Sunday, April 27, 2014

ልጅነትዎ (your childhood) መንገድ ላይ ሲደንስ ቢያጋጥምዎት ምን ያደርጋሉ? (Video)

ልጅነትዎ (your childhood) መንገድ ላይ ሲደንስ ቢያጋጥምዎት ምን ያደርጋሉ? (Video)

What LA Clippers will look like with out black


ክፍት የስራ ቦታ። ሰራዎ አልተመቸወትም? ወይስ ስራ የለዎትም?

ክፍት የስራ ቦታ። ሰራዎ አልተመቸወትም? ወይስ ስራ የለዎትም? ለሁሉም እስኪ ከዚህ በታች ያለው ክፍት የስራ ቦታ ለእርስዎ ይመጣጠን እንደሆን ስለ ስራው ማብራሪያ ይመልከቱ። ታዲያ ሌላ ዘመድ ወዳጅ ካለም ይህንን ክፍት የስራ ቦታ መኖሩን ናገሩን አይዘንጉ። እንረዳዳ

Sainthood for John Paul II and John XXIII (Live Video Stream )


Sainthood for John Paul II and John XXIII----
TV2000 - Streaming Online



Saturday, April 26, 2014

አደራ ዲያስፖራዎች ይህንን ቢዚነስ ቢዝነስ ነው ብላችሁ ኢትዮጵያ ይዛችሁት እንዳትገቡ

አደራ ዲያስፖራዎች ይህንን ቢዚነስ ቢዝነስ ነው ብላችሁ ኢትዮጵያ ይዛችሁት እንዳትገቡ

ነገሩ ቱ ሌት (too late) ነው። ግን ጀስት (just) ለመናገር ያክል ነው ። አንድ የማውቀው ሱቅ አለ ገበያው የደራ ነው:: ደንበኞች በየቀኑ በቃ ወጣ ገባ ይላሉ ። ልክ የቤንዚን ማደያ (gas station) ይመስል ሁሉም  ብልቃጡን ይዞ ይሰለፋል:: የሳምንት ቀለቡን ሊሽምት። ይህ በአሁኑ ወቅት  የአሜሪካን የህክምና ባለሙያዎችንና ፖለቲከኞችን እያነጋገረ ያለ ጉዳይ ነው። ስሙ የኤሌክትሮኒክስ ሲጋራ (Electronics Cigarette)  ይባላል። ልክ ጋያ ወይም ሲሻ በትንሹ ብልቃጥ እንደ ማጨስ ነው። 

  ይህንን ሲጋራ ብዙዎቹ የሚያጨሱበት ዋናው ምክንያት ማጨስ ማቆም  ወይም መቀነስ እምቢ ብሏቸው ይህንን እንደ አማራጭ መንገድ ወስደውት ነው። ታዲያ በየቀኑ የማገኘው  ከሱቁ የሚሰራ ሲጋራ የተለመደውን እኛ የምናውቀውን   የሚያጨስ  ልጅ አለ።ልጁ እንደ ነገረኝ ይሀ ሲጋራ የሚሞላ ፈሳሽ (liquid) ሲኖረው እንድ ግለሰቡ ምረጫ ኒኮቲን (nicotine) የተባለው ንጥረ ነገር ይበዛል ወይም ያንሳል። አብዛኞች በትንሹ ይጀምሩና ወደታች ከመሄድ ይልቅ አላሰማቸው ሲል ወደላይ የሄዳሉ ወይም ብዙ ያጨሳሉ። ያም ማለት ከዚህ በፊት ከሚያጭሱት በላይ ስለሚያጨሱ እራስ ምታት ይይዛቸውና በላዩ ላይ መደበኛውን ሲጋራ ሲያጨሱ የባሰ አጫሽ ሆነው ቁጭ። 
ታዲያ ከዚያ የሚሰራውን ልጅ ግን ሁሌ መደበኛ ሲጋራ  ሲያጨስ የማየውን ልጅ ለምን እሱ ለሰው እየሸጠ እራሱ እንደማያጭስ ጠየቅሁት። ልጁም እንዲህ አለኝ። እኔ አለርጅክ (allergic) ነኝ አለ። 

የህ ሲጋራ የሚሞላ ሲሆን የተለያዬ ጣም (flavors)  አለው ለምሳሌ አናናስ፣ሜንታ፣ ብርቱካን በቃ የፈለጉት ጣእም። ታዲያ ልጁ ሲንገርኝ ለነሱ የሚላክላቸው ድፍድፍ (concentrate) ሲሆን እነሱ በርዘው ፣ ከልሰው፣ ጨምረው ጨማምረው ነው የሚሸጡት። ታዲያ ያ የኒኮቲን ጭማቂ/ድፍድፍ በጣም ጠንካራ ሰለሆነ ልጁ እንደ ነገረኝ አፉን ልክ እንደ ቀዶ ጥገና ባላሙያ ሸፍኖ ነው የሚሰራው። ግን ያ አፉን የሚሽፍንብት  ማስክ (surgical mask)  በቂ ስላልሆነ ፈሳሹ ቆዳውን ሲንካው በቃ እከክ ያስመስልበታል ታዲያ ልጁ በጣም ስለሚጠየፈውና ስለሚመው  አጫሸ በመሆኑ ብቻ  እሱ የሚያጨሰው መደበኛ ሲጋራ (regular cigarette) ነው። ታዲያ እንደ ልጁ አገላለጥ ኤሌክትሮኖክስ ሲጋራ ኬሚካል ነው። ገና ጥናቶች አልውጡም, ቢወጡም ለጋዎች ናቸው  አንድ ቀን ግን ብዙ ሰው በዚህ ኬሚካል ሰለባ እንደሚሆን አልጠራጠርም። ታዲያ ዲያስፖራ ይህንን መርዝ ለዚያውም ቻይና የተሰራ ነው የሚሆነው አገራችን ይዛችሁ ህዝቡም እንዳትጨርሱት። ከተቻላችሁ ዶሮ አርቡ ፣ ከብት አድልቡ፣  የሹራብ ፋብሪካ ትከሉ፣ሙዝ ብርቱካን እርሻ መስርቱ፣  but not Electronic Cigarette .አደራ ሲያጌጡ ይመለጡ እንዳይሆን::እንተዛዘን!
 


The 2014 አዳዲስ ምርቃት፣ እርግማንና አባባሎች

The 2014 አዳዲስ ምርቃት፣  እርግማንና አባባሎች:
ቋንቋ ይወለዳል፣ ያድጋል ይመነድጋል ከሆን ምርቃትም ሆን እርግማን ባሉብት መቅረት የለባቸውም ለምሳሌ:-
  • ሃብትህን/ሽን ጉግል(Google) ያድርገው ::
  • የጨነቀው ሚስ ኮል (miscall) ያደርጋል::
  • ቀለጠህ/ ቅር/ሪ እንደ ማሌዥያው አዬር መንገድ::
  • የፌስ ቡክ (Facebook) ጓደኛ ከጅብ አያስጥልም::
  • ሲሮጡ ያስገቡት ጂፒስ አድራሻ (GPS Address) ሲሮጡ ይደመሰሳል::
  • የአሜሪካን እንጀራ መብላት በብልሃት::
ጊዜ ካገኘሁ ሞር (more) አለ።

የትኛው ደቀ መዛሙር (ሃዋርያ) ነው ኢትዮጵያ የሞተው?

