የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Saturday, December 5, 2020

የጁንታው የጭካኔ ጥግ በሰሜን እዝ ላይ - በወታደሮቹ አንደበት

የጁንታው የጭካኔ ጥግ በሰሜን እዝ ላይ - በወታደሮቹ አንደበት
👉  "አንድ የሰራዊቱ አባል እጁን ከሰጠ በኋላ በታንክ ደፈጠጡት"
👉 "አራስ ልጄን ይዤ የታጣቂዎችን አስከሬን ተሸከሙ አሉን"
👉 "....ቁስለኞችን ሳይቀር ገደሏቸው"
👉  "የሴቶችን ጡት እንደቆረጡም ሰምተናል"
👉 "የተሰው የሰራዊቱ አባላትን አስከሬን በመንገድ ላይ እየጎተቱ ግፍ ፈጽመዋል"
👉  "....አይናቸው ውስጥ በርበሬ እየጨመሩ ያሰቃይዋቸው ነበር"

*************
(ኢፕድ)

አስር አለቃ ቤቴልሄም በዛ ትባላለች፡፡ የ11ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አባል ነች፡፡ የከሀዲው ህወሓት ጁንታ  ታጣቂዎች በሰሜን እዝ መከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የፈጸመውን የጭካኔ ጥግ ተመልክታለች:: ደርሶባታልም፤ የጁንታው ጭካኔ እንኳንስ በወገን ላይ ቀርቶ በሰው ልጅ ላይ ሊታሰብ የማይችል መሆኑን ትናገራለች።

‹‹ሁኔታው ከመፈጸሙ በፊት በሰራዊቱ ውስጥ የጁንታው ተላላኪዎች የሆኑ የሻለቃው አባላት እየተደበቁ በየቀኑ ይሰበሰቡ ነበር፡፡ የዋርዲያ ተራቸውን ጠብቀው ስለማይሰሩም የተቀረው ወታደር ያለእረፍት የእነርሱንም ጭምር ሲሸፍን ቆይቷል። የተቀረው ሰራዊት ቀን ቀን አንበጣ እንዲያባርር ይደረጋል። ደምም ሰጥተናል፡፡ በብዙ ሌሎች ነገሮችም ማህበረሰቡን እንደግፋለን” ትላለች አስር አለቃ ቤቴልሄም፡፡

ጥቃቱ በተፈጸመበት እለትም ቀኑን በሙሉ አንበጣ ሲያባርሩ ውለው ጎናቸውን ለማሳረፍ ጋደም ባሉበት ቅፅበት ነዉ አብረዋቸው በኖሩ በሰራዊቱ ውስጥ በነበሩ ከሀዲ የጁንታው ተላላኪዎች ከጀርባ የተወጉት:: አስር አለቃ ቤቴልሄም ትናገራለች፤ “በዕለቱ ከሌሊቱ አምስት ሰዓት ተኩል ከውጭ ወደ ውስጥ የጥይት ሩምታ ተከፈተብን፡፡ ከውስጥ ደግሞ እነዛ አስቀድመው ሲሰበሰቡና ሲያሴሩ የቆዩት የጁንታው እኩይ አላማ ፍፃሚ የሰራዊቱ አባላት የገዛ ጓደኞቻቸው የሆኑ የሌላ ብሄር ተወላጆችን እየመረጡ በተኙበት በጥይት መምታት ጀመሩ፡፡ ከተኛንበት እየተጣደፍን ወደ ውጭ ወጣን፤ ትጥቃችን ወዳለበት መጋዘን ሄድን። የመሳሪያ ግምጃ ቤቱ ግን ተቆልፏል፡፡ የመጋዘኑን ቁልፍ የያዘውን ወታደር አስቀድመው ገድለውታል” ትላለች አስር አለቃ ቤቴልሄም፡፡

በእለቱ ዋርድያ ላይ የነበሩ የሰራዊቱ አባላት በኮለኔል ሀጎስ መገደላቸውን የምትናገረው አስር አለቃ ቤቴልሄም፤ “ባዶ እጃችንን ስለሆንን እራሳችንን ለመከላከል አልቻልንም፡፡ ጥቂት ሰዎች ብቻ ነበሩ የሚከላከሉት፡፡ ብዙዎችን ገደሉ፡፡ እጅ የሰጡትንም ጭምር ገደሏቸው” ትላለች።

የጁንታው ታጣቂዎች ግፍና ጭካኔ የትየለሌ መሆኑን የምተናገረው አስር አለቃዋ፤ “አንድ የአራተኛ ክፍለ ጦር አባል የነበረ ወታደር እጁን ከሰጠ በኋላ በታንክ ደፈጠጡት፡፡ መትረፍ የሚችሉ ቁስለኞችን ሳይቀር ገደሏቸው፡፡ ሬሳቸውን ሳይቀብሩ የራሳቸውን ሰዎች ሬሳ ብቻ አንሰተው ሄዱ” ስትል ነው የጓዶቿ በከሀዲ የሰራዊቱ አባላትና በጁንታው ታጣቂዎች የተፈጸመባቸውን ግፍ የምትናገረው። 

ከዚህ ሁሉ ግፍና ጭካኔ  በኋላ የተረፉትን እንድነ አስር አለቃ ቤቴልሄም ያሉ የሰራዊቱ አባላትን የጁንታው ታጣቂና ከሀዲ የሰራዊቱ አባላት በሲኖትራክ ጭነው አጉላ ወደተባለ ትምህርት ቤት ወስደው እንዳጎሯቸው ትናገራለች፤ “በህይወት የተረፉና ከሻምበል በላይ የነበሩ የኦሮሞና የአማራ ተወላጅ የሆኑ የጦር መኮንኖችን ለብቻቸው አስቀመጧቸው፡፡ ትኩረታቸው በነሱ ላይ ነበር፡፡ እስከ አሁንም የት እንዳደረሷቸው አላውቅም፡፡

