Shop Amazon

Tuesday, June 10, 2014

አምስተርዳም ላይ የተካሄደው የአበሻው የድብድብ ውድድር ካለ አሸናፊ ተጠናቀቀ።(video)





ቪዲዮው እንደሚያሳየው ማን ማንን እንደሚመታ እና ማን የማን ቡድን እንደሆነ  በውል አለመታወቁ ነው። በቃ ዝም ብሎ ካገኙት ሰው ጋ መቧቀስ ነበር። ቪዲዮው ላይ  የአማርኛና የትግሪኛ ድምጽ ይሰማል።
ድብድቡ የተፈጠረው በኢትዮጵያዊያንና በኤርትራዊያን መካከል ከሆነ ቦክሱን አለማቀፋዊ ይዘት የሚሰጠው ሲሆን ነገር ግን ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ከሆኑ ብሔራዊ የቦክስ ውድድር ይሆናል። ተመልካቾቹ ወይም ቦክሰኞቹ በአራት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ በትግሪኛ፣ በደችና በእንግሊዘኛ ሞራልና ማበረታቻ ለቦክሰኞች የሰጡ ሲሆን አንዳንድ ቦክሰኞች ማንም ሳይነካቸው የተዘረሩ ሲሆን አንዳንዴ ደግሞ ተቃቅፈው አንዱ አንዱን እያባበለ ሲነርተው ያሳያል። በዚህ ውድድር ላይ ሴት እህቶቻችን ጨዋታው ደመቅ እንዲል ከወዲያ ወዲህ እያሉ ልክ የአሜርካው እግር ኳስ (football) ላይ እንዳሉ አድማቂ ሴቶች (cheerleaders) እንጣጥ እንጠር ሲሉ ተመልክቷል። የኛ ፍራቻ ይህ ትይንት ዘንድሮ  ሳንሆዜ ላይ በሚደረገው የኢትዮጵያዊያን እግር ኳስ በአል ላይ እንዳይደገም ነው። መጣላቱን ይጣሉ ምነው ይህን እንስሳ የሆነ ጸባያቸውን ይዘው በጠራራ ፀሃይ የሰው አገር ላይ ያሳያሉ? አሰዳቢ ብቻ..ኤዲያ ለቃቅሞ ነበር ወደየ አገሩ መመለስ::
yebbo.com


No comments:

Post a Comment