የትኛው  ደቀ መዛሙርት(ሃዋርያ) ነው ኢትዮጵያ የሞተው?በቃ አንዳንዴ ሳያስቡት የሚሆን ነገር አጋጥሞውት ያውቃል? ያ ነበር ትናት በኔ ላይ የደረሰው::  ከቻናል ቻናል ሳማርጥ በቃ መፀሃፍ ቅዱስ (BIBLE) ከሚለው ሪሞት ኮንትሮሉ ክሊክ ክሊክ ካላደርግሁ አለ። ስፍራ ስቸር ጠቅ ሳደርገው የፊልሙ 10 ክፍል አለው። የመጣው ይምጣ ብየ ክፍል አንድን (ኦርት ዘፍጠረትን) ጀመርሁት።  ከዚያ  በኋላ የሆነውን ሆድ ይፍጀው ነው። በአስር ቀን የሚያልቀውን ፊልም በአንድ ሌሊት ላፍ አንድጌው ቁጭ። ፊለሙ እንደ ዶክመንተሪ ሆኖ የተሰራ ነው። ያላየሁት ነገር የለም።  አብርሃምን፣ ይሳቅን፣ እስማኤልን፣ ዳዊትን፣ ቅዱስ ገብሬልን፣ እመቤታችንና ልጇን እየሱስ ክርስቶስን ፣ ቅዱስ ሚካኤልን፣ መጥምቁ ዮሓንስን ፣ ሙሴን፣ ጳውሎስን፣  ጎሊያድን፣ በካፋን፣ እየሱስን፣ ሳምሶንን፣ ገሊላን፣ ቤተልሄምን፣ ናዝሬትን፣ ሶዶምና ጎሞራን፣ እዬሩሳሌምን፣ ቀይ ባህርን፣ ግብጽን፣ ሃናን ዮሴፍን፣  ንጉስ ሃሮልድን፣ ጎለጎታን፣  በቃ ሁሉንም አስመስሎ ያሳያል። ፊልሙ ውስጥ  የጌታን ታምር፣ ማን እንደከዳው፣ ማን እንደ ተከተለው፣ ማን አሳልፎ እንደሰጥው፣ ማን እንደፈረደበት ሁሉንም ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ፊልሙ የተሰራው በ2013 ነው። ፊልሙ ከኦሪት ዘፍጥረት ጀምሮ ትንሳኤን ያሳይና እንዴት አድርገው 12ቱ ሃዋርያት (ደቀ ሞዛሙርቱ) እንዴት የእግዚያብሔርን ቃል በአለም ላይ እንዳስፋፉ ይናገርና ከነዚህ 12 ደቀ ሞዛሙርቱ ውስጥ አንዱ ኢትዮጵያ ውስጥ ተገደለ ይላል። ይገርማል ይህንን ያለው ክፍል ፲ ላይ ልክ ሊያልቅ ሲል ነው። ይህንን ነገር ለእኔ አዲስ በመሆኑ የትኛው ደቀ መዛሙርት መሆኑን ከመናገሬ በፊት ጥያቄው ለእርስዎ እተወዋለሁ::ታዲያ የትኛው ደቀ መዛሙርት ነው? የጠላት ወሬ እንዳይሆን?

Thursday, April 24, 2014

እፅዋት እንደ ሰው ህመም ይሰማቸዋል ወይ? ይሰማቸዋል ወይም አይሰማቸውም ከማለታችሁ በፊት ይህንን ቪዲዮ ይመልከቱ


የዛሬው ምርጥ ቃል "ተባበሩ" ነው። (watch the video and share it)


Wednesday, April 23, 2014

እናንተ ክሊክ (click) ባደረጋችሁ ቁጥር ጉግል Google ሳንቲም ክሊክ ያደርጋል ብላችሁ ክሊክ ማድረጉን ታቆማላችሁ ወይስ ክሊክ፣ ክሊክ አድርጋች ሁ እኔን ዶላር በዶላር ታደርጉኛላችሁ?

እናንተ ክሊክ (click)  ባደረጋችሁ ቁጥር ጉግል Google  Adword ሳንቲም ክሊክ ያደርጋል ብላችሁ ክሊክ ማድረጉን ታቆማላችሁ ወይስ ክሊክ፣  ክሊክ አድርጋች ሁ እኔን ዶላር በዶላር (dollar) ታደርጉኛላች ሁ?

