Shop Amazon

Tuesday, January 4, 2022

The five superpowers pledged to prevent a nuclear war

አምስቱ የዓለም ኃያላን አገራት የኒውክሌር ጦርነትን ለመከላከል ቃል ገቡ
 ******************

 አምስቱ የዓለም ኃያላን አገራት የኒውክሌር ጦርነትን ላለማድረግና ለመከላከል የሚያስችል አዲስ ስምምነት ማድረጋቸው ተነገረ።
 አምስቱ የዓለም የኒውክሌር ሃይሎች ቻይና ፣ ፈረንሳይ ፣ ሩሲያ ፣ ብሪታንያ እና አሜሪካ ሰኞ እለት በሰጡት የጋራ መግለጫ የኒውክሌር ጦርነትን ለመከላከል እና የጦር መሳሪያ ውድድርን ለማስወገድ ቃል መግባታቸውን ገልጸዋል።

 የኒውክሌር ጦር መሳሪያ መስፋፋትን ለመከላከል ቃል የገቡት እነዚህ የዓለም ኃያላን መንግሥታት የኒውክሌር ጦርነትን ማሸነፍ እንደማይቻል እና ፈጽሞ መዋጋት እንደሌለበት አረጋግጠናል ሲሉም በመግለጫቸው አክለዋል።

 አምስቱ ፈራሚ ሀገራት የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን የኒውክሌር ሃይል ያለመስፋፋት ስምምነትን ፣ ትጥቅ የማስፈታት እና የጦር መሳሪያ ቁጥጥር አለም አቀፍ ስምምነቶችን አክብረው እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል።

 ፒ አምስት በመባል የሚታወቁት አምስቱ የኒውክሌር መንግስታት በአለም ላይ የአቶሚክ መሳሪያ ያላቸው ብቸኛ ሀገራት አይደሉም።

 ህንድ እና ፓኪስታን ሁለቱም የያዙ ሲሆን እስራኤል የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዳላት በሰፊው ይታመናል።

 ከዚህ ባለፈም ሰሜን ኮሪያ በርካታ የኒውክሌር መሳሪያዎችን እንደሞከረች ይነገራል።

 በትናትናው ዕለት ይፋ የተደረገው የጋራ መግለጫ ለ 10 ኛ ጊዜ ሊካሄድ ከነበረው የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎችን ያለመስፋፋት ስምምነት ግምገማ በፊት ቀደሞ የተደረገ ሲሆን ይህም በዚህ ወር በኒውዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ሊካሄድ ታቅዶ እንደነበረ አርቲ ዘግቧል።
The five superpowers pledged to prevent a nuclear war
 ******************

 The five world powers are said to have reached a new treaty on nuclear non-proliferation.

 The five world nuclear powers, China, France, Russia, Britain and the United States, said in a joint statement on Monday that they were committed to "preventing nuclear war and eliminating arms race."

 "These superpowers, which have pledged to prevent the spread of nuclear weapons, have proved that nuclear war cannot be won and will never be fought," he said in a statement.

 The five signatory countries will continue to abide by the bilateral and multilateral nuclear non-proliferation treaties, disarmament and arms control agreements.

 The five nuclear powers, known as the P5, are not the only ones in the world with nuclear weapons.

 Both India and Pakistan hold, and Israel is widely believed to have nuclear weapons.

 North Korea has reportedly tested a number of nuclear weapons in the past.

 The joint statement issued ahead of the 10th Nuclear Non-Proliferation Treaty (NPT) review, which was scheduled to take place at the United Nations headquarters in New York this month, Arty reported.

No comments:

Post a Comment