የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Friday, May 16, 2014

አሜሪካ አገር ያለውን ኢትዮጵያዊያዊ ካለ ጊዜው የሚቀጩት ሶስት ነገሮች

የአሜሪካ አገር ያለውን ኢትዮጵያዊ ካለ ጊዜው የሚቀጩት ሶስት ነገሮች
አሜሪካ ቶሎ አድጎ ቶሎ ባይ ባይ የሚባልባት አገር ናት። የሆስፒታል ብዛት ወይም የመድሃኒት ጋጋታ ሁሉም ትንሽ እድሜ ያራዝም እንደሆን እንጂ ብዙም አያቆይም። በተለይ ኢትዮጵያዊያን  ሞታችንን በኪሳችን ይዘን ነው የምንዞረው። እነዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ነገሮች እንድሜ አሳጣሪወች ናቸው::





፩ኛ ስጋ። አበሻ ከአንበሳ ጋር ዝምድና ሳይኖርን አይቀርም። ምግባችን ስጋ ከሌለው ምግብ አይደለም። እስኪ እንዬው  ቁርጥ፣ ክትፎ፣ አልጫ፣ ቀይ ወጥ፣ ጎረድ ጎረድ፣ አሮስቶ፣ ዶሮ ወጥ፣ ፍርፍር በቃ ሁሉንም ዘርዝሩት ስጋ ከሌለ ሙያ ገደል ገባ ነው። ታዲያ የአሜርካ ከብት ከብት አይመሰላችሁ ሁሉም  በኬሚካል አድጎ ገና ጥጃ እያለ የሶስት አመት ወይፈን ነው የሚመስለው ታዲያ ያንን ስጋ ከጥሬው እስከ ቅቅሉ ስንለው እኝም በቀሰም እንደተነፋ ፊኛ አብጠን ቁጭ። ዶክተር ጋር ስንሄድ የበሽታችን አይነት ልክ ተዋቂ ምግብ ቤት ያለ የምግብ ዝርዝር (menu) ይመስላል።
  1. ጨንጓራ፣
  2. ኮልስትሮ፣ 
  3. ጉበት፣ 
  4. ጣፊያ፣ 
  5. ኩላሊት፣ 
  6. ስኳር፣
  7. በቃ በያይነቱ። 
ዶክተሩም የሚያዝዝልን ውሃ ብቻ ይሆናል
http://yebbo.com/2013/%E1%88%88%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB%E1%8B%8D%E1%8B%AB%E1%8A%95/
፪ኛ እንጀራ የእንጀራ ነገር ድሮ ቀረ። የአሜርካ እንጀራ ጤፍ 0-5 እጅ (0-5%)  ስንዴ 95 -100  እጅ (95 -100 % )ነው። በአለም ላይ የጤፍ (Teff) ዝና (super food) እየተለፈፈ እኛ ግን ጤፍ ሳይሆ የፍርኖ ዱቄት እንቅማለን። ተመራማሪዎች እንደሚሉት ነጭ ስንዴ  (bleached  wheat) በጣም አደገኛ በሽታ ነው። ያወ የጨውና የበርበሬ ነገር ደግሞ ሆድ ይፍጀው ነው::

፫ኛ ጭንት  በቅርቡ አንደኛ ሳይሆን አይቀርም። አይ አሜሪካ ስንቱን ንጉስና ንግስት ልክ አስገባሽው። ይህ የሚያጠቃው የተንደላቀቀ ኑሯቸውን ለቀው ጌቶች፣ እመይቴ፣ እመቤቴ፣ ጋሸዬ እየተባሉ ተንደላቀው ሲኖሩ ያየሁት አይቅርብኝ ብለው የሞቀ ቤታቸን ለቀው ስደት ላይ ያሉትን ነው። እነዚህ ሰዎች ሂዎታቸው ወይ አሜሪካ ወይ  ኢትዮጵያ አልሆነ በቃ ባዝነው ይቀራሉ። ለዚህ ዋንው መድሃኒት ቆራጥነት ነው። ከዚህ ግሩፕ ላይ አብረው የሚመደቡተ ሳይዎዱ በግድ የሚመጡ ወላጆች ናቸው። ለምን እንደሆን አላውቅም ወዲያው የታመማሉ፣ በጣምም ያሳዝናሉ። በተቻለ መጠን ልጆች ሃላፊነት መውስድ አለባቸው። ነገረ ግን ሳይዎዱ በግዳቸው ከሃገር የወጡት ልብ ይንካሉ። ሁሉም የኛው ናቸውና።

ከላይ የጠቀስኋቸው በተለይ ሁለቱ ህዝቡን እንደ ቅጠል ሊያረግፉት ነው። ችግሩ ምን ይበላ ነው? የፈረንጁ ምግብ ሳር ሳር ይላል። አንድ ቀን ይበላል ግን ማነው ፓስታ ወይም እሩዝ በየቀኑ የሚበላው? እያዎቁ ማለቅ ይሉያል የህን ነው።
የአሜሪካ የቢሉ (bill) ነገር እራሱን የቻለ በሽታ ነው። በዚህ ሰጥተው በዚያ ይወስዱታል::ሌላም ሌላም ብዙ አለ ሆድ ይፍጀው ነው።

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Curated Products for Generation X

https://amzn.to/3VhbwJz GenX Essentials - Curated Products for Generation X ...

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon