No comments:

Post a Comment