Shop Amazon

Tuesday, January 4, 2022

Ethiopia is the second country for all Africans," said Senegal's ambassador

"ኢትዮጵያ ለመላው አፍሪካውያን ሁለተኛ ሀገር ናት" ፦የሴኔጋል አምባሳደር 
*******************

ኢትዮጵያ ለመላው አፍሪካውያን ሁለተኛ ሀገር ናት ሲሉ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙት የሴኔጋል አምባሳደር መሀመድ ላሚን ቲያው ገለጹ።

አምባሳደሩ የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኘሮቶኮል ጉዳዮች ምክትል ሹም ለሆኑት አምባሳደር ዓለማየሁ ሰውአገኝ አቅርበዋል። 

በወቅቱም ተሿሚ አምባሳደሩ ኢትዮጵያ ለመላው አፍሪካ ሁለተኛ ሀገር መሆኗን ጠቅሰው ÷ ሴኔጋል ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፍላጎት መኖሩን  ተናግረዋል። 

በሥራ ቆይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል በባሕል እና ቱሪዝም ዘርፎች ያለውን ትብብር ለማስፋት እና በኢንዱስትሪ ፓርክ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ልምድ ለመቅሰም እንደሚፈልጉም ጠቁመዋል። 

አምባሳደር ዓለማየሁ በበኩላቸው ÷ ሴኔጋልና ኢትዮጵያ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አንስተው ÷ የሁለቱ ሀገራት ህዝቦችም ይበልጥ ተጠቃሚ በሚያደርጉ መስኮች ላይ አተኩረው መሥራት እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

አምባሳደሩ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው የሥራ ቆይታ የተሳካ ስራ ማከናወን እንዲችሉ ተገቢው ትብብር እንደሚደርግላቸውም አምባሳደር ዓለማየሁ እንዳረጋገጡላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
"Ethiopia is the second country for all Africans," said Senegal's ambassador
 *******************

 New Ethiopian Ambassador to Ethiopia Mohamed Lamin Tiaw

 The Ambassador presented a copy of his credentials to Ambassador Alemayehu Seguegen, Deputy Chief of Protocol at the Ministry of Foreign Affairs.

 He said Ethiopia is the second largest country in Africa and that Senegal wants to strengthen its historic bilateral relations with Ethiopia.

 He said the two countries would like to expand cooperation between the two countries in the fields of culture and tourism and gain experience in the industrial park sector.

 Ambassador Alemayehu on his part said Senegal and Ethiopia have strong diplomatic relations and the people of the two countries should focus on areas that benefit them the most.

 According to information obtained from the Spokesperson's Office of the Ministry of Foreign Affairs, Ambassador Alemayehu assured them that they will be given the necessary cooperation to enable them to carry out their duties successfully during their stay in Ethiopia.



No comments:

Post a Comment