የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Tuesday, October 11, 2016

ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ጉዳይ ሥጋቷን ገለፀች (VOA)

ጃን ኪርቢ - የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይጃን ኪርቢ - የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ
የዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የውጥረት ሁኔታ ሥጋት ያደረባት መሆኑን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ ቃል አቀባይ ጃን ኪርቢ ዛሬ ከአሜሪካ ድምፅ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ አስታውቀዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የውጥረት ሁኔታ ሥጋት ያደረባት መሆኑን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ ቃል አቀባይ ጃን ኪርቢ ዛሬ ከአሜሪካ ድምፅ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ አስታውቀዋል፡፡
በኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ላነሷቸው የመሬት መብትና የምርጫ ሕግን ማሻሻያ የመሳሰሉ ብሦቶች መልስ ለመስጠት መንግሥት ቃል መግባቱን ፕሬዚዳንት ሙላቱ መስከረም 20 ለፓርላማው ያደረጉትን ንግግር መንግሥታቸው እንዳጤነው ቃል አቀባዩ ገልፀው የኢትዮጵያ መንግሥት ያቀረባቸውን ሃሣቦች ተግባራዊ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንዲንቀሣቀስ እንደሚያበረታታ አመልክተዋል፡፡
ኪርቢ በማከልም የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው ሣምንት መጨረሻ ላይ የደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፤ በተለይም ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰዎችን መያዝን፣ ነፃ ሃሣብን መገደብን፣ ሕዝባዊ ስብሰባዎችን ማገድን እና የሰዓት ዕላፊ ገደብ መጣልን የመሳሰሉ የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎቹን ተግባራዊ ለማድረግ የሚፈልግበትን ሁኔታ ግልፅ እንዲያደርግ መንግሥታቸው እንደሚፈልግም አስረድተዋል፡፡
“እነዚህ እርምጃዎች ሥርዓትን ለመመለስ የታሰቡ ቢሆኑ እንኳ - አሉ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ጃን ኪርቢ - ነፃ ድምፆችን ማፈንና በኢትዮጵያዊያን መብቶች ውስጥ እራስን የሚጎዳ ጣልቃ ገብነት ማድረግ ለብሦቶቹ መፍትኄ ከማግኘት ይልቅ ሁኔታዎችን የሚያባብሱ ነው የሚሆኑት፡፡”

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Curated Products for Generation X

https://amzn.to/3VhbwJz GenX Essentials - Curated Products for Generation X ...

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon