Shop Amazon

Monday, December 7, 2015

Songs for Ethiopia by Italy in war time.. የዛሬው ቆይታዬ ከጣልያኑ ጋር









የዛሬው ቆይታዬ ከጣልያኑ ጋር።

ነገሩ የተከሰተው  በአጋጣሚ ነው። የእሁድ ጠዋት ፀሀይን ለመሞቅ ወደ መናፈሻው  ጎራ ስል አንድ እድሜው ወደ 80 አምት የሚጠጋ ሽማግሌ (ነጭ) ውሻውን  ይዞ  ከተፍ አለ። ምንም ፋታ ሳይሰጠኝ ተዋወቀኝ። ስሜንም ጠየቀኝ፣  ስሜ ትንሽ ግር ሲለው የዬት አገር ስም ነው አለኝ እኔም ያው የማማ ኢትዮጵያ ብቸኛው አቻ የሌለው ስም ነው አልሁት። እኔም ብድሬን ለመመልስ ይመስላል በተራየ ከሄት ነው የመጣሀው አልሁት።  ነጭ ቢመስልም አነገገሩ ትንሽ ያዝ ስለሚያደርገው የአሜሪካ ሰላቶ እንዳልሆነ ያስታውቃል። ስውየውም ሰምቼው የማላውቀው የአገር ስም ጠራልኝ። እኔም ግራ ተጋብቼ  “ የት ነው ?” አልሁት ሰውየውም ከጣልያን ነኝ አለኝ፣ እኔም ግራ ተጋብቼ ታዲያ ለምንድን ነው ከዚያ ሰምቼው ከማላውቀው አገር ነህ ያልኸኝ ሰለው አይ እኔ እኮ ያልሁህ በጣሊያንኛ  ገምት ነው ያልሁ ብሎኝ ፈገግ አደረገኝ።

ቀጥሎም ለመሆኑ ስንት አመትህ ነው አለኝ። እድሜየን ነገርሁት። የእሱን እድሜ ግን ብን ካለው ፀጉሩና ከተጨማደደው ቆዳው መገመት ሰለማያዳግት እድሜውን አልጠየቅ ሁትም ። ወደ ሰማንያው ሳይጠጋ አይቀርም።  ከዚያ “ይህንን ሙዚቃ ታውቀዋለህ?”  አለኝና ትንሽ በጣልያንኛ ተቀኘልኝ። እኔም የትም ሰምቼው አላውቅም ስለው
“ አወ ልጅ ልሆን ትችላለህ”  ብሎ ስለ ሙዚቃው አወጋኝ።

እንደነገረኝ ሙዚቃው የጣልያን ወታደሮች ኢትዮጵያን ሊወጉ ሲነሱ  ህዝቡና ወታደሮች የሚዝፍኑት አነቃቂ ዘፈን ነበር። ይገርማል። እኔም ምኔ  ሞኝ ነው ስውዬውን“ ምን ይል ነበር እስኪ በእንግሊዘኛ ንገረኝ ” ስለው ይህን አለኝ።

“ሙዚቃው የሚለው” አለ፣“ የአቢሲንያን  ጥቁር ፊት በጣልያን ፊት ተካው ነው አለኝ።”  “ ምን?” አልሁት።
አወ የጣልያን ታላቁ ህልም ኢትዮጵያን ቀምቶ ህዝቧን ጨርሶ በጣልያን ብቻ ለመሙላት ነበር:: እኔም እባብን የልቡን አይቶ በሆዶ አስተኛው እንደሚባለው የጣልያንንም ከይሲ ሴራ አይቶ ፈጣሪ በአጭሩ አነሳቸው። እኔም ምኔ ሞኝ። ያ ሽማግሌ ጣልያን ልክ ሮም ላይ አብርሃም ደቦጭና ሞገስ አስግዶም ያደርጉትን አስታወሳኝ። ፊቴ ፈካ ብሎ “ታዲያ ምን ያደርጋል ተሽነፋችኋ!!!” አልሁት። አወ እሱም የኔ ኩራት ሳይገባው አልቀረም። ከዚያም በአይኔ ህሊናዬ ጣልያኖች ኢትዮጵያን ቢይዙ ኖሮ ምን እሆን ነበር የሚለውን አሰላሰልሁ።
እኔ እፈጠር ነበር?መልሱን ማግኘት አልቻልሁም ግን አንድ ነገር እንደሚሆን  አወቅሁ  ያም ዛሬ የምናያት ኢትዮጵያ እንደማትኖር። እኔም ማንነቴ እንደ ኑግ ተወቅጦ ተለውሶ ማንንቴ ለዘላልም ተዳፍኖ ይቀር ነበር። አወ ዛሬ በኩራት የምፅፈው አማርኛም ዳብዛው ጠፍቶ ጣሊያንኛ ለአለቆቼ ስመልስ ባይኔ ታዬኝ። ያ ኔ ነው ሂወታቸውን፣ አንገታቸውን ሰጥተው፣ ደረታቸውን ለመትረየስ አፈሙዝ ግልብጠው ስጥተው ማቄን ጨርቄን ሳይሉ ቤት ንብረታቸውን ትተው በዱር በገደል ቅጥል በልተው ጎርፍ ጠጥተው ፣ ቅማል በላያቸው ላይ  እንደ ዝናብ እየዘነበ፣ እርሃብና ጥምን አምቀው ይዘው እማማ ኢትዮጵያን ለዚህ ያበቋትን የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆችን በአይነ ሂሊናዬ ቃኘኋቸው። አፍረትም ተሰማንኝ::

እኔን ለሀገሬ ምን አደርግሁላት????  የሚለውን ሳስብ። መጪው ትውልድስ ከኔ ምን ይወርሳል ጉድ ነው አልሁ። ያ ፈረንጅ (ሰላቶ) እኔን  በሃሳብ ውቅያኖስ ውስጥ ለቆ ጉዞውን ቀጠለ። እኔ ግን ሃሳቤን ከኒያ የቁርጥ ቀን ልጆች ጋር አድርጌ ጉዞየን ቀጠልሁ። ለራሴም ቃል ገባሁ ይህንን ለማካፈል።  ባለኝ አቅም እና ችሎታ ቀሪውን የሙዚቃ ስንኝ እና ግጥም ለማግኘት ወደ መከረኛው ጉግል አንባ አመራሁ። ያስብሁም ተሳካ። ጣልያን ኢትዮጵያን ልትወጋ ስትመጣ የተዘፈኑ ዘፈኖችን አንድ በአንድ አገኘሁ። ጉድ ነው አልሁ። ፈጣሪ አያድርገውና ቢያደርገው ኖር  የሀገራችን ዘፋኞች በጣሊናኛ ነበር የሚያዝናኑን። እረ ስንቱ?  እነ ማሪቱ ለገሰ ማራቸው አልቆ፣ እነ እሳቱ ተሰማ እሳታቸው ተዳፍኖ፣  እነ ሜሪ አርሚዴ  መሪ አልባ ሆነው፣ እነ ጥላሁን ገሰሰ ጥላቸው ተገፎ ሁሉም እርቃናቸውን ይቀሩ ነበር። ደግነቱ የኢትዮጵያ ጀግኖች አርቆ አሳቢ ለትውልድ ተቆርቋሪ ነበሩና  ማሪቱም ማር፣ እሳቱም እሳት፣  ጥላሁንም ጥላ ሁሉም ዘፋኞች ዘፋኝ እንዲሆኑ አድርገዋል። ታዲያ የነዚህ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች ውለታችው ምን ይሆን? መልሱን ለእናንተው
ለሁሉም ጣልያን ለኢትዮጵያ የዘፈነላትን ዘፈን በከፊል እንሆ

 ==================================

======================================= 

Adua

Words: Nino Rastelli Music: Dino Olivieri

======================================= 

Amba Alagi

  Words: Cap. Alfredo De Biasio Music: Dino Olivieri

==========================================

Cantate di legionari

Words: Auro D'Alba Music: Francesco Pellegrino
canz

================================================ 

Cara mamma

Words: C. Bruno Music: Eldo Di Lazzaro
=======================================
=======================================

---------------------------------

Faccetta nera/Little Black

Words: Renato Micheli Music: Mario Ruccione 
==================================================
=============================

==================================

==================================
==================================
==================================

No comments:

Post a Comment