ሴቶችን ለብቻችን በአንድ ክፍል ውስጥ አጎሩን፡፡ ሞባይላችንን፣ ልብሳችንንና ያለንን ዶክመንት፣ ገንዘባችንን ሁሉ ዘረፉን፡፡ ያለምግብና ውሃ ለሶስት ቀን ወንበር ላይ እየተኛን አሳለፍን፡፡ አንዳንድ የወታደር ሚስት የሆኑ ነዋሪዎች ምግብ ሊሰጡን ሲሞክሩ ይከለክሏቸው ነበር፡፡ በረሀብ የተነሳ በጣም ተዳከምን፡፡ በመጨረሻ ጥሬ እየቆነጠሩ ይሰጡን ጀመር”

አፍኝ ቆሎ እየሰጡ አጉረው ለሁለት ሳምንት ያቆይዋቸውን የሰራዊት አባላት እጃቸውን ጠርንፈው አስረው ወደ መቀሌ እንዳመጧቸው ትነገራለች፤ “መቀሌ የእንሰሳት ጤና ኮሌጅ ውስጥ አስቀመጡን፡፡ ስድብ፣  እርግጫና ማንጓጠጥ ይደርስብን ነበር፡፡ ሌላ አካባቢ የሴቶችን ጡት እንደቆረጡም ሰምተናል፡፡ በእኛም ላይ ተመሳሳይ ድርጊት ለመፈጸም መዘጋጀታቸውን እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊቱ የሰጡ የጁንታው ታጣቂዎች ተናግረዋል፡፡ ህዳር 21 እቅዳቸውን ለመፈጸም ሲዘጋጁ ህዳር 20 የመከላከያ ኮማንዶዎች ደርሰው ነጻ አውጥተውናል” ስትል በሰራዊቱና በፈጣሪ ታምር መትረፋቸውን ተናግራለች። 

ጁንታው ለእኩይ አላማው ያልተባብረውን ሁሉ ከማጥፋት የማይመለስ ጨካኝና ከሀዲ ነዉ ያለችው አለቃ ቤቴልሄም በትግራይ የኩያ ተወላጁን ወታደር ተጋድሎም ታስታውሳለች “የአራተኛ መካናይዝድ አባል የሆነ የኩያ አካባቢ ተወላጅ ከእኛ ወገን ቆሞ ያደረገውን ተጋድሎ ማንሳት ያስፈልጋል፡፡ ልጁ ታንከኛ ነው፤ ታንክ ውስጥ እንዳለ እጅህን ስጥ ይሉታል፡፡ እኔ የቆምኩት ለኢትዮጵያ ስለሆነ እጄን አልሰጥም ብሎ በታንክ መዋጋት ጀመረ፡፡ ታንክ ከታንክ ጋር ገጠሙና ተረባርበው ገደሉት”፡፡

ሌላዋ የአይን ምስክር ኮንስታብል አለምነሽ ገመዳ የሰባት ወር እመጫት ናት። የፌደራል ፖሊስ አባል ስትሆን የጁንታው ታጣቂዎችነ የሰራዊቱ ከሀዲ አባላት ለእሷና መሰል እመጫቶች እንኳን እንዳልራሩላቸው ትናገራለች።

ኮንስታብል አለምነሽ  ምድብ የጥበቃ ስራዋ አክሱም አየር መንገድ ውስጥ ነው፡፡ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት አካባቢ አየር መንገዱ ውስጥ በጥበቃ ስራ ላይ ባሉ የፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ የተፈጸመውን ክህደት ስታነሳ እንባዋን መቆጣጠር አትችልም።
“እኔ የሰባት ወር እመጫት ስለነበርኩ መሳሪያዬን ለሌሎች ሰጥቼ ማረፊያ ቤት ውስጥ አራስ ልጄን ይዤ ተቀምጬ ነበር፡፡ ጋንታ አመራሩ የጁንታው ተላላኪ ነው፡፡ ላካስ ከታጣቂዎች ጋር ተመካክሮ ጨርሷል፡፡ በጫካው በኩል አድርገው ወደ ጊቢው ገቡና እጅ ስጡ አሉ፡፡ እርሱ ቶሎ ብሎ መሳሪያውን ሰጣቸው፡፡ ሌሎቹ አንሰጥም ብለው አፈገፈጉ፡፡ ከዚያም ተኩስ ተጀመረ፡፡ አንድ ሃይል አመራር ከማማው ላይ ሆኖ ለመከላከል ሞከረ፡፡ መጨረሻም እጁን እንዲሰጥ አደረጉት፡፡ እጁን ከሰጠ በኋላ ግን በረንዳው ላይ እጁን በሰንሰለት አስረው በዱላ ጨፈጨፉት›› ትላለች ኮንስታብል አለምነሽ።

ኮንስታብል አለምነሽ በከሀዲዎች የተፈጸመው ግፍ ዛሬም ድረስ ከአይኗ አልጠፋ ብሎ አይኖቿ በእንባ እንደተሞሉ ሳግ እየተናነቃት ነበር ሁኔታውን የነገረችን። 
“ከዚያ ወደ እኔ መጡ ቤቴን ዘግቼ እንደተቀመጥኩ የጥይት እሩምታ አወረዱብኝ፤ ውጪ አሉኝ ህጻን ልጅ ስለያዝኩ አልወጣም አልኳቸው፡፡ ጨካኞ ናቸው ለአራስ ልጄ እንኳን አልራሩም:: አስገድደው ገቡና ቤቱን ፈተሹ ፤ አንድም ነገር ሳልይዝ ባዶ እጄን አስወጡኝና ልጄን እንዳቀፍኩኝ በሶምሶማ ሩጪ አሉኝ፤ ከእኔ ጋር ሌላም አንድ ልጅ የያዘች ሴት ነበረች፡፡ እርሷ ግን ጭንቅላቷ አካባቢ ተመታ ደሟን እያፈሰሰች ሩጪ ተባለች። ሁለታችንም ህጻን ልጅ ይዘናል፤ እሩጡ እያሉ አስሮጡን፡፡ ስላሴ ወደሚባል ቤተክርስቲን ጫካ ውስጥ ወሰዱንና የሞቱ የነሱን ታጣቂዎች ተሸከሙ አሉን፡፡ ልብሳችንን ጫማችንም አስወልቀው በባዶ እግራችን አስኬዱን፤ እንደዚ አድርገው ወደ ሽሬ አመጡን፤ እጅ የሰጡ አመራሮቻችንንም ገደሏቸው፡፡ በተለይ ኦሮሞና አማራን እየለዩ አስቀሯቸው፡፡ የደቡብ ተወላጆች ላይም አይናቸው ላይ በርበሬ እየጨመሩ ያሰቃይዋቸው ነበር፡፡ በረሀብም የሞቱ አሉ፡፡ የሞቱትን አስፋልት ላይ ሲጎትቷቸው ነበር፤ አንዳንዶቹን አፍነው የት እንደወሰዷቸው አናውቅም፡፡ ከባለቤቴ ጋር እስከ ሽሬ ድረስ አብረን ከመጣን በኋላ እርሱን እዛው አስቀሩት፤ አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አላውቅም” ከዚህ በላይ ኮንስታብል አለምነሽ  መናገር አልቻለችም፤ እንባዋንም መግታት ተሳናት፡፡

ጁንታው በህግ ማስከበር ዘመቻው በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ከሁሉም የትግራይ አካባቢዎች ተወግዷል:: ከጁንታው አባላት መካከል እጃቸውን መስጠት የጀመሩ ያሉ ሲሆን ቀሪ የጁንታው አባላት በጠባብ አካባቢ  መከላከያ ሰራዊቱ በቅርብ እየተከታትላቸው እንደሚገኝ መንግሥት መግለፁ ይታወሳል::

በኢያሱ መሰለ

The cruel corner of Junta is on the north command - in the language of the soldiers
 👉 "An army officer surrendered and was beaten by a tank"
 👉 "They told me to take my baby and carry the bodies of the militants."
 .... "... they even killed the wounded"
 ተናል "We also heard that they cut off women's breasts"
 መዋል "They committed atrocities by dragging the bodies of members of the armed forces on the road."
 .... ".... they were adding pepper to their eyes and torturing them"

 *************
 (IPod)

 Her name is Bethlehem.  She is a member of the 1st Battalion of the 11th Battalion.  She witnessed the brutality of the apostate TPLF Junta militants against members of the Northern Command.  It has happened to her,  She says that even Junta's cruelty is unimaginable to humans.

 "Before the incident, the members of the battalion, who were the messengers of the junta, were hiding and gathering every day," he said.  The rest of the army has been relentlessly covering theirs as they have not been on duty.  The rest of the army will be chased away by locusts.  We have donated blood.  We support the community in many other ways, ”said Bethlehem.

 On the day of the attack, they were being chased by locusts all day long as they lay down to rest on their backs.  Bethlehem, the chief of the ten;  “At 5:30 pm, we were shot in the head.  From the inside, those who had been gathering and plotting in the past were the evil intentions of Junta.
_

የወታደሯ የ3 ቀናት የመቃብር ውስጥ ቆይታ።

የወታደሯ የ3 ቀናት የመቃብር ውስጥ ቆይታ። 
የወታደሯ የ3 ቀናት የመቃብር ውስጥ ቆይታ። 
የወታደሯ የ3 ቀናት የመቃብር ውስጥ ቆይታ

****************** 

መ/ወ/ር ተስፋነሽ ጋቢሳ ትባላለች። የመከላከያ ሠራዊቱ ልዩ ኃይል አባል ናት፡፡ ጁንታው በከፈተው ውጊያ ለመፋለም በራያ ግንባር ከክፍሏ አባላት ጋር ተሰልፋ በርካታ ግዳጆችን በድል ተወጥታለች።

ጠላት ለዓመታት ያዋጋኛል ብሎ እንዳዘጋጀው በወታደራዊ ጠበብቶቹ በግንባሩ መሪ ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ እና ሌሎች አመራሮች የተመሰከረለት ልዩ ቦታው አዲ ቀይህ የተባለው ቦታ ላይ ለ3 ቀናት በተደረገው ፍልሚያ በጀግንነት እየተዋጋች ሳለ ያልጠበቀችው ሁኔታ ገጠማት። 

በዚህ ቦታ ላይ ጠላት ሙሉ ኃይሉን ተጠቅሞ መዋጋት በመጀመሩ እንደ ሌሎች ምሽጎች በቀላሉ መስበር ካለመቻሉም ባሻገር፣ ጠላትን ለመደምሰስ የገባውን የወገን ጦር ለመቁረጥ መልሶ ማጥቃት በማድረጉ ወገን የኃይል ሚዛኑን ለማመጣጠን እና ሌሎች ወታደራዊ ጥበቦችን ለመጠቀም ሲባል ከጠላት ከበባ ሰብረው እንዲወጡ ሲደረግ መ/ወ/ር ተስፋነሽ በጠላት ቀጣና ተቆርጣ ትቀራለች። 

ወ/ር ተስፋነሽ ወገን አሸንፎ ሞሽጉን እንደሚሰብር ሙሉ እምነት ስለነበራት፣ የታጠቀችውን ስናይፐር ጨምሮ መሬቱን ቆፍራ ራሷን ጉድጓድ ውስጥ ትቀብራለች።  አፈሩን በእጆቿ በላይዋ ላይ በመመለስ ከመሬቱ ጋር በሚገባ ትመሳሰላለች። 

በዚህ ሁኔታ ላይ እያለች ብዙ የጁንታው ታጣቂዎች በላይዋ ላይ እየተረማመዱ ከወዲያ ወዲህ ይመላለሱባታል። 

መማረክን ከሞት በላይ የምትፈራው እና ድሉን ሳታይ መሞት የማትፈልገው ጀግናዋ መ/ወ/ር ተስፋነሽ ያላት አማራጭ ሁሉንም ችላ ዝም ማለት ብቻ ነበር።

ነገር ግን ጁንታው ከአጠገቧ ላይ ዲሽቃውን ሲጠምደው፣ አንዱ የዲሽቃው መቋሚያ እግር ከተቀበረችበት አቅራቢያ ላይ አረፈ።  ዲሽቃውም ቦታውን ሳይለቅ ከአቅራቢያዋ እየተኮሰ 3 ቀናት ተቆጠሩ።

በእነዚህ ቀናት ራሷን እንደ ሙት ያለ ምንም እንቅስቃሴ ትንፋሿን አምቃ ምድር ውስጥ ሳለች ከፍተኛ ውጊያ ከተካሄደ በኋላ ሠራዊቱ ምሽጉን ሰብሮ ድል ማድረጉን የዲሽቃው መቋሚያ እግርም እሷ ካለችበት ጉድጓድ አካባቢ መነሣቱን አወቀች፡፡

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ራሷን ከቀበረችበት በማስነሣት አካባቢውን ስትመለከት ጀግኖች ጓዶቿ ጁንታውን አባርረው ቦታውን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረውታል። 

እሷ ብታውቃቸውም እነሱ ግን ሙሉ ሰውነቷ ከአፈር ስለተመሳሰለ አላወቋትም ነበርና 'እጅ ወደ ላይ' የሚል ድምፅ ሰማች።

እሷም እጆቿን አንሥታ 'ወገን ነኝ ' የሚል ድምፅ በደስታ ብዛት ተውጣ አሰማች። እነሱም ወደ ኋላ በመውሰድ ከ3 ቀናት በኋላ እህል እና ውኃ እንድትቀምስ አድርገዋታል።
መ/ወ/ር ተስፋነሽ ጋቢሳ በአሁኑ ወቅት በሙሉ ጤንነት ወደ መደበኛ ተግባሯ ተመልሳ ጁንታውን ለደምሰስ እየተፋለመች ትገኛለች ሲል ከመከላከያ ሠራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Thursday, December 3, 2020

The midnight attack on an army camp that plunged Ethiopia into war

https://gf.me/u/zayxcs
https://www.africanews.com/embed/1302098

It was late on the first Tuesday in November, and Captain Hussen Besheir, an Ethiopian federal soldier, was on duty at a guard post outside the military camp in Dansha.

It was close to midnight when he saw headlights approaching.

Ten armed members of the Tigrayan special forces got out of the vehicle and demanded to see the camp's commander.

"'We're not here for you'," Hussen recalled them saying. "'We want to talk to the leaders.'"

Hussen refused. An argument ensued and gunfire rang out.

They were the first shots in a conflict that has since engulfed northern Ethiopia's Tigray region, killing many hundreds of people and forcing tens of thousands from their homes.

This week AFP visited the Dansha barracks, home to the Fifth Battalion of the Northern Command of the Ethiopian military, after gaining rare access to Tigray, where a near-complete communications blackout has been in place since the fighting began.

Shell casings littered the camp's grounds, and bullet holes were punched in the walls of buildings and sides of military trucks.

A metal sign at the entrance reading, "We need to protect the constitution from anti-development forces and lead our country to renaissance," was so perforated with gunfire as to be almost illegible.

'Betrayal'

Hussen and others described hours-long rifle and grenade battles against fighters loyal to the Tigray People's Liberation Front (TPLF), including special forces and militiamen, joined by some federal soldiers of Tigrayan ethnicity who turned against their comrades.

Echoing a statement from Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed, Hussen said soldiers "were killed in their pyjamas", adding, "What happened here is even worse than that."

"Betrayal alone wouldn't describe the feeling that I have. These are soldiers who have been eating and drinking with us," he said of those former federal troops who allegedly turned their guns against them.

The government in Addis Ababa has claimed the attack on Dansha - and a simultaneous assault on another barracks in the regional capital Mekele - as justification for its military offensive in Tigray since November 4.

It points to an interview on Tigrayan media in which a prominent TPLF supporter, said a pre-emptive strike was "imperative".

"Should we be waiting for them to launch attacks first? No," said Sekuture Getachew, in the interview, which Abiy's office has called a "confession".

Confrontation between Abiy and the TPLF was a long time coming. The TPLF dominated Ethiopian politics for nearly three decades until anti-government protests swept Abiy to power in 2018.

Since then the TPLF has complained of being sidelined and scapegoated for the country's woes.

The rift widened after Ethiopia postponed national elections because of the coronavirus pandemic. Tigray went ahead with its own vote, then branded Abiy an illegitimate ruler.

Ethnic forces

Tadilo Tamiru, a sergeant in the government-aligned Amhara special forces, was 50 kilometres to the south with his 170-strong unit, in a small town along the border between the Tigray and Amhara regions, when the fighting began in Dansha.

They were ordered to march north to join the battle.

"The support we provided the Ethiopian defence forces was very important," he said, claiming it turned the tide against the TPLF.

In the hours and days after the fighting in Dansha, Abiy sent troops, tanks and jets into Tigray to oust the "criminal clique" of TPLF leaders. On Thursday, he ordered a "final" assault on Mekele, after the TPLF rejected a 72-hour deadline to surrender.

'A lot of shooting'

Restrictions on access to the conflict zone make it hard to verify claims from either side, but a visit to Dansha revealed that a battle, limited in scope, took place: while the military barracks was bullet-scarred, the surrounding town was unscathed.

Some shops were boarded up but the town - unlike others in Tigray visited by AFP - was far from abandoned.

The main thoroughfare, tree lined and paved, was busy with cattle and vehicles, women roasting coffee on the roadside as a group of boys played pool at a pavement table.

Relieved residents described fearfully listening as gunfire erupted from the barracks.

"During the first night there was a lot of shooting. And when we woke up in the morning, we could see bullets everywhere," said Mulye Bayu, a wide-eyed 19-year-old in a floral dress, who runs a roadside cafe.

United Ethiopia -Rebuilding Communities Fundraiser

to Donate please go 

Wednesday, December 2, 2020

የፌዴራል ፖሊስ ልዩ ኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን መቐለ ከተማ ገባ

የፌዴራል ፖሊስ ልዩ ኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን መቐለ ከተማ ገባ
*******************

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ልዩ ኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን ዛሬ ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም መቐለ ከተማ መግባቱን አስታውቋል።

የፌዴራል ፖሊስ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት የጁንታውን ተፈላጊ ወንጀለኛ ቡድን ማደን መጀመሩንም ነው ያስታወቀው። 

የኮማንዶ ቡድኑ በከተማዋ በሚያደርጋቸው አሰሳዎችና የተለያዩ ኦፕሬሽኖች እንዲሁም በወንጀል ምርመራ ቡድኑ የሚገኙ ውጤቶችን በቀጣይ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግም ኮሚሽኑ አስታውቋል። 

በትግራይ ክልል በሚገኙ ባንኮች ሒሳብ የከፈቱ እና ከትግራይ ውጭ ያሉ ደንበኞች በያሉበት አካባቢ ሒሳባቸውን ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ተፈቅዷል"፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ

"በትግራይ ክልል በሚገኙ ባንኮች ሒሳብ የከፈቱ እና ከትግራይ ውጭ ያሉ ደንበኞች በያሉበት አካባቢ ሒሳባቸውን ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ተፈቅዷል"፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 
****************** 

በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በወንጀል ተጠርጥረው ሂሳባቸው እንዳይንቀሳቀስ ከተደረገው ደንበኞች በስተቀር በትግራይ ክልል በሚገኙ ባንኮች ሒሳብ የከፈቱ እና ከትግራይ ውጭ ያሉ ደንበኞች በያሉበት አካባቢ ሒሳባቸውን ከዛሬ ኅዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ማንቀሳቀስ እንዲችሉ መፈቀዱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አስታወቀ። 

በትግራይ ክልል እየተከናወነ ባለው የሕግ ማስከበር እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የፀጥታው ሁኔታ ለባንኮች አመቺ በሆነባቸው ከተሞች ባንኮች ተከፍተው ሥራ እንዲጀምሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሚመለከታቸው ጋር እየሠራ መሆኑን ባንኩ አስታውቋል። 

የፀጥታው ሁኔታ አመቺ ባልሆነባቸው ከተሞች ደግሞ ባንኮች ተዘግተው የሚቆዩ መሆኑን ነው የገለጸው። 

በትግራይ እየተካሄደ ባለው የሕግ ማስከበር እንቅስቃሴ ምክንያት የፀጥታው እና የኔትወርክ ሁኔታ እስኪሻሻል ባንኮች ተዘግተው እንዲቆዩ መወሰኑ ይታወሳል። 

"Banks opened in banks in Tigray Region and allowed outside of Tigray to move their accounts wherever they are": National Bank of Ethiopia
 ******************

 The National Bank of Ethiopia (NBE) said in a statement to ABC that customers who have opened accounts in banks in the Tigray Region and outside Tigray have been allowed to move their accounts from November 23, 2013.

 The National Bank of Ethiopia (NBE) said it is working with stakeholders to reopen banks in Tigray State.

 He said banks would remain closed in insecure cities.

 It is to be recalled that due to the ongoing law enforcement activities in Tigray, it was decided to keep the banks closed until the security and network situation improves.