አበሻ ምቅነኛ ነው አሉ (ይባላል)  እኔ ግን አላምንበትም::

ከእለታት አንድ ቀን 2 አበሾች ይታሰራሉ አሉ። አሉ ነው ። ከዚያ ፍርድ ይፈረድባቸውና ቅጣታቸውን እራሳቸው ይመርጣሉ አሉ። ግን አንዱ ያንዱን ቅጣት ማየት አይችልም ይባልና አንደኛው አበሻ ተራው ሲደርስ  የሚቀጣውን ሰውዬ  1 አይኔን አጥፋው  ይለዋል። ቀጭውም  በጣም ተደንቆ አንድ አይኑን ጥፍት ያድርግለታል። ከ ዚያ የሁለተኛው አበሻ ይገባና ምን እንደሚቀጣ ይጠየቃል። አፉን ሞልቶ የኔ ጓደኛ ያገኘውን እጥፍ ስጥኝ ይለዋል። የሚ ቀጣው ሰውዬም የአበሻውን ሁለት አይን አጥፍቶር አረፈ አሉ።

አሁን ይህንን ግራ የገባው ተረት ብዙ ሰው ካነበበው ጉግል ሳንቲሙን ዝርግፍግፍ ያደርገውና እኔ ሃብታም እሆናለሁ ግን እናንተ ለራሳችሁ ብቻ አንብባችሁ ከቀራች ሁ ምንም ሳንቲም አላገኝም። ታዲያ ምን ለማድርግ አስቡ? ክሊል(Click)   ውየስ ኖ ክሊክ (no click) ። የሚገርመው ገንዘቡ ከኪሳች ሁ አይወጣም::

Tuesday, April 22, 2014

ካንጋሮ እጅ ወንድ ምን አይነት ወንድ ነው? (Watch the video for your answer)

 
ካንጋሮ እጅ ወንድ ምን አይነት ወንድ ነው? (Watch the video for your  answer) 

መረዋው ድምፄን ሀኪሞች ለፈውስ ተጠቀሙበት::ተመስገን ማለት ይህን ነው።

Love of Songs
መረዋው ድምፄ ሀኪሞች ለፈውስ ተጠቀሙበት
ጓደኞቼ እንደነገሩኝ ድምጼ እንኳን ለዘፈን ለልቅሶም አይሆን ብለውኝ በቃ ሰው ፊት እንኳን ልዘፍን የሌላ ሙዚቃ ማንጎራጎር አቁሜ ነበር።  አንድ ቀን ግን ከኒዎርክ ከተማ ስልክ ተደወለልኝ። እንድዘፍን ወይም ዘፋኝ እንድፈልግ። በነፃ! ዘፋኝ ፍለጋ ለመሄድ አስቤ ግን በነፃ ማንም እንደማይዝፍን ሰላዎቅሁ አፌን አላበላሽም ብዬ ቁጭ አልሁ። ከዚያ ስልኬ መጮሁ አላቋርጥ አለ። ነገሩ እንዲህ ነው። አንድ ኢትዮጵያዊት ህጻን ታማ ኒዎክ ህክምና ላይ ነበረች (ካንሰር ነው ያመማት) ታዲያ ካለባት ህመም ትንሽ እንኳ ፈገግ እንድትል ታስቦ በእሷ ስም ነበር ዘፈኑን ለመዝፍን የተጥየቅሁት ከዚያ ምራጫ ሳጣ እራሴ ዘፈንሁታ። ብታምኑም ባታምኑም ዘፍኛለሁ። አርቲስት ግን ለመባል ገና አልወሰንሁም::ታዲያ ከዚህ የበለጠ ዘፋኝ ከሄት ይምጣ።

ታድዬ ምሳ ከዶክተር ጋር በላሁ

ታድዬ ምሳ ከዶክተር ጋር በላሁ
Well today I have lunch with a doctor. You may say "So what?" Well, here is the story. I was there when he graduated  from 4  years college, and later they told me he went to medical collage.  We never seen each other for years until today. He looks the same even younger than last time I saw him.  If you see him  you can not even think he graduated from high school,  but when he told me what he did my jaw was dropping.
He told me after he graduated from college he went to 6 years for his medical degree to be a surgeon and after 6 years he ditched his dream and started another 6 years to be a heart anesthesiologist, means he will be  dealing with HEART, the center of our life. Yeap, he said he want to do what he loves to do and now he has two medical degrees. I call it running two marathons in single day. This is impossible, imagine most of us are unable to finish what we started thinking it takes too long, but  others are doing it twice with style. So my advice for you  JUST DO IT.
I will!       

ታዲያ ይህን ግለስብ ኮሌጁን ብጥስጥሱን አወጣው ማለት አነሰው።