Shop Amazon

Tuesday, June 10, 2014

ሙዚቃና አእምሮ Music and brain


ሙዚቃና አእምሮ Music and brain

ሳይንቲስቶች ስለ ሙዚቃ ብዙ ምርምር አድርገዋል።እንኳን በዚህች ጽሁፍ ቀርቶ በሌላ አልጨርስውም። እንደ ሳይንቶስቶች አባባል ህፃናት በለጋ እድሚያቸው ለሙዚቃና ስን ጥብብ ከተጋላጡ አእምፘቸው ለሳይንስና ሂሳብም ክፍት ይሆናል ነው። ያም ማለት ልጆች ቀኑ ሙሉ ይዝፈኑ ሳይሆን የሙዚቃ መሳሪያ ይጫወቱ ነው። ይህ በሃገራችን ከበድ ሊል ይችላል ግን ትንሽ ጠለቅ ብለን ስላላሰብነው እንጂ የሙዚቃ መሳሪያ ሀገራችን ተርፚል። ግን ማንም አላዬውም። ለመሳሌ አስተማሪው ነው። አዎ የሙዚቃ አስተማሪ በጣም ጎበዝ መሆን አለበት። የማስተማር ብቻ ሳይሆን ጥሩ ጆሮ ያለው አስተማሪ መሆን አለበት። ብታምኑም ባታምኑም ከሃምሳ በላይ ሙዚቀኞች ሲጫወቱ አንድ ሰው ትንሽ እንኳ ቢሰሳት ያንን ስው ለይተው ሲያዎጡ በ አይኔ አይቻለውሁ። ጥያቄው አስተማሪ ከየት ይምጣ ነው። መልሱም በጣም ቀላል ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ ውስት ትንሽም ቢሆኑ የተወሰኑ ባንዶች አሉ። ታዲያ እነዚህ የባንድ አባላት ያላቸውን እውቀት ለመጪው ትውልድ ማስትላልፍ የሚችሉት በፍቃደኝነት ልጆችን ሲያስየምሩ ነው። አንዳንዱ የሙዚቃ መሳሪያ አንድ- ለ-አንድ አስተማሪ ያስፈልገዋል ግን አንድ አስተማሪ በቀላሉ መቶ ልጆችን ማስተማር ይችላል። ይታያችሁ አስር አስተማሪዎች አንድ ሺ ህፃናትን ቢያትምሩ እንዴት ደስ ይላል። ታዲያ እነዚህ ህፃናት ከሙዚቃ የሚያገኙት ደስታ ለሌላውም ትምህርት እድል ይከፍታል። አዎ አንዳዶቻችሁ ይህ የህፃናት አሳሳቢ ችግር አይደለም፣ ዛሬ ህጻናትን የሚያሳስባቸው ምሳዬ ምን ይሆን እራቴ ምን ይሆን ነው ልትሉ ትችላላችሁ። አልቃዎምም። የኔ አባባል ቢቻል ነው። ህልም ነው።ታዲያ ይህ ምክር አኢትዪጵያ ላሉ ህጻናትና ወላጆች ብቻ አይደለም ሌላም ሌላም አገር ያሉትን ያጠቃልላል
ከዚህ  ገና ህፃናት የሚዚቃ መሳሪያ ከመጫወታቸው በፊት ልክ ዋሽንት የምትመስል የምትነፋ መሳሪያ አለች። ዋጋዋም በጣም እርካሽ የሆነ ከፕላስቲክ የተሰራ አንድ ዶላር አለ። ዋናውና በጣም ውዱ ከቅርቀሃ የተሰራው ነው። አገራችን ደግሞ ቅርቀሃ ሞልቷል። ከዚያ ነው ልጆች በትንሹ ጀምረው ወደ ሌላው የሚሄዱት። ገማሹ በክር የሚሰራ (sting) ፣ በትንፋ የሚነፋ (air) ፣ በእጅ የሚደለቅና (percussion instrument) ፒያኖ (piano)፣ ኦርጋን (organ) ሌላውንም የሚጫወቱት።  ከዚህ ውስጥ በ አገራችን በጣም የሚወደደው ፒያኖና ኦርጋን ብቻ ነው ሌላው ግን ሞልቶ ተርፎ። ክራር፣ ዋሽንት፣ መስንቆ፣ እንቢልታ፣ ከበሮ፣ በገና ሌላም ሌላውም ሞልቶናል። አገራችን ውስጥ በጣም ከባዱና የማይገኘው መጫዎቻው ሳይሆን

ታዲያ ይህ ምክር ኢትዪጵያ ላሉ ህጻናትና ወላጆች ብቻ አይደለም ሌላም ሌላም አገር ያሉትን ያጠቃልላል::

No comments:

Post a Comment