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮቪድ-19 ክትባትን ጨምሮ ሌሎች ክትባቶች የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ለመጀመር ከአሊባባው ሳይናው ድርጅት ጋር ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮቪድ-19 ክትባትን ጨምሮ ሌሎች ክትባቶች የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ለመጀመር ከአሊባባው ሳይናው ድርጅት ጋር ስምምነት ተፈራረመ
****************** 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመድኃኒት ማቀዝቀዣ በተገጠመላቸው የካርጎ አውሮፕላኖቹ የኮቪድ-19 ክትባትን ጨምሮ ሌሎች ክትባቶች የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ለመጀመር ከአሊባባው ሳይናው ግሎባል ድርጅት ጋር ስምምነት ተፈራርሟል። 

የትራንስፖርት አገልግሎቱ የመድኃኒት ማቀዝቀዣ እና የሙቀት ቁጥጥር በተገጠመላቸው አውሮፕላኖቹ የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል። 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ለማጓጓዝ ሙሉ ዝግጅቹን አጠናቆ ክትባቱ ለትራንስፓርት ዝግጁ እስከሚሆን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ አየር መንገዱ ገልጿል። 

ጀግናዋ ም/አስር አለቃ ከሀዲውን ኮሎኔል ማንቁርቱን ይዛ አስረከበች

ሕዳር 23 ቀን 2013 

ጀግናዋ ም/አስር አለቃ ከሀዲውን ኮሎኔል ማንቁርቱን ይዛ አስረከበች ።

20ኛ ቃሉ ክ/ጦር ሰሜን ዕዝ ካሏት የጦር ክፍሎች ውስጥ አንዱ ነው። በዚህ ክ/ጦር 1ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አባል የሆነችው ምክትል አስር አለቃ ገባያነሽ ደባልቄ የሻለቃው አዛዥ ኮሎኔል ሰለሞን ገ/ዮሃንስ አጃቢ ነች ። ጁንታ መሆኑን ግን አታውቅም ።

የእብሪት ርምጃቸው ከመጀመሩ ከ3 ቀናት በፊት ሰራዊቱ የምግብና መጠጥ አገልግሎት የሚያገኝባቸውን መንገድ በመዝጋት ሰራዊቱን ለከፍተኛ ርሃብና ጥም ዳርጏል ።

ሁሉም የሰራዊት አባል የግል ትጥቁን በአንድ ክፍል በማስቀመጥ በህብረተሰብ የድጋፍ ስራዎች ላይ እንዲረባረብ ማድረጉን ትናገራለች ።

በተለይም ጥቅምት 24 ቀን 2013 ምሽት ላይ ሁሉንም የጥበቃ ቦታዎች በትግራይ ተወላጅ የሰራዊት አባላት እንዲሸፈኑ በማድረግ ፣ የከሃዲው ቡድን ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ምንም አይነት ዝግጅትና ትጥቅ ባልነበረው ሰራዊታችን ላይ ከፍተኛ ተኩስ እንዲከፍትም አድርጏል ብላለች ።

ሆኖም ታላቅ ጀግንነትና ኢትዮጵያዊ ማንነትን የወረሰው ጀግናው ሃይላችን የማይታሰቡ ጀብዶችን ጭምር በመፈፀም ፣ ወደ ኤርትራ ስልታዊ ማፈግፈግ በማድረግ ራሱን ማዳን ችሏል ብላለች ።

በዚህ ሁሉ ግፍና በደል መሃል የሻለቃዋ ዋና አዛዥና ለዘመናት የመራቸውን የሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የካደው ኮሎኔል ሰለሞን ገ/ዮሃንስ ራሱን መፀዳጃ ቤት ውስጥ በመደበቅ በጁንታው የተሰጠውን ተልዕኮ መፈፀም እንደጀመረ በሃዘን ስሜት ውስጥ ሆና አስታውሳለች ።

ውትድርና በኢትዮጵያዊነት ፍቅር መታጠብና በጀግንነት ካባ መድመቅ ነው የምትለው እንስቷ ጀግና ፣ ራስህን ለሃገር አሳልፈህ ከሰጠህ ኢትዮጵያዊ መሆን ብቻውን ጀግንነትን ይወልዳል ስትል የቀድሞ አለቃዋን እንዴት ከስሯ እንዲንበረከክ እንዳደረገችው እንዲህ ታጫውተናለች ።

"... ሰራዊታችን በታፈነበት ጥቅምት 24 ምሽት 2 ሰዓት ላይ በከባድ መሳሪያ የታጀበ ተኩስ ወደ ካምፓችን ተተኮሰ፣ በዚህ ሰዓት ወደ  መፀዳጃ ቤት ራሱን የደበቀው ከሃዲው አዛዥ ተብዬ ፣ እኔ በትግራይ ሚሊሻና ልዩ ሃይል ጥይት ከምሞት አንተን ገድዬ ራሴን አጠፋለሁ አልኩት፣ ተኩሱ በርትቷል፣ ሁሉም ራሱን ለማዳን ወደህሊናው የመጣለትን አማራጭ እየተጠቀመ ይሯሯጣል..."

"... በመጨረሻም ከተደበቀበት መፀዳጃ ቤት እንዲወጣና እኔ የምለውን ብቻ እንዲፈፅም እሽ የማይል ከሆነ ግን እንደምገድለው አስጠነቀቁት፥ እሱም በፍርሃት ውስጥ ሆኖ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ ወደነገርኩት ቦታ መጣ፥ ሽጉጡንና ማዕረጉን እንዲሰጠኝ አደረኩ፣ ከዛም ጫማውን እንዲያወልቅ አድርጌ በየመንገዱ ከማገኛቸው የሰራዊት አባላት ጋር በመተባበርና ሙሉ ለሊት የእግር ጉዞ በማድረግ ኤርትራ ይዤው በመግባት ታማኝ እና ሙሉ ኢትዮጵያዊ ለሆኑ አመራሮች አስረከብኩ  ።"

