Shop Amazon

Friday, May 16, 2014

አሁን ኢትዮጵያን የመሰል አገር የት ይገኛል?

አሁን ኢትዮጵያን (Ethiopia) የመሰል አገር የት ይገኛል?

GOD LOVES ETHIOPIA!

ፋጣሪ ኢትዮጵያን ይወዳታል ሲባል ለአንዳንዶቹ አይዋጥላቸውም። ግን እስኪ መለስ ብላችሁ አስቡ። እንደ ጃፓን(Japan)  ያለ የጎርፍ ማጥለቅለቅ (Tsunami) ፣ እንደ ሄይቲ (Haiti) ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ እንደ ካሊፎርንያ ያለ በሳት መለብለብ (wildfire)፣ አውሮፓ ላይ ባለፈው የደረስው አመድ (ash) የሚጠፋ እሳተ ጎሞራ ፣ ደቡብ ሱዳን ላይ ያለው የእርስ በርስ ጦርነት (civil war)፣ ሶርያ (Syria) ላይ ያለው እልቂት እና ሌሎችንም ሰው ስራሽም ሆነ የተፈጥሮ አደጋዎችን ስናይ ኢትዮጵያ ገነት ናት ያሰኛል። ባለፈው አመት ኒዎርክና ኒው ጀርሲን ያጥለቀለቀው ጎርፍ፣ በየቦታው ያለው የበረዶ ማእበልና አውሎ ንፋስ ፣ ላልፈው ጊዜ ሉዚያና  ላይ የደርሰው ሄሪኬን ካትሪና (hurricane Katerina) ተብሎ የሚጠራው የእግዜር ቁጣና ሌላውን ስናይ ወይ አገሬ ነው የሚያሰኘው።  በሌላው አለም ሲሞቅ ሙቀቱ በቁም የሚያቀልጥ ሲቀዝቅዝ ደግሞ በቁም የሚያደርቅ በረዶ ነው። ብርድ ላይ ልብስ ድራርቦ ቁም ሳጥን መስሎ ሲኖር ሲሞቅ ደግሞ እንደ እብድ እራቁት ካለሄዳችሁ የሚያሰኝ ሙቀት ነው ያለው። ቤቱ ክረምት(winter) ካለማ ሞቂያ (heater) በጋ  Summer ደግሞ ካለማቀ ዝቀዣ (air condition)  አይሆንም:: ያገራችን ብርድ ግን ግፋ ቢል በጋቢ  ከጠነከረም ብርድ ልብስ ጣል አድርጎ ለጥ ነው። ሲሞቅም ውጭ ወጣ ብሎ ወይም ጥላ ስር ቁጭ ነው።አመቱን ሙሉ አንድ ልብስ ብቻ መልበስ ይቻላል::

ሌላው የአለም ክፍል ሰው በብርድ ወይም በሙቀት ይሞታል። አዎ በተለይ ህፃናት እና አሮጊት በጊዜው ተገቢውን ሙቀት ወይም ቅዝቃዜ ካላገኙ  ወዲያ ተክ ሊሉ ይችላሉ። ለምሳሌ የበረዶ ላይ ያለ ብርድ በአጭሩ ላስረዳችሁ። ሰውነታችን ብርድ በሚሆንበት ጊዜ እራሱን ለማሞቅ ብዙ ሃይል ያመነጫል። ያም ሲሆን ልባችን በተለያዩ የአካላችን ክፍሎች ላይ ደም መርጨት ይጀምርና በቶሎ እርዳታ ካላገኘን ልባችን አስፈላጊ ናቸው ለሚላቸው የስውነት ክፍሎች ብቻ ደም ይስጥና ሌሎችን  ደም መስጥት ያቆማል። በዚህ ሁኔታ ልባችን በጣም አያስፈልጉም የሚላቸው የእግር እና የእጅ ጣትና ጥፍር፣ የጆሮ እና የ አፍንጫ ጫፍ ናቸው። እነዚህ የሰውነት ክፍሎች ልባችን ደም እንዳይሄድ ስለሚከለክል ይደርቃሉ። ግለሰቡ ለብዙ ሰዓት በጣም ቀዝቃዛ በረዶ ላይ ቢተው መጀመሪያ ጆሮው ድርቅ ይልና ልክ እንደ ደረቅ ቂጣ ቢነኩት ቅንጥስ ይላል። እንዲሁም የእግራችን ጣት ይደርቅና መልኩ ይበልዛል (frostbite)። አስችኳይ እርዳታ ካላገኘ ወዲያው ይቆረጣል። ግለሰቡ ለብዙ ሰዓታት ለብርድ ከተጋላጠ (hypothermia) ልብ የሚቻላውን ሁሉ እየቆጠብ አስፍላጊ ናቸው ለተባሉ የስውነት ክፍሎች ሁሉ ደም ይርጫል። የመጨረሻው አንጎላችን ነው። ከዚያ ወደ አንጎላችን በቂ ደም ካልሄድ ግለስቡ እራሱን ይስትና (feint) ተገቢው ህክምና ካልተገኘ ወዲያ ይሞታል።
ታዲያ ከዚህ ከላይ ይተገለጠው ሰቆቃ አገራችን ቢኖር ስንቱ የጎዳና ተዳዳሪ፣ መናኝ፣ ዘላን፣ ሌላውም እንዴት ይሆን ነበር?  ነገሩማ በአጠቃላይ የአገራችን ቤቶች (most of them) ነፋስ ሳይሆን አሞራ የሚያሾልክ ቀዳዳ ስላለቸው ያ ሁሉ ስቃይ ይደርስብን ነበር:: ግን ጌታ ስለሚዎደን በሰላም ተኝተን በሰላም እንነሳለን። ታዲያ ይህን ምን ይሉታል? እኔማ መታደል ነው ብዬዋለሁ!  እርስውስ ?

No comments:

Post a Comment