A Yebbo Global Information Hub

EthioVibes Global

World travel, documents, money, auto, food, culture, history, sports, diaspora, business and technology.

Passport Photo Translation Notary Tax Travel ለኢትዮጵያውያን

One global hub for useful information.

EthioVibes Global organizes practical guides for travel, passport and visa documents, money, tax, auto, food, culture, history, sports, diaspora life, technology, and business.

Best Global Hub Topics
  • Passport, visa, translation, apostille and embassy guides
  • Travel guides for Ethiopia, Africa, USA and the world
  • Money, tax, import/export and small business education
  • Auto, sports, food, culture, history and diaspora resources
Advertisement

Explore the Global Departments

Each department keeps the site organized so readers and search engines understand the purpose of every article.

🌍World TravelCountry guides, airports, travel checklists, Africa, Europe, USA and World Cup travel. 🛂Passport, Visa & DocumentsPassport photos, visa checklists, Yellow Card, apostille, embassy and translation help. 💼Money, Tax & BusinessTax basics, 1099 workers, small business, bookkeeping, imports, exports and banking. 🚗Auto Knowledge CenterHonda, Toyota, used car buying, VIN checks, repair basics, auctions and insurance. ☕Food, Coffee & CultureEthiopian food, African food, coffee culture, restaurants, etiquette and lifestyle. 📚History & BiographyWorld history, Ethiopian history, biographies, inventors, leaders and educational stories. ⚽Sports & World CupFIFA rules, World Cup 2026, teams, stadiums, African football and fan guides. 🤝Diaspora ResourcesCommunity guides, churches, events, family documents, immigration and local services.
Advertisement

ኢትዮጵያ እንደ ህንድ ብትሆን ፋሲካ ምን ይመስል ነበር?

Published

ህንድ አገር አሉ፣ "አሉ" ነው ሰው የከብት ስጋ ስለማይበላ በሬና ላም ጋሪ ይጎትታሉ, ከዚያ አርጅተው መሞት ብቻ ነው። ይህ  አገራችን ውስጥ ቢሆን ምን ይፈጠራል? አታድርስ ነው እንጂ እውን ቢሆን ክትፎ፣ ዱለት፣ ጥብስ፣ ጎረድ ጎረድ፣ ስጋ ወጥ ሁሉም ባይ ባይ ይሉና አቶ ሽሮ ብቻ አለቃ ይሆን ነበር።   ፋሲካም በቃ  ምን ይመስል ይሆን:

ግን እርስዎ ይስማማሉ? ብታምኑም ባታምኑም ጥቅሙ ያመዝናል።  ለኪስም ለጤንነትም ጥሩ ነበር ፣ በተለይ ደግሞ አሁን በሬው በማዳበሪያ እያደገ ሰውን በሽታ ላይ ነው የጣለው አሉ::

ሱዳንና ግብፅ ሉጣሉ ነው አሉ?

Published
የምስራች ሱዳንና ግብፅ ሉጣሉ ነው አሉ። ሰው ሲጣላ የምስራች አይባልም ግን በኢትዮጵያ የመጣ ስለሆ ነው። ይህን ቢቢሲ፣ ሲኤንኤን ወይም አልጃዚራ የዘገበው አይደለም። የውስጥ አዋቂ ነው የተነፈሰው። ነገሩ እንዲህ ነው። ድሮ ሱዳን ከዛሬዋ ደቡብ ሱዳን ነፃ አውጪ ጋር ግብ ግብ ስትፈጥር ግብጽ ድመጿን አጥፍታ በሰሜን ሱዳን ወይም ደግሞ በደቡብ  ግብፅ ላይ ወደ ቀይ ባህር የምትጥጋዋን  ሃላብ (Hala'ib (Arabic: حلايب‎) or Halayeb) የተለለች ቦታ(ወደብ) አፈፍ አድርጋ ልክ አሁን ራሽያ ካርምያን እንደወስደችው ትወስዳልች። በዚያን ወቅት አልባሽር ሃሳቡ ሁሉ ደቡብ ሱዳንና ዳርፉር ላይ ስለነበር የሆዴን በሆዴ ብሎ ቁጭ ብሎ ነበር። አሁን ግን የይገባኛል ጥያቄ ስላነሳ ግብፅ ለጥያቄው ደስተኛ አይደለችም ነው የሚሉት። ይህ ብጥብጥ ገና ጥንስስ ሲሆን  እየፈላ ነው አሉ። ይህ ለኢትዮጵያ ታላቅ ዜና  ነው። ሳይደግስ አይጣላም ይሉታል ይህን ነው።

Hala'ib

Hala'ib or Halayeb is a Red Sea port and town, located in the Hala'ib Triangle, a 20,580 km² area disputed between Egypt and Sudan. The town lies on the southern tip of the Egyptian Red Sea Riviera and is near the ruins of medieval Aydhab.