ሰራዊታችን በራሱ ወገኖች የደረሰበትን በቃላት የማይገለፅ ግፍና በደል ተሸክሞ ቂምን ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ፍቅር አስቀድሞ ለድል በመብቃቱ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማትም ምክትል አስር አለቃ ገበያነሽ ደባልቄ ስሜቷን አጋርታናለች ።

ኢትዮጵያችን ምንም እንኳን በራሱ ጉያ ተወሽቀው ሳቋን እየቀሙ ውርደቷን የሚያፋጥኑና መበተኗን ገሃድ ለማውጣት ሌት ተቀን የሚሯሯጡ ወጪት ሰባሪዎች ቅዠታቸውን ቢኖሩትም ፣ ክብሯን የሚያስጠብቁ ከራሳቸው ህይወት ይልቅ የሃገራችውን ክብር የሚያስቀድሙ ፣ የማይታመን ጀግንነት እየፈፀሙ ኢትዮጵያችንን ከፍ ያደረጉ የበርካታ የቁርጥ ቀን ልጆች ባለቤት ናት ኢትዮጵያ !

ምክትል አስር አለቃ ገባያነሽ ደባልቄም ጀግና ማፍራት የማትሰለቸው ሃገራችን ከሰጠችን እንቁ ኢትዮጵያውያን አንዷ ናት ። እንዳንቺ  አይነት ኩሩ ኢትዮጵያዊ ሁሌም በኢትዮጵያዊ ክብር ደምቆ ይኖራል ።

የከሃዲዎች መጨረሻ ፣ ሃገርን ለማዋረድ ባሴሩት ህልም ውስጥ ተጠልፎ መውደቅ ነው ።

አበበ ሰማኝ ( ከግዳጅ ቀጣና )
ፎቶግራፍ ብርሃኑ ወርቁ

Tuesday, December 1, 2020

በአማራ ክልል የሚገኙ 23 ከተሞች በከተማ አስተዳደርነት እንዲመሩ መወሰኑ ተገለጸ

በአማራ ክልል የሚገኙ 23 ከተሞች በከተማ አስተዳደርነት እንዲመሩ መወሰኑ ተገለጸ 
*************************

በአማራ ክልል የሚገኙ 23 ከተሞች በከተማ አስተዳደርነት እንዲመሩ መወሰኑ ተገልጿል፡፡

በከተሞች የአደረጃጀት ፈርጅ መወሰኛና ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 65/2001 መሰረት መስፈርት አሟልተው የተገኙ 23 ከተሞች ከፈርጅ ሶስት ወደ ፈርጅ ሁለት የደረጃ ሽግግር ማለትም በከተማ አስተዳደርነት ለመመራት በክልሉ ከተማ ልማትና ቤቶች ኮንስትራክሽን ቢሮ አጥንቶ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ተቀብሎ ም/ቤቱ አጽድቋል፡፡

ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ በስፋት መክሮ የከተሞችን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ከመፍታትና ወደ ፊት ያላቸውን የመልማት ዕድል የተጠቀሱ ከተሞችን የደረጃ ሽግግር አጽድቋል፡፡

በዚህም መሰረት ከደቡብ ጎንደር ዞን ወገዳ፣ሀሙሲት እና እብናት፣ከአዊ ብሄረሰብ ዞን አዲስ ቅዳም፣አገው ግምጃ ቤት፣ፈንድቃ፣ከምስራቅ ጐጃም ዞን ደብረ ወርቅ፣ሉማሜ አማኑኤል እና ግንደ ወይን፣ከምዕራብ ጐጃም ዞን ሽንዲ፣ጅጋ ከተሞች ይገኙበታል፡፡

ከደቡብ ወሎ ዞን ከለላ፣ቱሉአውሊያ፣ሀርቡ፣አቅስታ፣ደጎል፣ ከሰሜን ሽዋ ዞን ደብርሲና፣ሞላሌ፣አንዋሪ፣ከሰሜን ወሎ ዞን ጋሸና እንዲሁም ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ደግሞ ቆላ ድባ እና ሻውራ ከተሞች መስፈርቱን ያሟሉ ሆነው በመገኘታቸው በከተማ አስተዳድር እንዲመሩ ተወስኗል፡፡

በመሆኑም ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ የተጠቀሱ ከተሞች ከፈርጅ ሶስት ወደ ፈርጅ ሁለት የደረጃ ሽግግር በማድረግ የከተማ አስተዳደርነት ዕውቅና እንዲያገኙ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ወስኗል፡፡

ተግባራዊነቱን በተመለከተም ክልሉ ካለበት ነባራዊ ሁኔታ አንፃር የበጀት እጥረት ያገጠመ በመሆኑ የደረጃ ሽግግር የተፈቀደላቸው 23ቱ ከተሞች ከክልል የስራ ማስኬጃም ይሁን ሌላ በጀት የማይመደብ መሆኑን አውቀው በራሳቸው በጀት ቁጠባን መሰረት በማድረግ ወደ ስራ መግባት እንዳለባቸው ማስታወቁን ከአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሰሜን ዕዝ ከተለያዩ ብርጌዶችና ክፍለ ጦሮች ታግተው የነበሩ 1240 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ሠቆጣ ገቡ

ከሰሜን ዕዝ ከተለያዩ ብርጌዶችና ክፍለ ጦሮች ታግተው የነበሩ 1240 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ሠቆጣ ገቡ
*****************************
ከሰሜን ዕዝ ከተለያዩ ብርጌዶችና ክፍለ ጦሮች በጁንታው ኃይል ታግተው የነበሩ 1240 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ዋግኸምራ ዞን ሰቆጣ ሠቆጣ ከተማ ገብተዋል።

