የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Thursday, January 6, 2022

The arrival of 10 ambassadors to Ethiopia this week will increase the country's stability - Ambassador Dina Mufti

በሳምንቱ የ10 አገራት አምባሳደሮች  ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው የሀገሪቱን ተደማጭነት የሚያሳድግ ነው -አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
*******************
አንዳንድ ምዕራባዊያንና የአውሮፓ ሀገሮች ዲፕሎማቶች ከኢትዮጵያ ሲሸሹ የ10 አገራት አምባሳደሮቹ  ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው የሀገሪቱን ተደማጭነት ይበልጥ እንደሚያሳድገው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቃባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው ሳምታዊ  መግለጫ 10 የተለያዩ ሀገራትን አምባሳደሮችን  ሹመት ደብዳቤያቸውን  ለፕሬዝደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ማቅረባቸውን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴም ለአምባሳደሮቹ ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ በተመለከተ መብራሪያ መስጠታቸውን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል፡፡
የፈረንጆቹ ዓመት 2021 በኢትዮጵያ ላይ ከባድ ፈተናዎች የነበሩበትና ሀገሪቱ  በብልህነት  በአንድነትና ለድል የበቃችበት  ግዜ  እንደነበር ገልጸዋል፡፡

በተለይም መላው ኢትዮጵያዊያን ትውልደ ኢትዮጵያዊያን  በጋራ ለሀገሪቱ አብሮነታቸውን ያሳዩበት ወቅት ነበር ብለዋል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በመግለጫቸው፡፡

በታላቁ የህዳሴው ግድብ ዙሪያ ሲደረግ የነበረው ድርድርም ወደ አፍርካ ህብረት እንዲዛወር ለማድረግ የተደረገው ጥረት  ከፈተናዎች  መካከል ከጥቅቶች አንዱ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡

በሰሜን የሀገራችን ክፍል ከነበረው  ግጭት ባሻገር የሱዳንና ግብጽ ጫና ከባድ ፈተና እንደነበሩ አምባሳደር ዲና ተናገረዋል፡፡

በቀጣይ በፈረንጆቹ 2022 እቅዳችን  ሉዓላዊነታችንና ነጻነታችንና በማስከበር ከወዳጅ ሀገሮች ጋር ያለንን ግኑኝነት በማጠናከር ፤ በህዝቡ መካከል ውይይቶችንና ስምምነቶችን  አጠናክሮ ለማስቀጠል እንሰራለን ብለዋል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፡፡

በዋለልኝ ታምር
The arrival of 10 ambassadors to Ethiopia this week will increase the country's stability - Ambassador Dina Mufti
 *******************
 Foreign Ministry spokeswoman Dina Mufti said the arrival of the ambassadors of 10 countries to Ethiopia will boost the country's influence as some Western and European diplomats flee Ethiopia.

 In a weekly statement issued by the Ministry of Foreign Affairs, Ambassador Dina Mufti said that she has presented her credentials to President Sahle Work Zewde.

 President Sahle Work Zewdem briefed the ambassadors on the current situation in Ethiopia, Ambassador Dina Mufti said.
 He said the year 2021 was a time of great challenges for Ethiopia and a time when the country was wise, united and victorious.

 In particular, it was a time when all Ethiopians of Ethiopian descent showed solidarity with the country, Ambassador Dina Mufti said in a statement.

 He noted that efforts to relocate the Grand Renaissance Dam to the African Union were one of the few challenges.

 Apart from the conflict in the north of the country, the pressure from Sudan and Egypt has been a severe challenge, Ambassador Dina said.

 In the next 2022 plan, we will strengthen our ties with friendly countries by upholding our sovereignty and independence.  "We will work to strengthen dialogue and agreements among the people," said Ambassador Dina Mufti.

 By the miracle of my Walle Tamir
EBC



በጋና የቁንጅና ውድድር ኢትዮጵያን በመወከልና በማስተዋወቅ የተሳተፈችው ጋናዊት አዲስ አበባ ስተገባ የተደረገላት አቀባበል

በጋና የቁንጅና ውድድር ኢትዮጵያን በመወከልና በማስተዋወቅ የተሳተፈችው ጋናዊት አዲስ አበባ ስተገባ የተደረገላት አቀባበል
Welcome to Addis Ababa, Ghana.

The Aluha Bridge, which was demolished by the terrorist TPLF, has been completed and is open for service

በአሸባሪው ህወሃት ፈርሶ የነበረው የአልውሃ ድልድይ ጥገና ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
***************************

በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ፈርሶ የነበረው የአልውሃ ድልድይ ጥገና ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ቡድኑ የደረሰበትን ምት መቋቋም ሲያቅተው እና ሲፈረጥጥ የአልውሃን ድልድይ አፍርሶ መሄዱ ይታወቃል።

አካባቢው ከአሸባሪው ቡድን ነጻ መሆኑን ተከትሎ የተጀመረው የአልውሃ ድልድይ የጥገና ስራ በዛሬው ዕለት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን ኢዜአ በቦታው ተገኝቶ ተመልክቷል።

የአልውሃ ድልድይ ፕሮጀክት መሃንዲስ ኢንጅነር ዮሐንስ አያሌው በወቅቱ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የድልድዩ የጥገና ስራ በሰባት ቀናት ውስጥ ተጠናቋል።

የድልድዩ ግንባታም ሙሉ በሙሉ በብረት የተከናወነ መሆኑን ገልጸው፤ 55 ሜትር ገደማ ርዝመት እንዳለውም ተናግረዋል።

ድልድዩም 60 ቶን ወይም 600 ኩንታል የመሸከም አቅም እንዳለውም ጠቅሰው፤ ከሚሰጠው አገልግሎት አኳያ ከፍተኛ ወጪ ተደርጎበት በአጭር ጊዜ ውስጥ የጥገና ስራው እንዲከናወን መደረጉን አመልክተዋል።

የድልድዩ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊጠናቀቅ የቻለውም የኮምቦልቻ ዲስትሪክት የወልድያ ሴክሽን ሰራተኞች ሌት ተቀን በቁጭት ባከናወኑት ስራ መሆኑንም ገልጸዋል።

ድልድዩ ረጅም ጊዜ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ጥራቱን ጠብቆ መጠገኑን ገልጸዋል።

የአካባቢው ህብረተሰብና አሽከርካሪዎች በድልድዩ መልሶ መገንባትና ለአገልግሎት መብቃት በመቻሉ የተሰማቸውን ደስታ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

The Aluha Bridge, which was demolished by the terrorist TPLF, has been completed and is open for service
 ***************************

 Alwha Bridge, which was demolished by the terrorist group TPLF, has been completed and is operational.

 It is known that the Alwhan Bridge collapsed when the group could not cope with the blow.

 ENA observed that the Alwaha Bridge, which started following the liberation of the area from the terrorist group, has been completed and is open for service today.

 Alwha Bridge Project Engineer Yohannes Ayalew told ENA at the time:  Repairs to the bridge were completed in seven days.

 He said the construction of the bridge was made entirely of steel.  He also said that it is about 55 meters long.

 He said the bridge has a capacity of 60 tons or 600 quintals.  He said the repair work was carried out in a short period of time due to the high cost of the service provided.

 He said the construction of the bridge was completed in a short period of time due to the hard work of Woldia Section staff of Kombolcha District.

 He said the bridge has been maintained to ensure long service life.

 The ENA reported that the local community and drivers are happy that the bridge has been rebuilt and is ready for use.




 

Public enterprises have been banned from wasting resources on holidays and donations.

ታህሳስ 28፣2014 

የመንግስት የልማት ድርጅቶች በአላትን አስታከው የተለያዩ ስጦታዎችን በማበርከት ሀብት እንዳያባክኑ ተከለከሉ።

የገንዘብ ሚኒስቴር ለየመንግስት የልማት ድርጅቶች በፃፈው ደብዳቤ ነው ክልከላውን ያሳወቀው፡፡ 

ክልከላው ሃብትን በቁጠባ መጠቀምን ዓላማ ያደረገ መሆኑን ለልማት ድርጅቶች ከተፃፈላቻ ደብዳቤ ሸገር ተመልክቷል፡፡

የልማት ድርጅቶች በአላትን እያስታከኩ  አጋሮቻችን በሚል ለግለሰቦች እና ለተለያዩ ተቋማት ስጦታ የማበርከት ልማዳቸውን እንዲያቆሙ የገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔ ማሳለፉን አሳውቃል፡፡
 
በኮሮና በጦርነት እና በተለያዩ ምክንያቶች የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ጫና ውስጥ መሆኑን የጠቀሰው የገንዘብ ሚኒስቴር ደብዳቤ ጫናውን ተቋቁሞ ልማቱን ለማስቀጠል እንዲህ ያሉ ሀብት የሚባክንባቸው ልማዶችን ከማስቆም ጀምሮ የለተለያዩ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈልጓል ብሏል፡፡