ፔት (pet) ዶሮ ወይም በግ

Published
ፕት (pet) ዶሮ ወይም በግ

ከዚህ ከአሜሪካ አንድ ድረ ገጽ አለ ስሙ ክሬግስ ሊስት(craigslist)  ይባላል። ልክ ኮልፌ ተራ፣ መርካቶ፣ ፒያሳ ሁሉም ተደባልቆ እንደ ማለት ነው።ድረ ገጹ ላይ  አንዱ ቤት ያከራያል፣ ሌላው አሮጌ ካልሲ ይሽጣል፣ አንዷ እዩኝ ትላለች አንዱ ይህን እፈልጋለሁ ይላል ሌላው ስራተኛ ቀጣሪ አስቀጣሪ ነኝ፣ እንጨት ፈላጭ፣ ቀለም ቀቢ፣ አስተማሪ፣ ዘበኛ፣ ልጅ ጠባቂ በቃ ሁሉም አለ። ታዲያ አንድ ቀን በአጋጣሚ አንድ ሰው ዶሮ በነጻ እሰጣለሁ የሚል ማስታወቂያ አየሁ። በቃ  ቀይ ገብስማ ዶሮ። ወዲያው ደወልሁለት። የሚከተለው ቃላ ምልልስ ተደሮጎ ነበር። በአጭሩ
እኔ  “ሄሎ”
ባለ ዶሮ “ሄሎ”
እኔ “ማስታዎዊያ አይቼ ነበር ክሬግሊስት ላይ”
 ባለ ዶሮ  “የምን ማስታዎቂያ?”
እኔ” በነጻ የምትሰጥ ዶሮ”
 ባለ ዶሮ  “አዎ አለች”
እኔ “መውሰድ እችላለሁ”
ባለ ዶሮ “አዎ ግን አንድ ነገር ቃል ግባ”
እኔ “ምን?”
ባለ ዶሮ “ዶሮዋን መብላት አትችልም”
እኔ “ምን?”
ባለ ዶሮ  “አዎ ዶሮዋን መብላት አትችልም”
እኔ “ህም…”
ባለ ዶሮ  “አዎ ዶሮዋ ፔት (pet) ነች።  ግን አንቁላሏን ብቻ ነው መብላት የምትችለው”
እኔ ፔት የሚለው ድመት  ናት ነው የመሰለኝ
እኔ “እሺ”
ከዚያ የት እንደማስቀምጣት ግራው ሲገባኝ ሳላመጣ ቀረሁ።
ግን ያ ፔት (pet) የሚለው ነገር ሁሌ  ያስቀኛል

ምክንያቱም እዚህ አሜሪካ (የሌላውን አገር አላውቅም) በግም ሆነ ፍየል ወይም ዶሮ አሳማማ መሆን ይችላል አንዴ ፔት (pet) የሚለውን ስም ካገኘ አይበላም አሉ። ፔት (pet) ማለት ልክ የእንስሳ ጓደኛ ማለት ነው። ከሁሉ ፈገግ ያደረገኝ ኢትዮጵያ  እያለሁ አስፈልፍየ አሳድጌ ትልቅ ሲሆኑ ያው ታርደው የተበሉት ፔቶቼ ናቸው። አዎ የለመዱት በግም ሆነ ዶሮ ሲታረድ ያሳዝናል ግን ያው ያለ ነው። ቻለው ቻለው አለ ዘፋኙ:: የአገራችን ዶሮወችና በጎች የዚህ የፔትን ነገር ቢሰሙ ለፋሲካ ስንት ዶሮውች ነፍሳቸው ይተርፍ ነበር። ግን የፔትን ነገር ያገራችን ዶሮችና በጎች አይስሙት ነው። ዳሩ ዋጋቸው ስለናር ሳንወድ በግዳችን ፔቶች ሆነዋል።