የሠራዊት አባላቱ ከህዳር 20፣2013 ዓ.ም ከ 8 ሰዓት ጀምሮ እስከ እስከ ትላንት ማታ 12 ሰዓት ድረስ ነው ወደ  ሰቆጣ የገቡት። 

የመከላከያ ሰራዊት አባላቱ ሰቆጣ ለመግባት በርካታ ውጣ ውረድ  ማለፋቸውንም ገልጸዋል።
በተለይም የተከዜን ኮሪደር ተከትለው በቀን እና  ሌሊት የእግር ጉዞ  እንዲሁም ወንዝና ጫካ እያቆራረጡ ሰቆጣ  መግባታቸውን የሠራዊቱ አባላት ተናግረዋል።

የአካባቢው  አስተዳደር ለሰራዊቱ የምግብ እና የህክምና አቅርቦት ማመቻቸቱም ተመልክቷል።
 
በራሄል ፍሬው

የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እጃቸውን ሰጡ

የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እጃቸውን ሰጡ

ወ/ሮ ኬርያ የሕወሓት ከፍተኛ አመራርና በመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊነት የነበራቸው ናቸው።

ነገር ግን የጁንታው ጥቅም ይሻለኛል ብለው ወደ መቀሌ የሸሹ ሲሆን ሾፌራቸው ግን በወቅቱ የመንግሥትን ንብረት ለጁንታው አልሰጥም ብሎ ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ መኪናውን ይዞ ተመልሷል። 

ከዚህም ጋር ተያይዞ ሌሎችም የሕወሓት አመራሮች እንደ ወ/ሮ ኬርያ በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጡ መንግሥት ጥሪውን አቅርቧል።

Monday, November 30, 2020

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ ግጭቶችን አስመልክተው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ ግጭቶችን አስመልክተው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-
************************

• በእያንዳንዱ ሳምንት የጦርነት ድግስ ነበር፣ መንግስት ስራ እንዳይሰራ በየቦታው ችግር ይፈጠር ነበር፣ 113 የሚሆኑ ግጭቶች ተፈጥረዋል፡፡

• የብሔር፣ የሃይማኖት ግጭት እንዲነሳ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡

• አንድ ጎጃሜ ከጎጃም ወደ አምቦ ሲሄድ ወገኔ ነው ብሎ ነው የሚሄደው፣ ይህ ህዝብ በጥርጣሬ እንዲታያይ ነው ለማድረግ የሞከሩት፡፡

• ባለፈው ሁለት ዓመት ተኩል በኦሮሚያ ውስጥ 37 ግጭቶች ነበሩ፡፡

•  ባለፈው ሁለት ዓመት ተኩል በአማራ ክልል 23 ግጭቶች ነበሩ፡፡

• በአማራ ክልል ቅማንት የወሰድን እንደሆነ ጎንደር ከሁሉም ብሔሮች ጋር አብሮ ለመኖር ልምድ ያለው አከባቢ ነው፣ ቅማንትና አማራ ተብሎ መለየት በማይቻል ደረጃ ነው የህዝቡ አኗኗር፡፡

• በቤንሻንጉል ጉሙዝ  15 ግጭቶች ተከስተዋል፡፡

•  አዲስ አበባ ላይ 14 ግጭቶች ተከስተው ነበር፡፡

• የሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን በተመለከተ ከሃጫሉ በተጨማሪ ሌሎች የኦሮሞና የአማራ አመራሮችን በመግደል ግጭቱን የኦሮሞና የአማራ ለማስመሰል ጥረት ተደርጓል፡፡

• ከዚያ በኋላ ሃጫሉን አጥተናል እና ሌሎች ጉዳቶች እንዳይደርሱ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

•  በጋምቤላ 7 ግጭቶች ነበሩ፡፡

• በሚዛን ቴፒ፣ ጉራፈርዳ ግጭቶች ተከስቷል፡፡

• ጉጂና ጌዲዮ እንደ አንድ ቤተሰብ የሚኖር ህዝብ ሲሆን፣ እዚያ አካባቢ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ተደርጓል፡፡

• አማራ ክልል፣ ቤኒሻንጉል ያዋስነዋል ተጋጭቷል፣ ኦሮሚያ ያዋስነዋል ተጋጭቷል፣ አፋር ያዋስኗል ተጋጭቷል፣ ትግራይ ያዋስነዋል ነገር ግን አልተጋጨም፡፡

• ሌሎች ክልሎችም ከጎረቤት ክልሎች ጋር እንዲጋጩ ተደርጓል፣ ትግራይ ክልል ጎረቤት ክልል ቢሆንም ከትግራይ ግን አለመጋጨታቸው ግጭቱ ታስቦበት የሚሰራ በመሆኑ ነው፡፡

US embassy celebrates Nigerian doctor who helped Pfizer develop COVID-19 vaccine

US embassy celebrates Nigerian doctor who helped Pfizer develop COVID-19 vaccine
The US embassy in Nigeria has celebrated Onyema Ogbuagbu, a Nigerian-born researcher and medical doctor, for his role in the development of a COVID-19 vaccine.
Pfizer and BioNTech had announced that the first vaccine they developed against COVID-19 could prevent more than 90 percent of people from getting infected.
The vaccine has been tested on 43,500 people in six countries and no safety concerns have been raised. Pfizer was quoted as saying it would be able to supply 50 million doses by the end of 2020, and around 1.3 billion by the end of 2021.

Curated Products for Generation X

https://amzn.to/3VhbwJz GenX Essentials - Curated Products for Generation X ...

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon