በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል 8 የሽፍታ አባላትን ጨምሮ 95 የጉሙዝ ማህበረሰብ ክፍሎች ወደ ወረዳ ማዕከል ተመለሱ
****************
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በዳንጉር ወረዳ 8 የሽፍታ አባላትን ጨምሮ በህወሓት ተላላኪዎች በሚያደርሱባቸው ጫና ጫካ የገቡ 95 የጉሙዝ ማህበረሰብ ክፍሎች ወደ ወረዳ ማዕከል መመለሳቸው ተገለፀ፡፡
የክልሉ መንግስትና በዞኑ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ያቀረቡትን የሠላም ጥሪ በመቀበል በዳንጉር ወረዳ በርካታ የጉሙዝ ማህበረሰብ ክፍሎች በተዘጋጀላቸው የወረዳ ማዕከል እየገቡ መሆኑም ተገልጿል፡፡
በዛሬው እለትም 2 የታጠቁ እና ሌሎች 6 የሽፍታ አባላትን ጨምሮ 95 የጉሙዝ ማህበረሰብ ክፍሎች ወደ ወረዳ ማዕከል ገብተዋል ተብሏል፡፡
በመካከላችን በነበረው ጥርጣሬና አለመተማመን ምክንያት የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ሁላችንንም ዋጋ አስከፍሎናል ብለዋል አቶ መሰረት ፡፡
በተሳሳተ መንገድ እርስ በእርስ የምናደርገው ግጭትና ጦርነት ኪሳራ እንጂ ትርፍ የሌለው በመሆኑ፣ የመንግስትን የሠላም ጥሪ መቀበላቸው አግባብና ትክክለኛ ውሳኔ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ህዝቡ በተሳሳተ አሉ ባልታ ወሬ በመስጋት ለመግባት እየፈራ መሆኑን ገልፀው፣ መንግስት የሠላም ጥሪ የጊዜ ገደቡን በማራዘም ንፁሀን ዜጎች የከፋ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ሊሰራ ይገባል ብለዋል አቶ መሰረት፡፡
በዳንጉር ወረዳ እስካሁን 249 የጉምዝ ማህበረሰብ ክፍሎች የሠላም ጥሪውን ተቀብለው ወደ ወረዳ ማዕከል ማግባታቸውን ዘገባው አመላክቷል ሲል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል ፡፡
In Benishangul-Gumz, 95 members of the Gumuz community, including 8 bandits, returned to the district center
****************
In Benishangul-Gumz State, 95 members of the Gumuz community, including 8 bandits, have been returned to the Woreda Center under pressure from TPLF members, including 8 gang members.
It is also stated that a large number of Gumuz community members in Dangur woreda are entering the woreda center prepared by the regional government and the zonal command post.
As many as 95 members of the Gumuz community, including 2 armed men and six bandits, entered the district center today.
"The insecurity caused by the suspicion and mistrust among us has cost us all dearly," Meseret said.
He asserted that his confession had been obtained through torture and that his confession had been obtained through torture.
He said the people are afraid to enter the country due to rumors that the government is in trouble.
According to the Benishangul-Gumuz Regional State Communication Affairs Office, 249 members of the Gumz community have so far accepted the call for peace and entered the woreda center.
No comments:
Post a Comment