እንደየ ተቋማቱ ቢለያይም በተለያዩ የበዓላት ጊዜ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ከስጦታ ካርድ ጋር ውስኪና ወይንን ጨምሮ የተለያዩ ስጦታዎችን ለግለሰቦችና ለተቋማት በስጦታ የማበርከት ልማድ እንደነበራቸው ተሰምቷል፡፡ 

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የ2014 በጀትን ለመደገፍ ከውጪ ምንጮች ይገኛል ተብሎ የታሰበው ገንዘብ በዚህ ዓመት ላይገኝ ስለሚችል በጀትን ከብክነት በፀዳ መልኩ እና በቁጠባ መጠቀም እንደሚያስፈልግ ለመንግስት ተቋማት ማሳሰቢያ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን 

#Ethiopia #ShegerFM #ገንዘብ_ሚኒስቴር #በዓል #ገና #ShegerWerewoch 
December 28, 2014

 Public enterprises have been banned from wasting resources on holidays and donations.

 The Ministry of Finance announced the ban in a letter to public enterprises.

 Sheger wrote in a letter to development agencies that the ban was aimed at saving resources.

 The Ministry of Finance has announced that it has decided to discontinue the practice of donating to individuals and organizations in the name of our partners during the holidays.

 The letter from the Ministry of Finance stated that the Ethiopian economy is under pressure due to the war and other reasons.

 Despite the differences, it is believed that during the festive period, public enterprises used to give gifts to individuals and institutions, including whiskey and wine, during the holiday season.

 The Minister of Finance, Ahmed Shide, has warned government agencies that the budget, which is expected to be available from outside sources this year, may not be available this year.

 Trudy Zerihun

 #Ethiopia #ShegerFM #Ministry_Minister #F Holiday #Nest #ShegerWerewoch



Ministry of Health receives over 7.3 million doses of CV 19 vaccine !!

ጤና ሚኒስቴር ከ 7 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶዝ በላይ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ድጋፍ ተረከበ!!
_________________

የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባቱን ድጋፍ ያደረጉት አገራት የጀርመን እና የፖርቹጋል መንግስታት ናቸው።

የሁለቱንም መንግስታት ድጋፍ የተቀበሉት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የጀርመን እና የፖርቹጋል  መንግስታት ከ7 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶዝ በላይ የጆንሰን የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ለሀገራችን ድጋፍ ማድረጋቸው የኮቪድ-19 ስርጭት በተበራከተበት ወቅት መሆኑ  ያለውን ጫና ከመቀነስ አንፃር ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡ 

የጀርመን እና የፖርቹጋል  መንግስታት ለኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ እያደረጉት ያለውን ድጋፉና ትብብር ያደነቁት ዶክተር ሊያ ታደሰ  በጦርነቱ የተጎዱ የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረትም የሁለቱም መንግስታት ድጋፉ እንዳይለያቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ለተደረገው ድጋፍም የጀርመን እና የፖርቹጋል መንግስታትን፣ዩኒሴፍን እና የአለም ጤና ድርጅትን አመስግነዋል፡፡በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ዶክተር ሊያ ታደሰ  ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ የጀርመን ምክትል አምባሳደር ሄይኮ ኒትሽክ እና የፖርቹጋል ኤምባሲ ተወካይ ጆዋና ማሪንሆ  በበኩላቸው መንግስታቸው በኮቫክስ የክትባቶች ዓለም አቀፍ ጥምረት አማካኝነት ለኢትዮጵያ  የጆንሰን የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት  ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ያደነቁት የሁለቱ መንግስታት ተወካዮች እየጨመረ የመጣውን የኮቪድ-19 ስርጭት ለመግታት መንግስታቸው ወደፊትም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

የጀርመን መንግስት በኢትዮጵያ የጀርመን ምክትል አምባሰደር አማካይነት ሰባት ሚሊዮን አንድ መቶ ዘጠና ሁለት ሺ ስምንት መቶ (7,192,800) እና  የፖርቹጋል  መንግስት በኢትዮጵያ   የፖርቹጋል ኤምባሲ  በኩል አንድ መቶ ስልሳ አምስት ሺህ ስድስት መቶ (165,600) ዶዝ የኮቪድ -19 መከላከያ ክትባት ድጋፍ አድርገዋል።
Ministry of Health receives over 7.3 million doses of CV 19 vaccine !!
 _________________

 The governments of Germany and Portugal are co-sponsoring the CVD vaccine.

 Receiving the support of both governments, the Minister of Health, Dr. Leah Tadesse, said that the German and Portuguese governments will provide more than 7.3 million doses of Johnson's Covide-19 vaccine to our country at a time when the distribution of Covd-19 is increasing.

 Hailing the support and cooperation of the German and Portuguese governments to the Ethiopian government and people, Dr. Leah Tadesse called on both German and Portuguese governments, UNICEF and the World Health Organization (WHO) to continue their support for the ongoing efforts to rehabilitate war-torn health facilities.  Dr. Leah Tadesse asked.

 German Deputy Ambassador to Ethiopia Heiko Nietzsche and Portuguese Embassy Representative Joanna Mariho on his part said his government has supported the Johnson-Covide-19 vaccine in Ethiopia through the Covax International Coalition.

 Representatives of the two governments praised the ongoing efforts of the Ethiopian government to prevent the spread of CVD-19 and said that their government will continue to strengthen its support to curb the increasing distribution of CVD-19.

 The German government, through the German Deputy Ambassador to Ethiopia, provided 7,192,800's and the Portuguese Embassy in Addis Ababa provided 165,600 doses of CV-19 vaccine.



ወደ እናት ሀገራቸው ለሚጓዙ የደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት አሸኛኘት ተደረገላቸው

ወደ እናት ሀገራቸው ለሚጓዙ የደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት አሸኛኘት ተደረገላቸው
**********************

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጥሪን በመቀበል ወደ አገር ቤት ለመግባት ለተሰናዱት የደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲና በተባበሩት የኢትዮጵያውያን ማህበር በጋራ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል።

ኢትዮጵያኑ ሀገራዊ ጥሪን በመቀበል፣ የውጭ ኃይሎችን ጫና እና ጣልቃገብነት በመቃወም እንዲሁም የመከላከያ ሠራዊታችንን በማበረታታት እና ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን በገንዘብ በመደገፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን በሽኝቱ ላይ የተገኙት የኤምባሲው የዳያስፖራ ሥራ አስተባባሪ አቶ ጌታቸው መኬቦ ተናግረዋል።

ጥሪውን ተቀብለው በመጓዝ ላይ ያሉት በደቡብ አፍሪካ፣ በሌሴቶና እስዋቲኒ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ከ250 በላይ እንደሆኑ የጠቆሙት አቶ ጌታቸው፣ በራሳቸው መንገድ ወደ አገር ቤት የተጓዙ በርካታ ኢትዮጵያውያን መድሃኒት እና ሀገር ቤት አስፈላጊ የሆኑ ስጦታዎችን ጭምር ይዘው መጓዛቸውን አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ሲል ህይወቱን በመገበር ላይ ላለው የሀገር መከላከያ ሠራዊት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ማድረግ፣ በወራሪው ኃይል እኩይ ተግባር ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀደሞ ህይወታቸው እንዲመለሱ ማገዝ እንዲሁም የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ አቅምን ማጎልበት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በዚህም ሀገራዊ ህልውናን ለማዳከም የተሸረበውን ሴራ ከማምከን ባሻገር በአጠቃላይ በሀገሪቱ ላይ የተደቀነውን የህልውና አደጋ ለመመከት በሚያስችል መልኩ የተጀመረው የዲፕሎማሲና የሀብት ማሰባሰብ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማስተላለፋቸውን በፕሪቶሪያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገልጿል።

Members of the South African Ethiopian Diaspora on their way home
 **********************

 The Ethiopian Embassy in Pretoria was hosted by the Ethiopian Embassy in Pretoria and the United Nations in Addis Ababa.

 Getachew Mekebo, the Embassy's Diaspora Coordinator at the Embassy in Addis Ababa, said the Ethiopians have made significant contributions by responding to the call of the country, resisting the pressure and interference of foreign powers, encouraging our defense forces and providing financial support to the displaced.

 According to Getachew, more than 250 Ethiopians and friends of South Africa, Lesotho and Swatini are on their way home.

 He called on the Ethiopian Defense Forces (EDF) to provide all necessary assistance to the Ethiopian Defense Forces (EDF) in order to alleviate the threat posed by the invasion of Ethiopia.

 He called on the Ethiopian government in Pretoria to intensify its diplomatic and resource mobilization efforts to curb the threat to its very existence.

"የኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር በአሸባሪው የጥፋት ቡድን የወደሙና የተዘረፉ የጤና ተቋማትን መልሶ በማደራጀት በፍጥነት ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ ከማድረግ አንጻር ተምሳሌት የሚሆን ድጋፍ በማድረግ እየሰራ ይገኛል" ክቡር አቶ አወል አርባ - የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት
____________________

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በአፋር ክልል በአሸባሪው የጥፋት ቡድን ለወደሙ የጤና ተቋማት አገልግሎት የሚውሉ ግምታቸው ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ  የሚያወጡ የህክምና መገልገያ መሰሪያዎችና ቁሳቁሶችን በዛሬው ዕለት አስረክበዋል። 

በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አወል አርባ እንደተናገሩት ጤና ሚኒስቴር በአሸባሪው የጥፋት ቡድን የወደሙና የተዘረፉ  የጤና ተቋማትን መልሶ በማደራጀት በፍጥነት ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ ከማድረግ አንጻር ተምሳሌት የሚሆን ድጋፍ በማድረግ እየሰራ ይገኛል ብለዋል። 

አሸባሪው የህወሃት ቡድን በክልሉ በካሄደው ወረራ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ የክልሉ ህዝብና መንግስት ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆን የደረሰውን አደጋ በመቋቋም አሸባሪውን የጥፋት ቡድን መደምሰስ መቻሉን ገልጸዋል። በክልሉ የደረሰውን አደጋም ለመቀልበስና የወደሙ የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን መልሶ በማደራጀት መላው የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ከጎናቸው  በመቆም እያደረጉ ያለውን ርብርብ  ያደነቁት ፕሬዚዳንት አወል የኢትዮጵያ ህዝብ ያሳየውን ፍቅር በደንብ ማየት የተቻለበት ጊዜና አጋጣምም መሆኑን ተናግረዋል። ጤና ሚኒስቴርና ስርት የተባለ የግብረሰናይ ድርጅት በክልሉ ለወደሙ የጤና ተቋማት አገልግሎት ላበረከቱት  ድጋፍ በክልሉ ህዝብና መንግስት እንዲሁም በራሳቸው ስም ምስጋና አቅርበዋል። 

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በበኩላቸው አሸባሪውን የጥፋት ኃይል በመደምሰስ የክልሉ መንግስትና ህዝብ የፈጸመውን አኩሪ ገድልና ጀግነት መለው የኢትዮጵያ ህዝብ የኮራበት መሆኑን አንስቶ በክልሉ የወደሙና የተዘረፉ ጤና ተቋማትን በተቻለ መጠን በፊት ከነበሩበት በተሻለ መልኩ ጭምር ወደስራ እንዲገቡ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ሚኒስትር ዴኤታው በአሸባሪው የጥፋት ቡድን በክልሉ ከውደሙት አንዱ የሆነው የጭፍራ ጤና ጣቢያ በቅዱስ ጳውሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድጋፍ ተደርጎለት በፊት ከነበረበት በተሻለ መልኩ ከፍ በማድረግ በመጀመሪያ ሆስፒታል ደረጃ በቅርቡ አገልግሎት ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን በምሳሌነት አንስተዋል።  

በተጨማሪም የጤና ሚኒስትር ዴኤታው  ከአፋር ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ያሲን እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የዱብቲ ጠቅላላ ሆስፒታልን የስሬ እንቅስቃሴ   የጎበኙ ሲሆን የሆስፒታሉ አመራሮችና ባለሙያዎች  የሆስፒታሉ መደበኛ ስራ ሳይስተጓጎል በግዳጅ ላይ ለቆሰሉ የጀግናው መከላከያ ሰራዊት አባላት እያደረጉ ያሉትን ህክምና እና እንክብካቤ እጅግ የምያስመሰግን መሆኑን ተናግረዋል። ሆስፒታሉ የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እያስገነባ ያለው የላቦራቶሪ ማዕከል ግንባታ በተቻለ ፍጥነት ቶሎ አልቆ ስራ እንዴጀምር ጤና ሚኒስቴር አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ዶ/ር ደረጀ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የስርት (Center for international  reproductive health training- CIRHT) ማኔጅንግ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር መቅደስ ዳባ በጤና ሚኒስቴር አስባባሪነት ድርጅታቸው ከዚህ ቀደምም በአማራ ክልል በጦርነቱ ለወደሙ የጤና ተቋማት ድጋፍ ያደረገ መሆኑን አስታውሰው በዛሬው ዕለትም በአፋር ክልል የወደሙና የተዘረፉ ጤና ተቋማትን ወደነበረበት መልሶ አገልግሎት ለማስጀመር የሚያግዙ የተለያዩ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች እንዲሁም 100 ሜድካል አልጋዎች ከነፍራሽ ጋር መበርከቱን ገልጸዋል ። ለወደፍትም ድርጅታቸው ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

check

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon